የኣዕምሮ ጤና ግልጋሎቶች በመላ አገሪቱ በተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛሉ፤ በአብዛኛው የሚስተዳደሩትም በክፍለ አገራት ነው።
የአዕምሮ ጤና ድጋፍ የሚያሻባቸው መጠነ ሰፊ ሁኔታዎች አሉ። የመንፈስ ሁከትና ድባቴ፣ ባይፖላር፣ ድኅረ መንፈስ ጭንቀት፣ የስብዕና መታወክ የመሳሰሉ የአዕምሮ ሕመሞች በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሊቀሰቀሱ ይችላሉ።
ብዙውን ጊዜ እነዚህ ተቋማት የራሳቸው የሆኑ አስተርጓሚዎች የሌላቸው ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት የሚደጎሙትን አገልግሎት ሰጪዎች ይጠቀማሉ፡፡ የትርጉም እና የማስተርጎም አገልግሎትTranslating and Interpreting Service - TIS የስልክ እና በአካል በመገኘት የማስተርጎም አገልግሎትን በ 150 ቋንቋዎች ያቀርባል፡፡
ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ መደብ ጀርባዎች ባላቸው የአዕምሮ ጤና ላይ የሚያተኩረው ፕሮጄክት የሚመራው በአዕምሮ ጤና አውስትራሊያ ሲሆን ባሕላዊ ይዘት ባለ መልኩ የእገዛ ምንጮች፣ ግልጋሎቶችንና መረጃን ያቀርባል።
ከከባድ ስቃይ እና እንግልት ለተረፉ ስዎች አገልግሎትን የሚሰጠው የአውስትራሊያውያን ሸንጎ( The Forum of Australian Services for Survivors of Torture and Trauma (FASSTT) የስምንት ልዩ የማገገሚያ ተቋማት ጥምር አገልግሎት ሲሆን ፤ በሌሎች አገራት እጅግ አሰቃቂ የሚባሉ ስቃዮችን አልፈው ወደ አውስትራሊያለሚመጡ ሰዎችአገልግሎትየሚሰጥ፡፡ የ FASSTTተቋማት አብዛኛዎቹ በስደተኝነት ወይም በሰብአዊነት ፈቃድ ወደ አውስትራሊያ የገቡ ናቸው፡፡
የአእምሮእ ጤና ባለሙያዎችን ለማግኘት ይመልከቱ ፡፡
ብሔራዊ የአዕምሮ እርዳታና ግልጋሎቶች
- ላይፍላይን ( Lifeline ) - 13 11 14
- ሚሽን አውስትራሊያ( Mission Australia) -
- ቢዮንድ ብሉ( Beyond Blue ) - 1300 22 4636
- ሄድስፔስ (Headspace ) -
- ራስን የማጥፋት ስላጎትን የሚያስጥሉ (የሚከላከሉ) የስልክ አገልግሎቶች( Suicide Call Back Service -) www.suicidecallbackservice.org.au 1300 659 467
- ልጆችን የሚረዱ የስልክ መስመሮች ( Kids Helpline ) 1800 55 1800
- ወንዶችን የሚረዱ መስመሮች በአውስትራሊያ ( MensLine Australia ) - 1300 78 99 78
የቢዮንድብሉ ግልጋሎቶች መረጃ በዝንቅ ቋንቋዎች፤
የጤና ዲፓርትመንት ሶስት ኮቨድ -19 የአዕምሮ ጤና ማስገንዘቢያዎችን በደርዘኖች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች አስተርጉሟል፤
ኒው ሳውዝ ዌልስ
ኒው ሳውዝ ዌልስ የአእምሮ ጤና የስልክ መስመር
ይህየአእምሮ ጤና የስልክ መስመር በኒው ሳውዝ ዌልስ ለሚኖሩት ሁሉ የ24 ሰአታት አገልግሎትን በሳምንት ሰባቱንም ቀናት በ 1800 011 011 መስመርይሰጣል፡፡
