ድምፅ ለፓርላማ፤ በምርጫ ጣቢያዎች ሊከውኗቸውና የሚችሉና የማይችሏቸው

ቅዳሜ ኦክቶበር 14 / ጥቅምት 3 በሚካሔደው ሕዝበ ውሳኔ የድምፅ አሰጣጥ ወቅት መራጮች ሊያስወግዷቸው የሚገቡ መልዕክት አስተላላፊ ልብሶችን አስመልክቶ የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን ደንቦችን ዘርግቷል።

gettyimages-1721857231-612x612.jpg

PERTH, AUSTRALIA - OCTOBER 7: 'Vote NO' campaign signage is seen outside a polling centre on October 07, 2023 in Perth, Australia. A referendum for Australians to decide on an indigenous voice to parliament will be held on October 14, 2023 and compels all Australians to vote by law. Early voting began on Oct. 2, with voting getting underway in all states. (Photo by Matt Jelonek/Getty Images) Credit: Matt Jelonek/Getty Images

አውስትራሊያ ውስጥ በድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ወይም ከመግቢያው ስድስት ሜትሮች ርቀት ላይ የምርጫ ቅስቀሳን የሚያግድ የቆየ ድንጋጌ አለ።

የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን መራጮች በድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶችን የሚያንፀባርቁ ካናቴራዎችን ከመልበስና ደረት ላይ ተለጣፊ ምልክቶችን ሰክቶ ከመገኘት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

በታካይነትም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ቶም ሮጀርስ መራጮች እርስ በእርሳቸው መልካም ሥነ ምግባርን በተላበሰ ሁኔታ እንዲተያዩ ጠይቀዋል።

ከወዲሁ ከቅዳሜው የሕዝበ ምርጫ ቀን ቀደም ብለው አራት ሚሊየን መራጮች ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማን አስመልክተው ተጨማሪ መረጃ ካሹ SBS አማርኛን ይከታተሉ። በተለይ በነባር ዜጎች ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረውን የ SBS NITV ይመልከቱ፤ እንዲሁም እና ድረ ገፆችን ይጎብኙ።

 


Share
Published 12 October 2023 7:42pm
By Deborah Groarke, Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends