አውስትራሊያውያን 2021 አመትን በተለመደው አይነት የአዲስ አመት ዋዜማ ለማክበር ቢዘጋጁም የኮሮናቫይረስ ወጥመድ ተጨማሪ ክልከላዎች እንዲኖሩ አድርጓል ፡፡
በኒውሳውዝ ዌልስ የተያዦች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ፤ የቫይረሱ ምልክት የተታየባቸው ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ክሊኖኮች በመሄድ መርመራን እንዲያደርጉ ባለስልጣናቱ ግፊትን እያደረጉ ነው፡፡
የምርመራ ክሊኒኮቹ የፈርንጆቹን አዲስ አመት ቀን ጨምሮ በሁሉም የእረፍት ቀናት ክፍት የሚሆኑ ናቸው ፡፡በመላው ኒውሳውዝ ዌልስ ከ350 በላይ የኮቪድ-19 የመመርመሪያ ቦታዎች ሲኖሩ ፤ አብዛኛዎቹ በሳምንት ሰባቱንም ቀናት ክፍት ናቸው ፡፡በአቅራቢያዎ ያለውን ክሊኒክ በተመለከተ ይጎብኙ፡፡አልያም የቤተሰብ ሀኪምዎን ያነጋገሩ ፡፡
በአዲስ አመት ዋዜማ በአገር አቀፍ ደርጃ አካላዊ ርቀትን በተመለከተ ማድረግ የሚችሉትን እና የማይችሉትን ነገሮች የሚወስኑት ህጎች እነሆ
ሰሜናዊ የባህር ዳርቻ ( Northern Beaches area)
በሲድኒ ሰሜናዊ የባህር ዳርቻ ( Northern Beaches area) ቫይረሱ በስፋት በታየበት ማእከል ጠንካራ የሆኑ የኮሮናቫይረስ ገደቦች ተጥለዋል፡፡
በሰሜን ዞን እና ሰሜናዊ የባህር ዳርቻ ( Northern Beaches area) የሚኖሩ ሁሉ ቢያንስ እስከ ጃንዋሪ 9 ድረስ ጥብቅ በሆነ ክልከላ ውስጥ የሚቆዩ ሲሆን ፤ የአዲስ አመት ዋዜማን ምክንያት በማድረግ ለነዋሪዎች መጠነኛ የሆነ የገደብ መላላት የተደረገ በአቅራቢያቸው የሚኖሩ ሰዎች ህጻናትን ጨምሮ እስከ 5 ያህል እንግዶችን በመኖሪያ ቤታቸው ማስተናገድ ይችላሉ ፡፡
ከዲሴምበር 31, 2020 ከሰአት በኋላ 4፡00 ጀምሮ እስከ አርብ ጃንዋሪ 1,2021 ድረስ ሰሜናዊ የባህር ዳርቻ ( Northern Beaches area) ፔኒሱላ ዞን የሚኖሩ ሁሉ የሚከተሉት ክልከላዎች ተደርጎባቸዋል ፦
በአካባቢዎ ካሉት ሰዎች ( ህጻናትን ጨምሮ ) እስከ 5 ሰዎችን በቤትዎ ማስተናገድ ይችላሉ
ከቤት ውጭ ባሉ እንቅስቃሴዎች ( ህጻናትን ጨምሮ ) እስከ 5 ያህል ሰዎች መገኘት ይችላሉ ፡፡ — NSW Health (@NSWHealth) December 29, 2020
በሰሜናዊው የባህር ዳርቻ ደቡብ ዞን የሚኖሩ ነዋሪዎች ከሚኖሩበት ተመሳሳይ ዞን በመኖሪያ ቤታቸው ህጻናትን ጨምሮ እስከ 5 ያህል ሰዎችን ማስተናገድ የተፈቀደ ነው ፡፡
ሰሜናዊ የባህር ዳርቻ ( Northern Beaches area) የመጠጥ ቤቶች ፤ የምግብ ቤቶች ፤ የመዝናኛ ስፍራዎች ገዝተው ለመሄድ ለሚፈለጉ ሁሉ ክፍት ናቸው፡፡
ግሬተር ሲድኒ
ከማክሰኞ ምሽት 8፡00 በኋላ በ 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ ምረመራ በማህበረሰ ውስጥ የተሰራጨ 18 የኮሮና ቫይረስ ቁጥር ከታየ በኋላ ፤ የኒውሳውዝ ዌልስ ፕሪምየር ግላዲስ በርጂክልያን የአዲስ አመት ዋዜማ ላይ ጠንካራ ገደብን በግሬተር ሲድኒ ነዋሪዎች ላይ መጣሉን ባለፈው ረቡእ ባደረጉት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል፡፡
ከዛሬ ምሽት በኋላ በግሬተር ሲድኒ የሚኖሩ ነዋሪዎች በቤት ውስጥ የመሰባሰብ ላይ ገደብ የተቀመጠ ሲሆን እስከ 5 ያህል ሰዎችን ብቻ ማስተናገድ ይቻላል ፡፡
“በግሬተር ሲድኒ ዎሎንጎግ ፤ ሴንትራል ኮስት ፤ ኒፓን እና ብሉ ማውንተንስ እንዲሁም የሰሜን የባህር ዳርቻ ደቡባዊ ዞን ነዋሪዎች በአዲስ አመት ዋዜማ እስከ 5 ሰዎችን ማስተናገድ ይችላሉ ” ሲሉ ሚሥ በርጂክልያን ተናግረዋል ፡፡
ከቤት ውጭ የሚደረግ የመሰባሰብ ገደብ ከ 50 ሰዎች ወደ 30 ዝቅ ብሏል ፡፡ይህ ለውጥ ተጨማሪ ማሳሰቢያ እስከሚወጣ ድረስ የሚጸና ይሆናል ፡፡
ቪክቶርያ
ቪክቶርያውያን በዚህ አመት በአውስትራሊያ ጠንካራውና እና ረጅም የተባለውን ገደብ በስቃይ ካለፉ እና ላለፉትም 60 ቀናት ምንም አይነት የማህበረሰብ ስርጭት ባለማስቆጠራቸው ዘና ያለ የአዲስ አመት ዋዜማ እንደሚያሳልፉ ይጠበቃል፡፡
በመኖሪያ ቤታቸው እስከ 30 ያህል ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሲሆን ፤ ከቤት ውጭ እስከ 100 ሰዎች በአንድ ላይ መሰባሰብ ይችላሉ፡፡
የመጠጥ ቤቶች፤ የምግብ ቤቶች እና የምሽት ቤቶች ክፍት የሚሆኑ ሲሆን የሚያስተናግዷቸውን ሰዎች ቁጥር መከታተል ይኖርባቸዋል፡፡
በያራ ወንዝ ዳርቻ ይደረግ የነበረው የፋየር ወርክ ፕሮግራም የተሰረዘ ሲሆን የክልሉ መንግስትም ነዋሪዎች ከከተማ አካባቢ ራሳቸውን እንዲያርቁ ምክራቸውን ለግሰዋል ፡፡ይሁን እና በዚያ አካባቢ በሚገኙ የመዝናኛ ስፍራዎች ቀድመው ቦታ ያስያዙ ሰዎች ክልከላው አይመለከታቸውም ፡፡
ኩዊንስላንድ

آتشبازی شب سال نو بر فراز دریای یارا در ملبورن Source: AAP
ኩዊንስላንድ የኮሮናቫይረስ ሳይታይባቸው ረጅም ጊዜያትን ካሳለፉት ከተሞች መካከል አንዷ ስትሆን ፤ ነዋሪዎች ራሳቸውን ጨምሮ በመኖሪያ ቤታቸው እስክ 50 ያህል ሰዎችን ማስተናገድ ይችላሉ ፡፡
ከቤት ውጭ ለሚደረግ መሰባሰብ እስከ 100 ሰዎች ይፈቀዳል ፡፡
ሳውዝ አውስትራሊያ
የሳውዝ አውስትራሊያ ነዋሪዎች በመኖሪያ ቤታቸው እስከ 50 ያህል ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሲሆን ፤ በሁለት ሜትሮች ስኩዬር ውስጥ አንድ ሰው ብቻ የሚለው ህግ መከበር ይኖርበታል ፡፡
በግል በአዳራሾች በሚዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ እስከ 200 ያህል ሰዎች መገኘት የሚችሉ ሲሆን በሁለት ሜትሮች ስኩዬር ውስጥ አንድ ሰው ብቻ የሚለው ህግ ሊከበርም ግድ ይላል ፡፡
ዌስተርን አውስትራሊያ
በዌስተርን አውስትራሊያ በሁለት ሜትሮች ስኩዬር ውስጥ አንድ ሰው ብቻ የሚለው ህግ እስከተከበረ ድረስ በሚገኙት ሰዎች ቁጥር ላይ የተቀመጠ የቁጥር ገደብ የለም ፡፡
ታዝማንያ
ታዝማንያም እንዲሁ በሁለት ሜትሮች ስኩዬር ውስጥ አንድ ሰው ብቻ የሚለውን ህግ የምትከተል ሲሆን ባልተከፋፈሉ ክፍሎች ውስጥ እስከ 250 ያህል ሰዎች ማስተናገድ ይቻላል ፡፡
ከቤት ውጭ እስከ 1000 የሚሆኑ ሰዎች መሰባሰብ ይችላሉ ፡፡
ኖርዘርን ቴሪቶሪ እና የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
ኖርዘርን ቴሪቶሪ በመኖሪያ ቤቶች እና በውጭ የሚሰባሰቡት ሰዎች ቁጥርን በተመለከተ የተቀመጠ ምንም ገደብ የለም ፡፡ ነገር ግን ሰዎች ሁልጊዜም የ 1.5 ሜትር ርቀትን እንዲጠብቁ ይመከራል ፡፡
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በቤታቸው በሚያስተናግዱት ሰዎች ቁጥር ላይ ምንም አይነት ገደብ አልተቀመጠም፡፡
ከቤት ውስጥ የሚደረግ መሰባሰብን በተመለከት በዋና ከተማዋ ካምብራ እስከ 500 ያህል ሰዎች የተፈቀደ ነው፡፡በሁለት ሜትሮች ስኩዬር ውስጥ አንድ ሰው ብቻ የሚለው ህግ እስከተከበረ ድረስ ፡፡
በአውስትራሊያ የሚኖሩ ዜጎች በመካከላቸው ቢያንስ የ 1.5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ አለባቸው ፡፡
በጋራ የመሰባሰብ ገደብን በተመለከተ የየክልላቸውን የገደብ ህግ መመልከት ጠቃሚ ነው፡፡
የክልል እና ግዛቶች አዳዲስ መረጃዎች በተመለከተ ፦ , , , , , , .