ለፕላኔታችን የበኩልዎን ሚና ይጫወቱ ፡ በአውስትራሊያ እንደገና መጠቀም የምንችላቸውን ቁሳቁሶች በትክክል እንጠቀም

Recycling in Australia

Are we good recyclers? Source: Getty Images/Jessie Casson

Recycling in Australia
Your recyclables should not be bagged when placing them into the kerbside recycling bin. Source: Getty Images/RUBEN BONILLA GONZALO
አውስትራሊያውያን በአመት 74 ሚሊዮን ቶን ቆሻሻን የሚያስወግዱ ሲሆን ከዚህ ውስጥም ለእንደገና ጥቅም የሚውለው 60% ያህሉ ብቻ ነው። ጥናቶች እንደሚያመላክቱትም ከሆነ እንደገና በአገልግሎት ላይ ሊውሉ በሚችሉ የተጣሉ ቁሳቁሶች ዙሪያ ያለው የእውቀት ማነስ እና በግልጽ አለመረዳት ፤  የሚደረጉትን ጥረቶች ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርግጓቸዋል ።

እንደገና ይጠቀማሉ ? አብዛኛዎቻችን ለዚህ ጥያቄ መልሳችን አዎን ሊሆን ይችላል። ይሁን እና ዋናው አሳሳቢው ነገር በትክክል እናደርገዋለን ወይስ አናደርገውም የሚለው ነው ።

ቁልፍ ነጥቦች

  •  የትኛው ሂደት ነው ለብክለት ዋና አስተዋጻኦ የሚያደርገው
  • እንደገና ለጥቅም የሚውሉ ነገሮችን እንደ ሃብት ይቁጠሩ
  • ለተሻለ ነገ እንደገና ለአዲስ አላማ ይጠቀሙ
“ 89% የምንሆነው ጠቃሚ እንደሆነ እናውቃለን ፤ ነገር ግን ነገሮን በትክክለኛው መንገድ እንደገና መጠቀም የምንችለው ከሶስት ሰዎች ውስጥ አንዳችን ብቻ ።”

ጥናቶች እንደሚያሳዩትም በርካታ ሰዎች ቁሳቁሶችን እንደገና ለጥቅም እንዲውሉ በሚቀመጥበት ቦታ ያስቀምጣሉ ምንም እንኳ ቁሳቁሶቹ እንደገና ለጥቅም መዋላቸውን እርግጠኛ ባይሆኑም ።

እንደ ወረቀት፤ የጓዳ ማጽጃ ወረቀቶች ፤ጨርቃ ጨርቅ እና ናፒ ያሉት በውስጡ ያሉትን በሙሉ ሊበክሉ እና ችግርን ሊፈጥሩ ይችላሉ የሚሉን ሚስ ኬርናን ናቸው።

ባትሪዎች እና ኤሌክትሮኒክስ እንደገና ለጥቅም የሚውሉ እቃዎች ማጠራቀሚያ ውስጥ ሲከተቱ ችግርን ይፈጥራሉ ፤ ስለዚህ ለነሱ በተለየ እና እንደገና ለጥቅም የሚውሉበት ስፍራ መቀመጥ አለባቸው።

እንደገና ለጥቅም የሚውሉ ቁሳቁሶች ጠቃሚ ሀብቶች ናቸው

የትኞቹ እንደገና ለጥቅም መዋል ይችላሉ የሚለውን ለማወቅ የአካባቢያችሁን የቀበሌ መመሪያ መመልከት ያስፈልጋል ።በኦንላይን የሚገኙ መመሪያዎች ለምሳሌ ,  በአካባቢያችህ ስላለው የቆሻሻ ማስወገድ ሂደት በግልጽ ያስረዳሉ ።
“ እነዚህ ቁሳቁሶ ንጹህ እና ደረቅ መሆን አለባቸው ፤ በውጤቱም አዲስ ህይወትን ሊያገኙ ይችላሉ ”

ሰፋፊ ጠርሙሶች ባዶ መሆን እና መታጠብ አለባቸው ፤እንዲሁም የብረት ክዳን ካላቸው ማንሳት ያስፈልጋል ፤ በአንጻሩ በዘይት የተነካካ የፒዛ ካርቶን መወገድ ያለበት አጠቃላይ ቆሻሻ በሚጣልበት ማጠራቀሚያ ነው ።

እንደገና በጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ቁሳቁሶችን በተመለከተ ምን መደረግ እና አለመደረግ አለበትን የሚለውን ግልጽ ህግ መከተል ይጠቅማል ይላሉ ሚስ ኪርና

አውስትራልኤሽያን  እንደገና በጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ቁሳቁሶች ምልክት

የአውስትራልኤሽያን እንደገና በጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ቁሳቁሶሽ ምልክት  አብዛኛዎች ምልክቶች በእሽጎች ላይ ለተጠቃሚዎች የሚገለጹ ሲሆን ፤ የትኛውን እንደገና መጠቀም ይቻላል ወይም አይቻልም የሚለውን መመሪያ ይሰጣል።ይህ የተለያዩ ክፍሎችን ለያይቶ ማሳየትንም ሊያጠቃልል ይችላል ። ለምሳሌ ክዳን ፤ ማሸጊያ የፕላስቲክ መያዣዎችን መጥቀስ ይቻላል ።
Australian Recycling Label
Australian Recycling Label (ARL) Source: Clean Up Australia
እንደገና ጥቅም ላይ የሚውሉ ነገሮችን በተወሰነ ስፍራ ማስቀመጥ

ለስላሳ ፕላስቲኮችን ቀበሌዎ በሚያስመጠቀምጠው እና  እንደገና በጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ቁሳቁሶች መጣያ ውስጥ መጣል አይቻልም ።እነዚህም ለብቻቸው እንደገና ለጥቅም ሊውሉ ስለሚችሉ ተለይቶ በተቀመጠላቸው ስፍራ ማስቀመጥ ያስፈልጋል ።

“አራት ሚሊዮን የሚሆኑ ለስላሳ ፕላስቲኮች በቀዩ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ በየቀኑ ይጣላሉ”

“ በአገር አቀፍ ደረጃ በአማካኝ አራት ግራም ፤ ማለትም 16,000 ኪሎግራም ላስላሳ ፕላስቲኮች በየቀኑ ወደመሬት ከመጣላቸው በፊት ወደሌላ እንዲቀየሩ ማድረግ ነው። “ ብለዋል ሚስ ግሊጎርን

ከዳቦ መጠቅለያ ላስቲክ ጀምሮ እስክ ዚፕ ያላቸው ላስቲኮች ፤ መጠቅለያዎች  እንዲሁም ሌሎቹም እንዴት ወደ ጥቅም እንደሚውሉ ቢያውቁ ይገረማሉ።

ነገር ግን ከነዚህ በተለየ ሁኔታ የሚታዩ ስላሉ የARL.   ድረ ገጽማየት የትኞቹ ነገሮችን እንደገና መጠቀም ይቻላል የሚለውን በግልጽ ለማወቅ ያስችላል።
Secondhand economy
Reusing and repurposing, the way of the future Source: Getty Images/Su Arslanoglu
[yet]


Share
Published 15 July 2022 12:34am
Updated 15 July 2022 12:37am
By Yumi Oba
Presented by Martha Tsegaw


Share this with family and friends