አንኳሮች
- ወደ አገራችን እንኳን በሰላም መጣችሁ የሚለው ስነስርአት እና ለአገሪቱ እውቅናን ለመስጠት የሚደረገው የተለያየ ነው።
- እንኳን በሰላም ወደ አገራችን መጣችሁ የሚለውን የሚፈጽሙት ከተወሰነ ስፍራ የመጡ የአገሪቱ ልማዳዊ ባለቤቶች ብቻ ናቸው።
- በራስዎ ድምጽ እውቅናን መስጠትን እንዲችሉ የተዘጋጁ የተለያዪ መረጃዎች
ወደ አገራችን እንኳን በሰላም መጣችሁ የሚለው መልእክት ዝግጅቱ ከመጀመሩ በፊት በንግግር ፤ በጭፈራ ወይም ጭስን በማጨስ ስነስርአት ሊከናወን ይችላል ። የእንኳን በሰላም መጣችሁ ስነስርአት የሚከናወነውም በአገሪቱ ልማዳዊ ባለቤቶች፤ ሁነቱ በሚከናወንበት ስፍራ ነው ።
እንኳን በሰላም መጣችህ ማለት ምን ማለት ነው ?
እንኳን በሰላም ወደ አገራችን መጣችሁ ማለት ፤ መንፈሳዊ ደህንነትን ማረጋገጥ ማለት ነው የሚሉት በካንብራ ክልል የንጉናዋል አረጋዊ የሆኑት ጁድ ባርሎው ናቸው ።
“ እንኳን በሰላም መጣችሁ ማለት ከቅድመ አያቶቻችን መንፈስ ጋር በመነጋገር እነዚህ ሰዎች ወደአገራችን እንዲገቡ ይፈቀድላቸው ማለት ነው። ለዚህች አገር ክፉ ነገርን እንደማያደርጉ እናምናለን ስለሆነም አትጉዷቸው ማለት ነው ” ይላሉ ።
“ እኔ ወደ ሌሎች ቀደምት ህዝቦች አገር ስሄድ ፤ እንኳን ደህና መጣሽ የሚለው ስርአት እንዲደረግልኝ እጠብቃለሁ፤ በዚህም እኔ እዚያ በመገኘቴ መንፈሳቸው መስማማቱን ማወቅ ይኖርብኛል፤ ምክንያቱም አሁንም ድረስ ከእኛ ጋር ናቸው - እነሱ በእንስሳቱ እና ዛፎቹ ውስጥ አሉ ። ”
አገር ምንድን ነው ?
“ አገር ” የሚለው ቃል የወሰኑ እና የተወሳስቡ ሀሳቦችን የሚወክል ነው። መሬትን ፤ የውሀ መተላለፊያዎችን እና ሰማይን የሚወክል ነው ፤ ግን ደግሞ የህይወትን እና ቤተሰብን ትስስር ሀሳብ በውስጡ የያ ነው ይላሉ ጁድ ባርሎው ።
“ በአገሪቱ ላይ ስኖር የሚሰማኝ ሀይል አለ ፤ እዛ በማልኖር ጊዜ አንድ ነገር ከህይወቴ እንደጠፋ ይሰማኛል ። በተጨማሪም ከአያት ቅድመ አያቶቼ ጋር የሚያገናኘኝ ነው ፤ ምክንያቱም የአቦርጂናል ህዝብ የቃል ታሪክ ያላቸው ሲሆን እነዚህን ታሪኮች አቅፋ የያዘችውም አገሪቱ ናትና ።”
ማንኛውም ሰው ወደ አገራችን እንኳን በሰላም መጣችሁ ማለት ይችላልን ?
ወደ አገራችን እንኳን በሰላም መጣችሁ ማለት የሚችሉት እርስዎ በተገኙበት ስፍራ ያሉት የአገሪቱ ልማዳዊ ባለቤቶች ብቻ ናቸው ።
በአብዛኛውም ለአንድ የተለየ አካባቢ በይፋ እውቅና የተሰጣቸው ልማዳዊ ባለቤቶቹ ናቸው የሚሉን ፖል ፓቶን ናቸው ። እሳቸውም የጉናይ እና ማኖራ ሰው ሲሆኑ የደቡብ ምስራቅ አውስትራሊያ የቪክቶሪያ ፌዴሬሽን ባህላዊ ባለቤቶች ኮርፖሬሽን መሪ ናቸው ።

Welcome to Country performed at Big Bash League, Perth Source: Paul Kane/Getty Images
“ ልማዳዊ ባለቤቶች ከተለየ ቦታ ወይም አገር ጋር ትስስር አላቸው ፤ ሁላችንም ለዚያ ለተለየ ቦታ ወይም ባህላዊ ስፍራ እና በሺዎች ከሚቆጠሩ ትውልዶች ጋር ጸንቶ ለቆየውን ትስስር ከበሬታን መስጠት በጣም አስፈላጊ ነው። ” ብለዋል
በተወሰኑት የአውስትራሊያ ግዛቶች ባህላዊ ባለቤቶች በጉልህ የሚታወቁ ሲሆን ፤በአንጻሩም በይፋ እውቅናን ያልተሰጣቸው ባህላዊ ባለቤቶችን ፤ ለመለየት የተወሰነ ምርመር ማድረግ ግድ ይላል ።
የመንግስት ድርጅቶች እና የአካባቢ ቀበሌዎች ከልማዳዊ ባለቤቶች ጋር ሊያገናኝዎት ይችላሉ ። በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የአቦርጅናል መሬት ካውንስል ወይም የአቦርጅናል የጤና ድርጅት እንዲሁ ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲያመሩ አቅጣጫን ያመላክትዎታል ።
ለአገሪቱ “ እውቅናን መስጠት ” የተለየ ነውን?

Welcome to Country performed before Super Netball, Melbourne 2022 Source: AAP Image/James Ross
ለአገሪቱ እውቅናን የመስጠት ስርአት አንድ ስብሰባ ወይም የተለይ ዝግጅት ከመጀመሩ በፊት የሚደረግ የአክብሮት ስነስርአት ነው ።ልዪነቱም ይህ ስነስርአት በአገሪቱ ልማዳዊ ባለቤቶች አማካኝነት የሚደረግ አለመሆኑ ነው።
“ ለአገሪቱ እውቅናን መስጠት ሁላችንም ልናደርገው እንችላለን ፤ ጥቁር ወይም ነጭ ከየትም ብንመጣ፣ ” ያሉት የኤስ ቢ ኤስ የነባር ዜጎች ሽማግሌ የሆኑት ርሆንዳ ሮበርትስ ናቸው።
“ስለዚህ እውቅናን መስጠት ማለት ስራዎትን እየሰሩበት ወይም እየኖሩበት ያለው ስፍራ እርስዎ የመጡበት ስፍራ አይደለም ማለት ነው ፤ ባይሆንም ምንም ማለት አይደለም ። ምክንያቱም እዚያ መኖርን ይችላሉ ፤ ለልማዳዊ ባለቤቶችም እውቅናን መስጠት ይችላሉ። ”
የእውቅናን ስነስርአትን ማዘጋጀት
የእውቅና ስነስርአትን በተመለከት የተወሰነ ቃል የለም ፤ ቁልፍ መርሆቹ በጽኑ መነሳሳት እና ከልብ የሆነ ፍላጎት ናቸው ። ስለሆነም ተዘጋጅቶ የተቀመጡ አባባሎችን ከመናገር ይልቅ ከልብ አፍልቆ ለመናገር የሚያስችልን እድልን ይፈጥራል ።
የእውቅናን ስነስርአትን ለማዘጋጀት እንዲረዳዎት በኦንላይን ላይ የተቀመጡ መረጃዎች አሉ።
“ ይህንን በመጨረሻ ሰአት ላይ በጥድፊያ አያድርጉት ፤ የአጠቃልይ ዝግጅቱ አካል እንደመሆኑ መጠን በደንብ ያቅዱ ” የሚሉት ጁድ ባርሎው ናቸው ።
“ ይህ የአክብሮት ምልክት ነው ”
የምትገናኙበትን ቦታ አገር እና ስም በተመለከት የተለየ ትኩረት ይስጡ ።

Acknowledgement of Country given by Aunty Yvonne Weldon during the First Nations Fashion + Design show, Sydney 2022 Source: Stefan Gosatti/Getty Images
የልማዳዊ ባለቤቶቹ በይፋ እውቅና ከተሰጣቸው ፤ ስማቸውን ይጥሩ ፤እንዲሁም ለቀደምት አረጋውያን ለአሁን እና ወደፊት ለሚመጡት ከበሬታን ይስጡ ።
የልማዳዊ ባላቤቶቹ በግልጽ የማይታወቁ ወይም በርካታ ቡድኖች ከሆኑ እና ፤ ለአንድ የተወሰነ የአገሪቱ ክፍል ፍላጎትን ካሳዩ‘ ለልማዳዊ ባለቤቶች ’እውቅናን መስጠት ብልህነት ነው፤ ሲሉ ፖል ፓቶን ተናግረዋል ።