የድምፅ ለፓርላማ ጥያቄ ምን እንደሆነ አውቀናል፤ ለሕዝበ ውሳኔው ቀጣዩ ሂደት ምንድነው?

አውስትራሊያውያን ለነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማ ሕዝበ ውሳኔ የሚቀርበውን መጠይቅ አውቀዋል። ቀጣዩን እነሆ።

The Voice to Parliament referendum is due to take place this year.jpg

The Voice to Parliament referendum is due to take place this year. What do we know so far? Credit: SBS News / Lilian Cao

አንኳሮች
  • አንቶኒ አልበኒዚ የድምፅ ለፓርላማ ሕዝበ ውሳኔ አርፍተ ነገሮችን ዐ ይፋ አድርገዋል
  • አውስትራሊያውያን በዚህ ዓመት መጨረሻ ወደ ድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ያመራሉ
  • አቶ አልባኒዚ የሚቆመው አካል የተግባር ዝርዝሮችን አስታውቀዋል
አውስትራሊያውያን ለነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማ ሕዝበ ውሳኔ ድምፃቸውን የሚሰጡባቸው አርፈተ ነገሮች ምን አንደሆኑ አውቀዋል።

ድምፅ ሰጪዎች ከሩብ ክፍለ ዘመን በኋላ የመጀመሪያው በሆነው ሕዝበ ውሳኔ ድምፃቸውን ይሰጣሉ። ለስኬት ከበቃ አውስትራሊያውያን ከ1977 ወዲህ ለሕገ መንግሥት መሻሻል ድምፃቸውን ሲሰጡ ይህ የመጀመሪያው ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ ከድምፅ ለፓርላማ የሥራ ቡድን ጋር ስብሰባ ካካሔዱ በኋላ በምርጫ ወረቀት ላይ ለሕትመት የሚበቃውን ጥያቄ ይፋ አድገርዋል፤

ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻል በማድረግ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኞች ድምፅ ለፓርላማን ለመመሥረት ለአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ዕውቅናን መቸር፤ ለዚህ ማሻሻያ ይሁንታዎን ይሰጣሉ?
ረቂቁ ለፓርላማ ተመርቶ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክር ቤት በአብላጫ ድምፅ በማለፍ ወደ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ለይሁንታ ተመርቷል።

የድምፅ ለፓርላማ አተገባበር ምን ይመስላል?

ድምፅ ለፓርላማ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ጉዳዮችን ለመንግሥት የሚያማክር አካል ነው። ማናቸውም ዓይነት ሕጎች ላይ ድምፅን በድምፅ የመሻር ስልጣን የለውም።

አቶ አልባኒዚ ድምፅ ለፓርላማ እንደምን እንደሚሠራ በዝርዝር ሲያስረዱ፤

  • አባላት "ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ" በቀናት የተገደቡ የአገልግሎት ጊዜያት ይኖራቸዋል
  • የአባላቱ ተዋፅዖ ወጣቶችን አካትቶ የፆታ ሚዛንን የጠበቀ ይሆናል
  • ተወካዮቹ ከሁሉም ክፍለ አገራትና ግዛቶች የተውጣጡ ይሆናሉ
  • በተለይ በጣሙን ርቀው የሚኖሩ ማኅበረሰባትንም ያካትታል
ብለዋል።

ይሁንና አባላቱ የሚመረጡት በዲሞክራሲያዊ መንገድ ይሁን ወይም በስየማ ስለመሆን ጉዳይ ዘልቀው አልገቡም።
The question is slightly different to the draft wording Mr Albanese unveiled at the Garma festival last year.jpg
The question is slightly different to the draft wording Mr Albanese unveiled at the Garma festival last year. Credit: AAP / Aaaron Bunch / AAP Image

ቀጣዮቹ እርምጃዎች ምንድን ናቸው?

የፓርላማ የይሁንታ ድምፅ ካገኘ በኋላ ለሕዝብ ድምፅ ይቀርባል።

ሕዝበ ውሳኔ ከመካሔዱ በፊት ድንጋጌው በፓርላማ ማለፍ ይኖርበታል።

እንዲያም ሆኖ፤ ድንጋጌው በተወካዮች ምክር ቤትና በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ማለፈን ግድ አይልም። በሌበር አብላጫ ድምፅ በተያዘው የተወካዮች ምክር ቤት ለሁለት ጊዜያት ደጋግሞ ማለፍ ይችላል። ይህም ማለት የፓርላማን ይሁንታ ለማግኘት ስኬቱ አስተማማኝ ነው።

ድምፅ ለፓርላማ ዕውን እንዲሆን ግና አብላጫ የድምፅ ሰጪዎችንና የአብላጫ ክፍለ አገራትን ድምፆች በሕዝበ ውሳኔ ማግኘት ይኖርበታል።

ያ መስፈረት ከተከወነ በኋላ የነባር ዜጎች ማኅበረሰባትና የተቀረው ሕዝብ "የድምፅ ለፓርላማን ዲዛይን የመከወን" ሂደት እንደሚጀምሩ አቶ አልባኒዚ ተናግረዋል።

እንዲያ ከሆነ በኋላ እንደ ማንኛውም ረቂቅ ሕግ ፓርላማ ቀርቦ ክርክርና ክለሳ ይካሔድበታል።

ድምፅ ልንሰጥ የምንችለው መቼ ነው?

በቀጣይነት በሕዝበ ውሳኔ ወቅት አውስትራሊያውያን ድምፅ ሰጪዎች "ይሁን" ወይም "አይሁን" ብለው ድምፃቸውን እንደሚሰጡም አቶ አልባኒዚ አመላክተዋል።
possible Dates.jpg
ትንሽ ፍንጭ።

አቶ አልባኒዚ በተደጋጋሚ ሕዝበ ውሳኔው በዚህ ዓመት መጨረሻ እንደሚከናወን ቃል ገብተዋል።

ባለፈው ወር ከቶውንም ከዚያም አለፍ ብለው መራጮች ኦክቶበር ወይም ዲሴምበር ላይ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እንደሚያመሩ ተናግረዋል።

ቀደም ሲል ሕዝበ ውሳኔዎች የተካሔዱት ቅዳሜ ላይ በመሆኑ ለድምፅ መስጫ ያሉ ቀናት አነስተኛ ናቸው።

Share
Published 1 June 2023 6:18pm
By Finn McHugh, Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends