ለአውስትራሊያ ድምፅ ለፓርላማ ሕዝበ ውሳኔ ድምፅዎ የድጋፍ ነው የተቃውሞ?

Community The Voice.jpg

A general view of Uluru as seen from the designated sunrise viewing area at Uluru. L-R: Selam Tegegn (Perth, WA), Tilaye Tekete (Adelaide, SA), and Addis-Alem Tsegaye (Brisbane, QLD). Credit: Lisa Maree Williams/Getty Images/ Tegegn, Teketel, and Tsegaye

የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅናን አግኝተው ቋሚ የድምፅ ለፓርላማ አማካሪ አካል ለማቆም ቅዳሜ ኦክቶበር 14 / ጥቅምት 3 ይሁንታን ለመስጠት ወይም ለመንፈግ አገር አቀፍ ሕዝበ ውሳኔ ይካሔዳል። ኢትዮጵያውያም - አውስትራሊያውያንም በ 'ይሁን ' ወይም 'አይሁን ' ግለ ውሳኔ የሕዝበ ውሳኔ ድምፃቸውን ይሰጣሉ። ወ/ሮ አዲስ ዓለም ፀጋዬ ከኩዊንስላንድ፣ አቶ ጥላዬ ተከተል ከደቡብ አውስትራሊያና ነርስ ሰላም ተገኝ ከምዕራብ አውስትራሊያ የድምፅ ለፓርላማ አተያየትና የሕዝበ ውሳኔ ድምፃቸውን እንደምን ለመስጠት እንደወሰኑ ይናገራሉ።


አንኳሮች
  • የድምፅ ለፓርላማ ፋይዳዎች
  • የይሁን፣ አይሁንና ገና አልወሰንኩም አተያዮች
  • የሕዝበ ውሳኔ ቀን

Share