የዘመድ አዝማድዎ የቁማር ሱስ ያሳስብዎታል? እንደምን ሊደግፏቸው እንደሚችሉ እነሆን

ቁማር የሚያስከትላቸው መዘዞች በበርካታ መልኮች ይከሰታሉ። አሉታዊ ተፅዕኖዎቻቸው የሚያርፉት ቆማሪው ላይ ብቻ ሳይሆን በቤተሰብና ወዳጆችም ጭምር ነው። ዘመድ አዝማድዎ በቁማር ሱስ ተጠምደው ያሉ ወይም ከሱስ በመላቀቅ ላይ የሚገኙ ይሁኑ፤ እገዛን ማግኘትዎ ጠቀሜታ አለው። አውስትራሊያ ውስጥ እርዳታዎች በተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛሉ።

slot machines.jpg

Pokies present more risk of harm than any other form of gambling, according to an NSW Responsible Gaming Fund report. Credit: Getty Images/Alina555

አንኳሮች
  • በቁማር ሳቢያ ሊከሰት የሚችል ጉዳት ከፋይናንስ ወደ አዕምሮ ጤና ሊያመራ ይችላል
  • ቤተሰብና ወዳጆች ለመግታት አዋኪ በሆነ ቁመራ ተፅዕኖ ሊያድርባቸው ይችላል፤ ሆኖም እርዳታ አለ
  • ባሕላዊ እምነቶች እርዳታን ከመጠየቅ ሊገቱ ይችላሉ
  • ዘመድን ፍቱን በሆነ መልኩ ለመርዳት ቤተሰብና ወዳጆች ጭምር እርዳታ ሊያገኙ ይገባል
በሲድኒ ዩኒቨርሲቲ የስነ ልቦና ፕሮፌሰር ሳሊ ጌይንስባሪ በኦንላይንና ከኦንላይን ውጪ የሚካሔድ ቁመራ ምናልባትም ሁሌም ጎልቶ አይታይ ይሆናል።
ተዘውትሮ ስውር ሱስ ተብሎ ይጠራል። ስለምን የቁመራ ችግር ያለባቸው መሆኑን ከዓይኖቻቸው ላይ ማየት ወይም ከትንፋሻቸው ጠረን ማሽተት አይቻልምና... ይሁንና ጉዳቱ ግና ተመሳሳይ ነው፤ የፋይናንስ ወጪውም እንዲሁ።
ሳሊ ጌይንስባሪ - በሲድኒ ዩኒቨርሲቲ የስነ ልቦና ፕሮፌሰር
ፕሮፌሰር ጌይንስባሪ የሲድኒ ዩኒቨርሲቲ የቁማር ሕክምና እና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ናቸው።

ከቁማር ሱስ የመላቀቅ መንገድ ሂደት በቁማር ሱስ ለተጠመደውና በዙሪያው ላሉት ሰዎች ጭምር ውስብስብ እንደሆነ ይናገራሉ።

በአብዛኛውም ግርሻ ይገጥማል ሲሉም ተናግረዋል።
Tama ma lana kate talatupe.jpg
E pei fiafia nisi e ta'a'alo peletupe i luga o le 'upega tafa'ilagi, ae o nisi i masini poka, ae tutusa lava le ogaoga o a'afiaga. Credit: Getty Images/becon
7.2% ጎልማሶች ለቁማር ተጎጂነት የተጋለጡ ናቸው።

ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ ማኅበረሰባት ከጠቅላላው ማኅበረሰብ በበለጠ አይቁምሩም፤ ይሁንና ለቁማር ጉዳት ለመዳረግ ይበልጡን ተጋላጭ እንደሆኑ ምርምሮች ያሳያሉ።

ናታሊ ራይት፤ በኒው ሳውዝ ዌይልስ ኃላፊነት የተመላው ቁማር ቢሮ ዳይሬክተር፤ ከዝንቅ ማኅበረሰባት ለቁማር ሱስ የተጋለጡ ሰዎች በሐፍረትና መገለል ዕሳቤ ሳቢያ እርዳታ ወደ አለመጠየቁ እንደሚያዘሙ ይናገራሉ።
ለአብዛኛው ማኅበረሰባት የምክር አገልግሎት ባዕድ፣ የምዕራባውያን ፅንሰ ሃሳብ ነው። እናም፣ በአብዛኛው ነገሮችን በቤተሰብ ውስጥ ይዞ መቆየትን የመሻት ዕሳቤ አለ።
ናታሊ ራይት - በኒው ሳውዝ ዌይልስ ኃላፊነት የተመላው ቁማር ቢሮ ዳይሬክተር
Sad family.jpg
Negatívne dôsledky hazardných hier necítia len samotní gambleri. Credit: Getty Images/uniquely India
የቁማር ሱስ ያለበት ቤተዘመድና ወዳጆችም አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያድርባቸው ያችላል።

በአብዛኛው ከቁማር ሱሱ ጋር በተያያዘ የፋይናንስ ጉዳት ይገጥማቸዋል። ግንኙነታቸው በጭንቀት ሊታወክና ከዚያ ጋር በተያያዘም መዘዞች ሊገጥሟቸው ይችላሉ። .

“እናም፣ እኒህ ሰዎች በሱስ የተጠመደው ሰው እንኳ ከሱስ ለመላቀቅ ቢጥርም፣ ከሱስ ለመላቀቅ የሚጥረውን ሰው ለመርዳት ወይም እየደገፉ እያሉ ለራሳችው እገዛን ሊያገኙ ይገባል” ሲሉ ፕሮፌሰር ጌይንስባሪ ይናገራሉ።

አደም* ከ2014 ጀምሮ ከሱስ በመላቀቅ ላይ ያለ የአረብ ዝርያ ያለው የምዕራብ ሲድኒ ነዋሪ ነው።

አደም ከሱስ ለመላቀቅ ጥረት ባደረገበት ወቅት ሁሉ ከጎኑ ሆነው ድጋፋቸውን ሲቸሩት የነበሩት ቤተሰቦቹ ተፅዕኖ ያደረባቸው መሆኑን ተናግሯል።

ከሱስ የመላቀቅ ሂደቱ ወቅት የቅርብ ዘመዶቹ ለራሳቸው በምክር አገልግሎት በኩል እርዳታን ይሹ እንደነበርም ያስታውሳል።

“አንዳንድ ጊዜ ራስዎ ሱሰኛ እስካልሆኑ ድረስ ለመረዳት አዋኪ በሆነበት ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው፤ ለእኔ ከሱስ መላቀቅ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በተሻለ መልኩ ሊረዱኝ ችለው ነበር።

“ለሆነው ነገር ኃላፊነት የማይመለከታቸው ቢሆንም እንኳ ፕሮፌሽናል እገዛ ማግኘታቸው ግንዛቤ እንዲጨብጡ አስችሏቸዋል ብዬ አስባለሁ። ለሁነቱ መከሰት ስህተቱ የእነሱም ባይሆን፤ እኔን እንደ ግለሰብ በቀላሉ ቃኝተው እንዲገነዘቡኝ አስችሏቸዋል።”

ለአደም ከሱስ ለመላቀቅ መነሻ ነጥብ የሆነው ወንዶችና ሴቶች ተሞክሯቸውን የሚያጋሩባቸውና ሌሎች ከቁማር ችግሮች እንዲላቀቁ እገዛ የሚያደርጉበት መድረክ ነው።

ይሁንና አደም ሁሉም ሰው ከቁማር ሱስ የመላቀቂያ ብልሃት የመፈለጊያ መንገድ እንዳለው ያምናል።
[የተወሰኑ] ሰዎች በየሳምንቱ ወደ ምክር አገልግሎት በመሔድ፣ ሥራዎችን በመለወጥ፣ የሕይወት ፕሮግራሞቻቸውን በመቀየር ወይም ተጨማሪ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ስኬታማ ሆነዋል። ለሰዎች ሊሠሩ [የሚችሉ] የተለያዩ ነገሮች አሉ።
አደም* ከቁማር ሱስ የተላቀቀ
support group.jpg
Podpora typu “rovný s rovným” a online fóra môžu byť pre mnohých užitočné Credit: Getty Images/Marco VDM
ፕሮፌሰር ጌይንስባሪ ተገቢ የሆነ ድጋፍ እስከሆነ ድረስ ማንኛውም የድጋፍ መንገድ አጋዥ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ።

የቁማር ሱስንም ከአውሮፕላን ድንገተኛ አደጋ ሁኔታ ጋር ያመሳስሉታል፤ መንገደኞች ሌሎችን ከመርዳታቸው በፊት የኦክስጂን ጭምብላቸውን እንዲያጠልቁ ከሚቸራቸው ምክር ጋር።
ሰዎች ብቻቸውን እንዳልሆኑና ለእነሱ የሚሆኑ በርካታ እርዳታዎች እንዳሉ ልብ መሰኘታቸው ጠቃሚ ነው... [እናም] በቅድሚያ የኦክስጂን ጭምብልዎን ያጥልቁ የሚለውን አባባል አይዘንጉ።
ፕሮፌሰር ጌይንስባሪ
Doctor with patient.jpg
Some people feel more comfortable asking their doctor to direct them to a specialised service. Credit: Getty Images/nahsoon
በክፍለ አገር ደረጃ ያሉ አገልግሎት ሰጪዎች መጠቀሚያዎችንና የምክር አገሎቶችን በስልክ፣ በኦንላይን ወይም በአካል ይቸራሉ።

የኒው ሳውዝ ዌይልስ መንግሥት በቁማር ሱስ የተጠመዱና እርዳታንም እንደምን ማግኘት እንደሚችሉ እርግጠኞች ላልሆኑ ዝንቅ ማኅበረሰባት ላይ ያተኮረ ዘመቻ እያካሔደ ነው።

ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ማንኛውም እርዳታን የሚሻ ግለሰብ ወደ በ 1800 858 858 መደወል ይችላል። ድረ ገፃቸው አረብኛ፣ ቀላልና አዘቦታዊ ቻይንኛ፣ ሂንዲ፣ የኮሪያና ቬትናም ቋንቋዎችን ጨምሮ በአምስት ቋንቋዎች ተተርጉሞ ይገኛል።

እንዲሁም፤ የገንዘብ ምክር አገልግሎትም አለ።

በዘመድዎ የቁማር ሱስ ሳቢያ ዕዳዎ ተከመችቶ ያለ ከሆነ ወይም ሌላ የገንዘብ ጉዳዮች ካሉ የገንዘብ ምክር አገልግሎት መጠየቅ እንደሚችሉ ወ/ሮ ራይት ምክረ ሃሳባቸውን ይቸራሉ።
በርካታ ሰዎች መደበኛ ያልሆነ ድጋፍን ይፈልጋሉ። ያም፣ የጤና ሠራተኛ፣ ወይም እንደ ማኅበረሰብ መሪዎች ወይም የሃይማኖት መሪዎችን ድጋፍ ወይም ቤተሰባዊ እርዳታዎችን የመሳሰሉ።
ፕሮፌሰር ጌይንስባሪ
ወ/ሮ ራይት “በመላ ክፍለ አገሩ ከ50 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የምክር አገልግሎቶች ይገኛሉ” ይላሉ።

በመጨረሻም፤ የቁማር ሱስ ያለበት ሰው አጋዥ መሆን፤ ፕሮፌሽናል እርዳታ እንዲያገኝ ከማበረታታት ጋር እጀ ለእጅ አብሮ የሚሄድ እንደሆነም አመላከተዋል።

*እውነተኛ ስሙ አይደለም።

እርዳታ ለማግኘት ይደውሉ ወይም ከታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤


Share
Published 17 August 2022 12:20am
By Zoe Thomaidou, Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS


Share this with family and friends