የኒው ሳውዝ ዌይልስ የኮሮናቫይረስ ገደብ እስከ ጁላይ 30 ተራዘመ

*** ሜልበርን ውስጥ ሰባት ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቁ

A pedestrian walks past a deserted Sydney Opera House during the city's lockdown.

A pedestrian walks past a deserted Sydney Opera House during the city's lockdown. Source: AAP

ኒው ሳዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 97 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል።

የሲድኒ የኮሮናቫይረስ ገደብም ለተጨማሪ ሁለት ሳምንታት እስከ ጁላይ 30 እንዲራዘም መወሰኑን ፕሪሚየር ግላዲስ በርጂክሊያን አስታወቁ።

ወ/ሮ በርጂክሊያን የተጣሉትን ገደቦች ከመነሳታቸው በፊት  በሁለቱ ሳምንታት ውስጥ የቫይረሱን መስፋፋት መጠን አስመልክቶ ግምገማ እንደሚደረግ ገልጠዋል። 

የጤና ባለ ስልጣናት የፌርፊልድ ነዋሪዎች ከቤት እንዳይወጡ፤ የካንተርበሪና ሊቨርፑል ነዋሪዎችም እንቅስቃሴያቸውን እንዲገድቡ አሳስበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 7 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን አስታውቃለች።

በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ ስድስቱ ከኒው ሳውዝ ዌይልስ የቤት ዕቃ አጓጓዦች ጋር በነበራቸው ንኪኪ የተጠቁ ሲሆን አንደኛው ግለሰብ ከሲድኒ ወደ ሜልበርን የተመለሰ ነው።

 

 


Share

Published

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends