የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማና የሰብዓዊ መብቶች ፋይዳዎች

gettyimages-1229585139-612x612.jpg

Aboriginal people dance at Sydney Harbour, Australia. Credit: Xinhua News Agency/Xinhua News Agency/Getty Images

ቅዳሜ ኦክቶበር 14 / ጥቅምት 3 በመላ አውስትራሊያ ለአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ቀዳሚ ባለ አገርነት ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና ለመቸርና በተለይ እነሱን አስመልክቶ አዋኪና ጎጂ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በቋሚ አካልነት ተሰይሞ ለመንግሥት ሥራ አስፈፃሚና ፓርላማ የመፍትሔ ሃሳቦችን የሚያቀርብ ጉዳይ አስፈፃሚ አካል ለማቆም ሕዝበ ውሳኔ ይካሔዳል። ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርት ማዕከል ገዲብ ተመራማሪና መምህር የድምፅ ለፓርላማን የሰብዓዊ መብቶች ፋይዳዎች ነቅሰው ያስረዳሉ።


አንኳሮች
  • ድምፅ ለፓርላማ
  • ዓለም አቀፍ የነባር ዜጎች ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ መርሆዎችና ደረጃዎች
  • የድምፅ ለፓርላማ ክሽፈትና መዘዞቹ፤ ስኬትና ትሩፋቶቹ

Share