ብሔራዊ ፓርክ ሲጎበኙ ሊያደርጓቸውና ላያደርጓቸው የሚገቡ

ስለ አውስትራሊያ ሲነሳ አብዝተው የሚኒሱት ከቤት ውጭ ያሉ እንቅስቃሴዎች ናቸው። ብሔራዊ ፓርክም ተፈጥሯዊ አካባቢያችንን ለመቃኘት አንዱ ማለፊያ መንገድ ነው። ከታላቁ ባሪየር ሪፍ ውስጥ ሰጥመው መውጣት ይሹ፣ ካንጋሩ ደሴት ተገኝተው የዱር አራዊት መመልከትን ይውደዱ ወይም ራስዎን ኡሉሩ ላይ ከነባር ዜጎች ባሕል ጋር ያዋድዱ፤ ሁሌም ራስዎንና የአካባቢ ተፈጥሮን መጠበቅ ጠቃሚ ነው።

پارک ملی کاکادو

Kakadu National Park Source: Wikimedia Commons/Dietmar Rabich/CC BY-SA 4.0

በመጀመሪያ መዳረሻዎን አስመልክተው የኦንላይን ዳሰሳ ያካሂዱ። 

ተነስተው ከማቅናትዎ በፊት፤ በመንግሥት የሚተዳደሩ ድረገጾችን በኦላይን ቃኝተው ዕቅድዎን ይንደፉ።

ያን ሲያደርጉ፤ ስለ አካባቢ ተፈጥሮ፣ በአካባቢው ስላሉ የተለያዩ ግልጋሎት ሰጪዎች፣ ክፍያዎች፣ እንቅስቃሴዎችና የአየር ጠባይ ሁኔታዎች መማር ይችላሉ።

ታሪካዊ ወይም የነባር ዜጎች የሆኑ ታይታዎችን አይንኩ ወይም በላያቸው ላይ አይረማመዱ።

ብሔራዊ ፓርኮች በአብዛኛው ያልተነኩ ተፈጥሯዊ አካባቢዎች ወይም ለአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ባሕላዊ ትርጓሜያቸው በጣሙን ጠቃሚ ሆነው ያሉባቸው አካባቢዎች ናቸው። 

በአካባቢው ያሉ ታይታዎች አለት ላይ የተቀረጸ ሥነ ሰዕልን፣ የመሰብሰቢያ ቦታዎችንና ክብረ በዓል ማካሔጃ ሥፍራዎችን ያካተቱ ባሕላዊ ፋይዳዎች ያሏቸው ሊሆኑ ይችላሉ። 

የአውስትራሊያ መንግሥት በአብዛኛው ከነባር የአካባቢው ባሕላዊ ባለቤቶች ጋር ሆኖ ስድስት ብሔራዊ ፓርኮችንና 13 የተከለሉ ጥብቅ ኃ ውስጥ ያሉ ሕይወቶችን ያስተዳድራል። 

 
Uluru-Kata Tjuta National Park
Uluru-Kata Tjuta National Park Source: Flickr/nosha/CC BY-SA 2.0

መክፈል ይኖርብኛል?

በርካታ ብሔራዊ ፓርኮች በመኪና የሚዘልቁ ከሆነ የመግቢያ ክፍያ ይጠይቃሉ፤ ሆኖም በእግር ወይም በብስክሌት የሚገቡ ከሆነ ግና ከክፍያ ነጻ ናቸው።

ብሔራዊ ፓርኮችን አዘውትረው የሚጎበኙ ከሆነ፤ የዕረፍት ጊዜያትን፣ አያሌ ቀናትን ወይም ዓመቱን ሙሉ የሚሽፍኑ ይለፎችን ከገዙ ወጪዎን ሊቆጥብልዎት ይችላል።

 በርካታ ስቴቶች ለተለያዩ ፓርኮች መጎብኛ የሚሆኑ ይለፎችን ይሸጣሉ፤ ይሁንና ለሌላ ስቴት ሊጠቀሙበት አይችሉም።

ደኅንነቴን ጠብቄ መቆየት የምችለው እንዴት ነው?

በርቀት ፈንጠር ብሎ ወዳለ ብሔራዊ ፓርክ መቆየት የሚሹ ከሆነ አስቀድመው ለሚመለከተ ሰው ማሳወቅ ይኖርብዎታል።

ወደዚያ በሚያመሩበትም ወቅት ምግብ፣ ውኃና ሙቀት ሰጪ ልብሶችን እንዲይዙ ይመከራል። ምልክት ከተደረገባቸው መጓጓዣ መንገዶች ውጪ አይሂዱ። ሁሌም የደኅንነት መጠበቂያ ከሆኑ አጥሮች አይለፉ።
Great Australian Bight
Great Australian Bight Source: Wikimedia Commons/Nachoman-au/CC BY-SA 3.0

የፀሐይ መከላከያ ይቀቡ - ተጠንቅቀው ይዋኙ

የፀሐይ መከላከያ ክሬምን የመቀባትና ተጠንቅቆ የመዋኘት መልዕክት በብሔራዊ ፓርኮች ጉብኝት ወቅትም ግብር ላይ የሚውል ነው። የፀሐይ መከላከያ ክሬም ይቀቡ፤ ባርኔጣም ያድረጉ።

ለመዋኘት ወስነው ወደ መዋኛ ሥፍራ ከሔዱ፤ ሁሌም ጥልቀቱን፣ የወቅቱን የሙቀት ደረጃ ይለኩ። በባሕር ዳርቻ ደንጊያዎች ላይ ሲራመዱ ይጠንቀቁ። እርግጥ ነው፤ ከቶውንም አዞዎች ወዳሉበት ውኃ አይቅረቡ።

ቆሻሻዎን ይዘው ይሂዱ

ብሔራዊ ፓርኮች በሰው እጆች ያልተገራ መልከ ምድር አቀማመጥ ያላቸው፣ ዝንቅ ተክሎችና እንሰሳዎች የሚገኙባቸውና አራት ፐርሰንት የአውስትራሊያን  ምድር አካልለው የያዙ ናቸው።

ቁሻሻዎችዎን እዚያ ጥሎ መሔድ የአካባቢ ተፈጥሮ ላይ ጉዳትን ያደርሳል። ስለሆነም፤ ምርጫዎ በሆነ ብሔራዊ ፓርክ በሽርሽርና BBQ ከተዝናኑ በኋላ ሁሉንም ቆሻሻዎችዎን ወደ ቤትዎ ይዘው ይሒዱ።

ለተጨማሪ መረጃ  ድረገጽን ይጎብኙ። 
Hyams Beach
Hyams Beach Source: Wikimedia Commons/Charliekay/CC BY-SA 4.0

More ተጨማሪ ጠቃሚ ሊንኮች፤

Northern Territory Parks and Wildlife Service: 

NSW National Parks and Wildlife Service: 

Queensland Department of National Parks, Recreation, Sports and Racing: 

National Parks South Australia: 

Western Australia Department of Parks and Wildlife: 

Tasmania Park and Wildlife Service: 


Share
Published 31 May 2020 8:05am
By Ildiko Dauda
Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends