ከመደወልዎ በፊት ያስቡ ፡ ህብረተሰቡ የሶስት ዜሮ ቁጥሮችን ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ እንዲጠቀም ፖሊስ ጥሪውን አቀረበ

የሶስት ዜሮ ቁጥሮችን (000) ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ እንዲጠቀሙ ፖሊስ ለአውስትራሊያ ማህበረሰብ ጥሪውን አቀረበ ።

TOWNSVILLE, AUSTRALIA - JUNE 07: A policeman is seen on his phone at the scene of the car accident on June 07, 2020 in Townsville, Australia.

A policeman is seen on his phone at the scene of the car accident in Townsville, Australia. Source: Ian Hitchcock/Getty Images

አንኳሮች ፦

  • የሶስት ዜሮ ቁጥሮችን (000) የሚደውሉት፤ ጉዳዩ ለህይወት የሚያሰጋ ወይም አስቸጋሪና ድንገተኛ ከሆነ ብቻ ነው።
  • አስቸኳይ ላልሆኑ ሁኔታዎች ፓሊስን ለማግኘት፤ በተመለከት የፖሊስ የእርዳታ መስመርን በ (131 444) ይደውሉ።
  • በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ ያሉ ጠቋሚዎች እርዳታን በሚጠይቁ ጊዜ ያሉበትን አቅጣጫ በፍጥነት እና በትክክል ያመላክታሉ ።
በአውስትራሊያ የሶስት ዜሮ ቁጥሮች (000) አገልግሎታቸው ለአገር አቀፋዊ የድንገተኛ ጊዜ አገልግሎት ሲሆን ፤ ለአምቡላንሰ ፤ እሳት አደጋ ወይም ለህይወት የሚያሰጋ እንዲሁም አስቸጋሪ ድንገተኛ ሁኔታ ላይ ሲሆኑና  የፖሊስ እርዳታን ሲፈልጉ መደወል ይችላሉ ።

ከ 2019-2020 በቀን ውስጥ 7600  የስልክ ጥሪዎችን የሶስት ዜሮ ቁጥሮችን  አስተናግዷል፤ ይህም ማለት አንድ የስልክ ጥሪ በየ 11 ሰከንድ ማለት እንደሆነ ከድንገተኛ ጊዜ የስልክ ባልስልጣን የተገኘ መረጃ ያሳያል ።

ሲኒየር ሰርጀንት ክሪስቲ ዋልተር የኒው ሳውዝ ፖሊስ ሊንክ ዳይሬክተር እንዳሉት ሰዎች ወደ ሶስት ዜሮ ቁጥሮች የሚደረገውን የስልክ ጥሪ መጠን ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ በመደወል መቀነስ ይችላሉ ።

“ አንድ ሰው ድንገተኛ ላልሆን ጉዳይ ደውሎ መልስ ስንሰጥ ፤ ድንገተኛ የሆኑ ጥሪዎችን ለሚጠብቁ ሰዎች  በተፈለገው ፍጥነት ልንመልሳቸው አንችልም” በማለት አጽናኦት ሰጥተዋል ።

መቼ የሶስት ዜሮ ቁጥሮችን ለፖሊስ እንደውል ?

ሲኒየር ሰርጀንት ዋልተር እንደሚሉት ወደ ሶስት ዜሮ ቁጥሮች  መደወል ያለብዎ እርስዎ ወይም ሌላ ሰው አፋጣኝ በሆነ አደጋ ውስጥ ሲሆኑ ነው ።

“ የሶስት ዜሮ ቁጥሮችን  መደወል የሚኖርብዎት የወንጀል አደጋ እየተከናወነ ከሆነ ወይም ወንጀል መፈጸሙን ወዲያውኑ ከተመለከቱ እና ፓሊስ ችግር ፈጣሪውን የመያዝ እድል ካለው ፤ ከሁሉ በበለጠ እርስዎ ወይም ሌላ ሰው ከፖሊስ አፋጣኝ እርዳታን የሚፈለጉ ከሆነ ነው። ”

የፖሊስ የእርዳታ መስመር

ተጠባባቂ ሰርጀንት ካቲ ፊሽ ከፖሊስ የእርዳት መስመር ቪክቶርያ እንደሚሉት ፤ አነስተኛ የሆኑ ወንጀሎች አጣዳፊ ያልሆኑ ሁኔታዎች ለምሳሌ እንደ ቤት ሰብሮ ዘረፋ ፤ ሌብነት ፤ የእቃ መጥፋት ወይም አነስተኛ የሆነ የንብረት መውደም ከተከሰተ በ131 444 ለፖሊስ የእርዳታ መስመርን ይደውሉ ።
Police Assistance Line (131 444) is available nationwide 24 hours a day, seven days a week.
Police Assistance Line (131 444) is available nationwide 24 hours a day, seven days a week. Source: Victoria Police
“ በባቡር ወስጥ ሳሉ ወይም ከሆነ ቦታ ወደ ቤትዎ ሲመለሱ ንብረት ከጠፋብዎ ፤ ሌላ ነገር ከተሰረቀብዎ ለምሳሌ ብስክሌት ወይም መኪና ፤ የመኪናዎ ታርጋ ፤ ወይም ማንኛውም ነገር ከተሰረቀብዎ ወይም እርስዎ ከቤትዎ ሳይኖሩ የሆነ ሰው ቤትዎን ሰብሮ ከገባ፤ ይህንን በ131 444 በመደወል ማሳወቅ አለብዎ ።

የአደንዛዥ እጽ እና መጠጥን የመሳሰሉ ነገሮች ለሌሉብት እንዲሁም ማንም ሰው ላልተጎዳበት አነስተኛ ለሆነ የመኪና አደጋ  እና በአጠቃላይ ለእንደዚህ አይነት ነገሮች ፖሊስ መገኘት አይኖርበትም ። ከሌላኛው አሽከርካሪ ጋር አድራሻን በመለዋውጥ ጉዳዩን ከኢንሹራንስ ካምፓኒዎች ጋር መጨረስ ይቻላል ፤” የሚሉት ሲኒየር ሰርጀንት ዋልተር ናቸው ።
There is no requirement to report a minor car collision to the police.
There is no requirement to report a minor car collision to the police. Source: Getty Images/Guido Mieth
ነገር ግን በመኪና አደጋው አንድ ሰው ከተጎዳ ወይም መኪኖች መንገድን ከዘጉ የሶስት ዜሮ ቁጥሮችን (000) በአስቸኳይ መደወል ያስፈልጋል ።
A white SUV (far L) sits in the middle of the road as police and emergency personnel work at the scene of where a car ran over pedestrians in Flinders Street in Melbourne on December 21, 2017.
Police and emergency personnel work at the scene of where a car ran over pedestrians in Flinders Street in Melbourne Source: MARK PETERSON/AFP via Getty Images
ተጠባባቂ ሰርጀንት ፊሽ አጽንኦት ሲሰጡ ማንኛውም ሰው የአመጻ ባህሪ ባለው የትዳር አቻው ሳቢያ አፋጣኝ አደጋ ውስጥ ካለ የሶስት ዜሮ ቁጥሮችን (000) መደወል ያስፈልጋል ።

ከአየር ጠባይ ጋር በተያያዘ ለሚፈጠር አደጋ ፤ ለምሳሌ እንደ ጎርፍ ፤ አውሎነፋስ እና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ፤ በቤት እና ንብረት ላይ የመፍረስ አደጋ ከተከሰተ እና  ፤ ነገር ግን ሁኔታው የማንንም ህይወት በሚያሰጋ ሁኔታ ላይ ካልሆነ ፤ የሶስት ዜሮ ቁጥሮችን ከመደወል ይልቅ የከተማው የአደጋ ጊዜ አገልግሎት State Emergency Service (SES) መደወል ያስፈልጋል ።
For storm and flood assistance, call the State Emergency Service (SES).
For storm and flood assistance, call the State Emergency Service (SES). Source: Getty Images/doublediamondphoto
የአስተርጓሚዎች አገልግሎትም አለ

የሶስት ዜሮ ቁጥሮችን መስመር እና የፖሊስ እርዳታ መስመር ደዋዮች የእንግሊዝኛ ቋንቋን መናገር ካልቻሉ እና የሚናገሩትን ቋንቋ ለይተው ካሳወቁ ፤ ነጻ የአስተርጓሚ አገልግሎቶችንም እንዲሁ ይሰጣሉ ።

እንደ ሲኒየር ሰርጀንት ዋልተር አባባል ወደ ሶስት ዜሮ ቁጥሮች መስመር ሲደውሉ ሰዎች እንዲረጋጉ እና ትኩረት እንዲያደርጉ ነው።

“በተቻለ መጠን ሁሉ መረጋጋት እና ስልኩን የሚመልሱት ባለሙያዎች የሚጠይቁዎትን ጥያቄዎች ያዳመጡ ። ያሉበትን ቦታ ማወቅ ሌላው አስፈላጊ እና ከሚጠየቁጥ ጥያቄዎች አንዱ ነው ። ቦታውን የማየውቁ ከሆነ የ Emergency Plus app  መጫን እንዳለብዎ ማወቅ አለብዎ። ማፕን ወይም በአካባቢያችሁ ያሉትን መሳሪያዎችን መጠቀም አልያም ሌሎች ሰዎችን መጠየቅ አለብዎት ። ምክንያቱም የት እንዳሉ ካላወቅን ምላሻችንም ይዘገያል “
A man talks to police after he was rescued from his submerged car by State Emergency Service workers in Windsor NSW
A man talks to police after he was rescued from his submerged car by State Emergency Service workers in Windsor on July 04, 2022 in Sydney Australia Source: Jenny Evans/Getty Images
የተንቀሳቃሽ ስልኮች አፕ የት እንዳሉ ሊጠቁሙ ይችላሉ ።

 and   የተሻሻሉ የተንቀሳቃሽ አቅጣጫ ጠቋሚዎች በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ እንደ መሳሪያ የሚጠቁሙ እና በአውስትራሊያ መንግስትም የሚመከሩ ናቸው ። እነዚህም የሶስት ዜሮ ቁጥሮች (000) ደዋዮች በመላው አውስትራሊያ ያሉበትን አካባቢ በፍጥነት እና ትክክላኛ በሆነ መንገድ የሚጠቁሙ ናቸው።

 “ የሶስት ዜሮዎችን (000) ስልክን ለድንገተኛ ወይም አሁኑኑ ለተፈጠረ ሁኔታ ብቻ ብንጠቀም ህይወትን ለማትረፍ እንችላለል ። እርግጠኛ ካልሆኑ እና ጉዳዪ አስቸኳይ ካልሆነ  131 444 ይደውሉ ስልኩን የሚመልሱት ባለሙያዎች ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ይረዱዎታል ። ”
ለተጨማሪ መረጃ . ይጎብኙ

ለአስተርጓሚዎች አገልግሎት 131 450 ይደውሉ

ለቤት ውስጥ ጥቃት በተመለከት እርዳታን ለማግኘት 1800 RESPECT (1800 737 732 )


Share
Published 8 July 2022 12:37am
Updated 8 July 2022 12:59am
By Parisuth Sodsai
Presented by Martha Tsegaw


Share this with family and friends