*** ኖቫክ ጆኮቪች የፍርድ ቤት ውዝግቡን አሸንፎ ከኢሚግሬሽን ማገቻ ወጣ

በወንዶች ቴኒስ ቁጥር አንድ ደረጃ ላይ የሚገኘው እና የኮቪድ - 19 ክትባትን ያልተከተበው ጆኮቪች ባለፈው ሀሙስ ቪዛው እንዲሰረዝ የተደረገው በፌደራል መንግስት ውሳኔ ነው።

Serbia's Novak Djokovic holds the Norman Brookes Challenge Cup after defeating Russia's Daniil Medvedev in the men's singles final at the 2021 Australian Open

Serbia's Novak Djokovic holds the Norman Brookes Challenge Cup after defeating Russia's Daniil Medvedev in the men's singles final at the 2021 Australian Open Source: AP

ኖቫክ ጆኮቪች የፍርድ ቤት ውዝግቡን አሸንፎ ከኢሚግሬሽን ማቆያ ወጣ።

የፌደራል ሰርኪዩት ኮርት የተሰረዘውን የኖቫክ ጆኮቪች ቪዛ ውሳኔ እንዲቀለበስ በመወሰኑ ማምሻውን ከኢሚግሬሽን ማቆያ ወጥቷል።ነገር ግን በተያያዥ ቪዛው ሊሰረዝበት እና ለመጪው ሶስት አመታት ወደ አውስትራሊያ እንዳይገባ ሊከለከል እንደሚችል ተገምቷል ።

በወንዶች ቴኒስ ቁጥር አንድ ደረጃ ላይ የሚገኘው እና የኮቪድ - 19 ክትባትን  ያልተከተበው ጆኮቪች ባለፈው ሀሙስ ቪዛው እንዲሰረዝ የተደረገው በፌደራል መንግስት ውሳኔ ሲሆን፤ ምክንያቱም “ ወደ አገሪቱ ሲገባ ሊያሟላ የሚገባውን ትክክለኛ መረጃዎችን አላሟላም ” በሚል ሰበብ ነበር ።

ጉዳዩ በፍርድ ቤት እስኪታይ ድረስም በኢሚግሬሽን ማቆያ ስፍራ እንዲቀመጥ ተደርጓል።

በጆኮቪች ጠበቃ እና በሆም አፌርስ ሚኒስትር ካረን አንድሪውስ ፤ ዳኛው አንተኒ ኬሊ መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረትም ፤ ሰኞ ከቀትር በኋላ የተሰረዘው የቪዛ ውሳኔ እንዲቀለበስ እና በአስቸኳይ ነጻ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል።

የሰኞ የፍርድ ቤት ስሚው እስኪደርስ በታገተበት የኢሚግሬሽን ማገቻ ቆይታው ከፍተኛ የሆነ አለማቀፋዊ ሽፋንን እና ውዝግቦችንም ፈጥሮም ነበር። በመንግስት በኩል ያሉት ጠበቆችም ባለፈው ሀሙስ ጠዋት የቪዛውን መሰረዝ  አስመልከቶ ምላሽ እንዲሰጥ በቂ የሆነ ጊዜ እንዳልተሰጠው አምነዋል ።

ነገር ግን መንግስትን ወክለው የሚከራከሩት ጠበቃ ክርስቶፈር ትራን ለፍርድ ቤት እንዳስረዱት የኢሚግሬሽን ሚኒስትሩ  አሌክስ ሆክ ፤ የሚኒስትሩን ጣልቃ የመግባት መብት በመጠቀም እንደገና ቪዛውን የመሰረዝ መብታቸውን አሁን ለመጠቀም ማሰብ ይችላሉ ብለዋል ።

ዳኛው ኬሊ በበኩላቸው ሚኒስትሩ ያላቸውን መብት ተጠቅመው ቪዛውን ከሰርዙት የ 34 አመቱ ሰርቢያዊ የቲኒስ ተጫዋች ለመጪዎችት ሶስት አመታት አውስትራሊያ እንዳይገባ ይታገዳል ብለዋል።

የአውስትራሊያ የድንበር ህግ ሁለቱን ክትባቶች ያልተከተቡ የውጭ አገር ሰዎች እንዳይገቡ የሚከለክል ሲሆን ፤ ነገር ግን ይህን ለማለፍም ካስፈለገ  የህክምና ማስረጃ ማቅረብ የግድ ይላል።

ጆኮቪች ከሃኪሞች እና ፤ ከተለያዩ ባለስልጣናት ፤ ከቪክቶርያ ተወካዮች እና ቴኒስ አውስትራሊም ጭምር ወደ አውስትራሊያ እንዲጓዝ ፈቃድን ያገኘ ሲሆን  ከዚህ በላይ ምን ያድርግ ሲሉ ዳኛው ኬሊ ተናግረዋል ።
Novak Djokovic at the 2020 Australian Open at Melbourne Park on February 2, 2020.
Novak Djokovic at the 2020 Australian Open at Melbourne Park on February 2, 2020. Source: AAP
መንግስትን ወክለው የሚከራከሩ ጠበቃዎች በበኩላቸው የጆኮቪች አለመከተብ በአውስትራሊያ ህዝብ ጤና እና ደህነነት ላይ አደጋ ይጥላል ሲሉ የመከራከሪያ ሃሳባቸውን አቅርበዋል ።
Camera crews surround a van as it leaves the Park Hotel on Monday 10 January 2022
Camera crews surround a van as it leaves the Park Hotel on Monday 10 January 2022 Source: AAP
ቁጥራቸው በርካታ የሆነ ደጋፊዎቹም ታግቶ በቆየበት ፓርክ ሆቴል ተቃውሟቸውን ሱያሰሙ ቆይተዋል ።

የጆኮቪች ነጻነት ማለት በቅርቡ የሚጀመረውን የአውስትራሊያ ኦፕንን ዘውድ ለመጫን እና ግራንድ ስላምን ለ21ኛ ጊዜ ለማሸነፍ እጅግ የቀረበ እንደሆነ ማረጋገጫ ነው ተብሎለታል።


Share
Published 10 January 2022 9:49pm
Updated 10 January 2022 10:04pm
By Evan Young
Presented by Martha Tsegaw
Source: SBS News


Share this with family and friends