ከእንግሊዝ አገር የተነሳውን እና በከፍተኛ ደርጃ ተላላፊ የሆነውን የኮቪድ19 ተከተሎ እያደገ የመጣውን ስጋት ተከተሎ የብሄራዊ ካቢኔው በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ በረራዎች ላይ የተወሰደውን አዲሱን እርምጃ ደግፏል ፡፡
በግሬት ብሪዝበን በኮመንዌልዝ ደረጃ የኮሮናቫይረስ የታየበት “ አደገኛ ስፍራ” በመባል ታውጇል ፡፡ በአንድ የጽዳት ሰራተኛ ላይ የኮሮናቫይረስ በመገኘቱ ይህንኑም ተከትሎ ከተማዋ ለሶስት ቀናት ሙሉ ለሙሉ ዝግ እንድትሆን ተደርጓል ፡፡
በአዲሱ ለውጥ መሰረትም ወደ አውስትራሊያ የሚመጡ ተጓዦች ሁሉ ከኮቪድ19 ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቅድመ ምርመራ ማድረግ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የተመላሾች ቁጥር ገደብም እንደገና በተግባር እንዲውል ተደርጓል ፡፡
ከእንግሊዝ አገር የሚመለሱ ተጓዦችም እንዲሁ የአዲሱን የኮሮናቫይረስ ፈጣን ምርመራ ማድረግ ግዴታ አለባቸው ፡፡
የፊት መሸፈኛ ጭንብል በአገር አቀፍ እና አለማቀፍ በረራዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ አየር መርፊያዎች ሁሉ የግድ መደረግ አለበት ፡፡እድሜያቸው ከ12 አመት በታች የሆኑትን ግዴታው አያጠቃልልም ፡፡ እንዲሁም በውጭ ሀገር በሚገኙ አየር ማረፊያዎችም ጭምር የፊት መሸፈኛዎችን ተጓዦች እንዲያደርጉ ይመከራል ፡፡
“ ይህ ቫይረስ የራሱን ህጎች መጻፉን ቀጥሏል ፤ ስለዚህ እኛም እንዲሁ በረራን በተመለከት የሚመጡ ለውጦችን ቶሎ መቀበል ይኖርብናል ” ሲሉ ሚስተር ሞሪሰን ተናግረዋል ፡፡
የምርመራ ቅድመ ሁኔታዎችን በተመለከተ የተወሰኑ ማስተካከያዎች ይኖራሉ ፡፡ ለምሳሌ በአነስተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑ እና የመመርመሪያ ቁሳቁስ እጥረት ካላቸው አገሮች የሚመጡ ጊዜያዊ ሰራተኞች ተጠቃሾች ሲሆኑ ፤ በአንጻሩ ለእነሱ ተብሎ የተለየ ምርመራ የሚደረግ ይሆናል ፡፡
በአለም አቀፍ በረራዎች በሚመጡት ተሳፋሪዎች ቁጥር ላይ እስከ ፌብሩዋሪ ድረስ የሚቆይ ገደብ እንደገና ተቀምጧል ፡፡
በዚህም መሰረት በአለም አቀፍ በረራዎች ወደ ኒው ሳውዝ ዌልስ ፤ ዌስተርን አውስትራሊያ እና ኩዊንስላንድ የሚመጡት ተሳፋሪዎች ቁጥር በ50 በመቶ እንዲቀንስ ሆኗል ፡፡
በተሻሻለው የተሳፋሪዎች ቁጥር መጠን መሰረም ወደ ኒውሳዝ ዌልስ ተመላሾች በሳምንት ወደ 1505 ዝቅ ያለ ሲሆን ፤ ዌስተርን አውስትራሊያ በሳምንት 512 እንዲሁም ኩዊንስላንድ በሳምንት 500 እንዲሆን ተወስኗል፡፡
ቪክቶሪያ በአሁን ሰአት ያላትን በሳምንት የ 490 ተመላሾች ቁጥር ይዛ የምትቆይ ሲሆን ይህ ቁጥር የሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከታየበት ጊዜ ጀምሮ በተግባር የዋለ ነው ፡፡
የብሄራዊ ካቢኔው ባለፈው አርብ ከክልል እና ግዛት መሪዎች ጋር ባደረገው ስብሳባ ያስተላለፈው ውሳኔ እስከ ፌብሩዋሪ 15 ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል ፡፡
ሚስተር ሞሪሰን አያይዘውም ከአውስትራሊያ ውጭ ያሉ እና ለመመለስ ከተመዘገቡት 80 በመቶ የሚሆኑት አውስትራሊያውያን የሚገኙት አዲሱ ቫይረስ እንድታየ በታረጋገጠባቸው አገራት ነው፡፡
“ አዲሱን ውጥረት በተመለከተ በርካታ ያልታወቁ እና እርግጠኛ ያልሆንባቸው ነገሮች አሉ ፡፡ ለዚህ ነው ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድን የምንከተለው ፤ ይህ አካሄድ ስሜት እንደሚሰጥም እናምናለን ፡” ብለዋል ፡፡
የህክምና ዋና አማካሪ የሆኑት ፖል ኬሊ እንዳሉት “ ጠንካራ እና ፈጣን ምላሽ መስጠትን አላማ ያደርገ ሲሆን ይህም የመተላለፍ አቅሙ ከፍተኛ የሆነውን ቫይረስ ለመግታት የሚል አላማን የያዘ ነው ፡፡
“ ዋናው አላማችን የአውስትራሊያውያንን ደህንነት መጠበቅ ፤ እንዲሁም አዲሱ ቫይረስ በአውስትራሊያ እንዳይተላለፍ ማድረግ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
“ ምክንያቱም ለመቆጣጠር እጅግ በጣም አዳጋች ነው የሚሆነው ፡፡”
በለይቶ ማቆያ ስፍራ የሚሰሩ ሰራተኞች ሁሉ ከአሁን ጀምሮ በየቀኑ ምርመራን ያደርጋሉ ፡፡
በአለም አቀፍ በረራዎች ላይ የሚስሩ ሰራተኞች በየሰባት ቀኑ የኮቪድ19 ምርመራን ያደርጋሉ ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በየበረራቸው መካከልም በለይቶ ማቆያ ስፍራዎች እንዲቆዩ ይደርጋል ፡፡
በአሁን ሰአት ከ38000 የሚሆኑ አውስትራሊያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ንግድ ዲፓርትመንት በኩል ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ፡፡