ተዛማጅ ባህል ያላቸውን የሚያገለግል የአእምሮ ጤና ማእከል ( Transcultural Mental Health Centre (TMHC)
ክልል አቀፍ የሆነው አገልግሎት ከተለያያ ቋንቋ እና ባህል ለመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የአምሮ ጤና አገልግሎቶች ተደራሽነትን ያረጋግጣል ፤ የምክር እና ምርመራን ፤ የአእምሮ ጤና ንቃትን ፤ እንዲሁም ለስልጠና እናማስተማሪያ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ያቀርባል፡፡
(TMHC) ተዛማጅ ባህል ያላቸው ባለሙያዎቹ ከግለሰቦች እና ከኒው ሳውዝ ዌልስ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ጋር ግንኙነት ላላቸው ቤተሰቦች ነጻ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡ በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን ከአካባቢ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ቡድን ደብዳቤ ያስፈልጋል፡፡የ (TMHC)የሰራ ባልደረባ ሆነው ቋንቋን መናገር ለማይቸሉት እና አስተርጓሚ ለሚሹ TIS መጠቀም ይቻላል፡፡
ከከባድ ስቃይ እና እንግልት ለተረፉ ስዎች የህክምና እና የማገገሚያ አገልግሎት የሚሰጠው( Service for the Treatment and Rehabilitation of Torture and Trauma Survivors, STARTTS) STARTTS
ባህልን መሰረት ያደረጉ የስነልቡናዊ ህክምናዎችን እና እርዳታዎችን ያቀርባል፡፡ በተጫማሪም ማህበረሰባዊ ተሳትፎን በማበረታታት ግለሰቦች እና የህብረተሰብ አባላት በስደት፤ እንግልት እና ስቃይ ሳቢያ የደረሰባቸውን ጠባሳ እንዲድን ፤ እንዲሁም በአውስትራሊያ ህይወታቸውን እንደገና እንዲገነቡ ያደርጋል፡፡
የSTARTTS የስራ ባልደረባ ሆነው ቋንቋውን መናገር ለማይቸሉት እና አስተርጓሚ ለሚሹ TIS አስተርጓሚን ያቀርባል
ቪክቶርያ
ፋውንዴሽን ሀውስ ( Foundation House for Survivors of Torture)
ድርጅቱ ነጻ የሆነ አገልግሎትን ለስደተኞች ወይም በስደት ጉዞ ውስጥ ላለፉ ሰዎች በእንግሊዝኛ ፤ አረብኛ ፤ ሃካ ቺን ፤ ዳሪ ፤ ዲንካ ፤ ካረን ፤ ፐርዥያን ፤ስዋሂሊ ፤ ታሚል እና ትግርኛ ቋንቋዎች ያቀርባል ፡፡
ይህንን አገልግሎት ለማግኛት መመዘኛዎቹን ማሟላትዎን ለማወቅ ይሞክሩ፡፡
የቪክቶርያ ክልል የአእምሮ ጤና መረጃን በተመለከተ ተጨማሪ ማውጫን ወይም ዝርዝርን አዘጋጅቷል፡፡ ይህ ሂደት በቪክቶሪያ መንግስት ተነሳሽነት የተጀመረ ሲሆን የሚመራውም በባህል ማእከል ( Centre for Culture )ነው፡፡ በርከት ያሉ በጤና ዙሪያ የተተርጎሙ የመረጃ ስብስብን በማካተቱ ተጠቃሚዎች በቀላሉ ሊያገኙት ይችላሉ ፡፡
በቪክቶርያ ሌሎች ሁለት ድርጅቶች በአእምሮ ጤና ዙሪያ ስልጠናዎችን በመስጠት ይታወቃሉ ፡፡ ይሁንና ቀጥታ እርዳታን በግለሰብ ደረጃ አያቀርቡም፡፡
አክሽን ኦን ዲሴብሊቲ ኢን ኤትኒክ ኮምዪኒቴስ ( Action on Disability in Ethnic Communities (ADEC)
ADECየተለያዩ ባህል ያላቸውን የሚያገለግል የአእምሮ ጤና መርሃ ግብር ያለው ሲሆን( Transcultural Mental Health Access Program (TMHAP) ጠቀሜታውም የአእምሮ ጤና አገልግሎቶችን ለመድብላባህል የህብረተሰብ ክፍሎች ማዳረስ ነው ፡፡ የአእምሮ ጤናን በተመለከተ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ፤ አገልግሎቶች የት እንደሚገኙ እና እንክብካቤ ከየት ሊገኝ እንደሚችል ተዛማጅ ባህል ካላቸው ማህበረሰቦች በስፋት ይሰራል፡፡
የቪክቶሪያውያን ተዛማጅ ባህል ያላቸው የአእምሮ ጤና ክፍል( Victorian Transcultural Mental Health (VTMH)በቀደሞ ስሙ የቪክቶሪያውያን ተዛማጅ ባህል ያላቸው የሳይካትሪ ክፍል ( Victorian Transcultural Psychiatry Unit) VTPU በመባል ይታወቅ የነበር ሲሆን VTMH የአእምሮ ጤና አገልግሎቶችን ፤ የሳካትሪክ እንዲሁም ከአካል ጉደተኞ ጋር ለሚሰሩ ባለሙያዎች እና የተለያዩ ቋንቋ እና ባህል ላላቸው ተጠቃሚዎች እና ተንከባካቢዎች አገልግሎትን ይሰጣል፡
ከተለያ የስፍራ የሚመጡ ጥያቄዎችን ማለትም ባለሙያዎችን በተመለከተ፤አገልግሎች ሰጪዎችን፤ የማህበረሰብእድገትን ፤ትምህርትን፤ተጠቃሚነት እና በእንክብካቤ ዙሪያ ሊኖር የሚችል ተሳትፎን በተመለከተ መርሃግብሮችን ያዘጋጃል፡፡ይሁንና ቀጥተኛ አገልግሎትን ለግልሰቦች አይቀርብም ፡ ፡
ኩዊንስላንድ
በኩዊንስላንድ ተዛማጅ ባህል ያላቸውን የሚያገለግል የአእምሮ ጤና ማእከል Queensland Transcultural Mental Health Centre (QTMHC)
(QTMHC) በባለሙያዎች የሚሰጥ ክልል አቀፍ አገልግሎት ሲሆን አሰራሩም ከተዛማጅ ባህል እና ቋንቋ ለመጡ የህብረተሰብ ክፍል አባላት ባህልን መሰረት ያደረግ የአእምሮ ጤና ክብካቤን እና ድጋፍን ማድረግ ነው፡፡
የትርጉም መረጃዎችንም ያቀርባል ፦ እንዲሁም በአካባቢያዊ የጤና አስተባባሪዎች አማካኝነትም ባለሙያዎችን ለማግኘት ያስችላል ፡፡
በኩዊንስላንድ ከከባድ ስቃይ እና እንግልት ለተረፉ ስዎች የእርዳታ አገልግሎት መስጫ ፡ Queensland Program of Assistance to Survivors of Torture and Trauma (QPASTT)
QPASTT አመቺ እና ባህልን ከግምት ውስጥ ያደረግ አገልግሎትን በማስተዋወቅ ሰዎች አውስትራሊያ ከመምጣታቸው በፊት ከስደት ጋር በተያያዘ ከደረሰባቸውን እንግልት እና ስቃይ እንዲያገግሙ ፤ ጤናቸው እና ደህንነታቸውን እንዲረጋገጥ የሚሰራ ነው፡፡
ከደርሰባቸው አደጋ ተርፈው ለመጡ ሰዎችም ነጻ የሆነ የምክር አገልግሎትን ጨምሮ የስነልቡናዊ እና ማህበረሰባዊ እርዳታን ያቀርባል፡፡
አለማቀፍ የጤና ቡድን
መሰረቱን ብሪዝበን ያደረገው አለማቀፍ የጤና ቡድን ተዛማጅ ቋንቋ እና ባህል ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያየ መርሃ ግብሮችን ያቀርባል ፦
- መድብላ ባህላዊ የስነልቡናዊ ህክምና መርሃ ግብር ፦ የተለያዩ ቋንቋ እና ባህል ላላቸው እና በብሪዝበን ሰሜን እና ደቡብ አካባቢ ለሚኖሩ ሰዎች የተዘጋጀ ነው፡፡ መካከለኛ ደረጃ የሚባል የአእምሮ ጤና ችግር ላለባቸው ሰዎች ባህልን መሰርት ያደረግ ስነልቡናዊ እንክብካቤን ያቀርባል፡፡
- የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጤና ፦አደጋ ላይ ለሆኑ ሰዎች የታቀደ እና ባህልን ከግምት ውስጥ ያስገባ ፤ ሁሉን አቀፍ ፤ ቤተሰብን ማእከል ያደረገ የተቀናጀ እንክብካቤን የሚያቀርብ ሲሆን የለረጅም ጊዜ ግቡም ቀጣይ የጤና ጠንቆችን መቀነስ ነው፡፡
- ለአለማቀፍ ተማሪዎች የሚሆን የጤና አገልግሎት ፦ የጤና ተቋማት በልዮ ሃኪሞች አማካኝነት የተለያዩ ቋንቋ እና ባህል ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎትን እንደሚያቀርቡት ሁሉ ፤ የአለማቀፍ ተማሪዎችም Overseas Student Health Cover (OSHC) ይህንኑ አገልግሎት መጠቀም ይችላሉ ፡፡
- ካልቸር ኢን ማይንድ ፦ ማህበረሰብ ላይ የተመሰረተ መርሃ ግብር ሲሆን የስነልቡና እና ማህበረሰባዊ እርዳታን የተለያዩ ቋንቋ እና ባህል ላላቸው እንዲሁም እድሜያቸው ከ 18 አመት በላይ ለሆኑ እና በላይኛው ብሪዝበን አካባቢ ለሚኖሩ የሚያገለግል ነው፡፡
ሃርመኒ ፕሌስ
ሃርመኒ ፕሌስ መንግስታዊ ያልሆነ እና ማህበረሰብን መሰረት ያደረገ መድብለ ባህላዊ ድርጅት ሲሆን ፤ ባህልን ከግምት ውስጥ ያደረገ የአእምሮ ጤና አገልግሎትን ከተለያዩ ቋንቋ እና ባህል ለመጡ ሰዎች አገልግሎትን ይሰጣል፡፡እድሜያቸው ከ12 አመት በላይ ከሆኑ ተጠቃሚዎች ጋር የሚሰራ ሲሆን ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎችንም ያጠቃልላል ፡፡በመላው ኩዊንስላድ አገልግሎቱ የሚሰጥ ሲሆን በተለይም መድብለ ባህል በሚታይባቸው የብሪዝበን ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች ፤ ሎገን ፤ ኢፕስዊች ፤ እና ጎልድ ኮስት በዋናነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
የአእምሮ ጤና የስልክ መስመሮች
1300 MH 1300 642255 የአእምሮ ጤና የስልክ አገልግሎቶች ምስጢራዊ ናቸው፡፡ ኩዊንስላንደርስ የህዝብ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ተቋማትን ለማግኘት በቅድሚያ የስልክ አገልግሎቶችን መጠቀም ግድ ይላቸዋል፡፡
ኖርዘርን ቴሪቶሪ
MHACA (Central Australia)
MHACA እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ ለሆኑ እና የአእምሮ ችግር እንዳለባቸው ለተረጋገጠ ሰዎች አገልግሎትን ያቀርባል፡፡ቀጠሮን በማያስዝ የአስተርጓሚ አገልግሎትን በቻይንኛ ፤ ኡርዱ ፤ አይሪሽ ፤ እና ሂንዲ ቋንቋዎች ማግኘት ይቻለል፡፡
ቲምሄልዝ TeamHealth (Darwin)
ቲምሄልዝ በኖርዘርን ቴሪቶሪ የአእምሮ ጤናን በተመለከት ስጋት ላላቸው ፤ ለችግር ለተጋለጡ እና አገልግሎትን በበቂ ሁኔታ ተጠቃሚ ላለሆኑ የአካባቢው ህብረተሰብ አባለት አገልግሎትን እና ድጋፍን ያደርጋል፡፡
ሜላሊኡካ የስደተኞች ማእከል Melaleuca Refugee Centre
ትርፍን ለማግኘት በሚል ሰበብ ያልተመሰረተ ድርጅት ሲሆን ይልቁንም የሰዎች ክብር የሚጠብቁ አግልግሎትን ለሰደተኞች እና ለመጤ የማህበረሰብ ክፍል አባለት ፤ ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች ያቀርባል፡፡በተጨማሪም ለቤተሰቦች ፤ ለጎልማሶች ፤ ለህጻናት እና ወጣቶች የነጻ አገልግሎትን ይሰጣል፡፡
የኖርዘርን ቴሬቶሪ የአእምሮ ጤና የስልክ መስመር ፡ Northern Territory Mental Health Line: 1800 682 288
የክልሉ የአእምሮ ጤና አገልግሎት በአእምሮ ጤና የእርዳታ የስልክ መስመር ሊገኝ የሚችል ሲሆን የአስተርጓሚ አገልግሎት ካስፈለገም ያቀርባል፡፡
ዌስተርን አውስትራሊያ
ከከባድ ስቃይ እና እንግልት ለተረፉ ስዎች አገልግሎት የሚሰጥ ማህበር ፡ Association for Services to Torture and Trauma Survivors (ASeTTS)
ASeTTS ስደተኞች እንዲሁም ከከባድ ስቃይ እና እንግልት የተረፉ ስዎች ህይወታቸውን እንደገና እንዲገነቡ ሁሉን አቀፍ አገልግሎትን በአረብኛ ፤ዲንካ ፤ ካረን ፤ ኪሩንዲ ቋንቋዎች የሚያቀርብ ነው፡፡
West Australian Transcultural Mental Health Centre
በዌስት አውስትራሊያ ተዛማጅ ባህል ያላቸውን የሚያገለግል የአእምሮ ጤና ማእከል
ይህ አግልግሎት የሚሰጠው በሮያል ፐርዝ ሆስፒታል ብቻ ሲሆን ህመምተኞ ከሆስፒታሉ ከወጡ በኋላ ለሶስት ጊዜ ያህል ብቻ አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ፡፡
አስተርጓሚዎችን በስልክም ሆነ በአካል ማግኛት ይቻላል ፦
ታዝማንያ
ፎኒክስ ሴንተር Phoenix Centre
ፎኒክስ ሴንተር የሚመራው በማይግራንት ሪሶርስ ሴንተር ሲሆን ከከባድ ስቃይ እና እንግልት ለተረፉ ስዎች ልዩ የባለሙያዎች አገልግሎትን ያቀርባል፡፡ የግለሰቦችን እና ማህበረሰቦችን ጤና እና ደህንነት የሚያስጠብቁ የምክር እና ስፋት ያላቸው የስልጠና መርሃ ግብሮችን ያቀርባል፡፡ የፎኒክስ ሴንተር ሰራተኞች በሆባርት እና ሎንሴስተን መሰረታቸውን በማድረግ ክልል አቀፍ አገልግሎትን ያበረክታሉ፡፡
የታዝማኒያ መንግስት የአእምሮ ጤና አገልግሎት የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ነዋሪዎችን ተቀብለው የሚያስተናገዱ ሲሆን ለዚህም የማህበረሰብ የጤና ማእከላትን፤ የመንግስት የጤና ተቋማትን ፤ የግል ልዩ ሃኪሞችን እና የቤተሰብ ሃኪሞች በማካተት በጋራ ይሰራሉ፡፡
The assessment and referral call helpline is 1800 332 388
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
ካምፓኒየን ሃውስ ከከባድ ስቃይ እና እንግልት የተረፉ ስዎችን የሚረዳ ተቋም_ Companion House, Assisting Survivors of Torture and Trauma
ካምፓኒይን ሃውስ በድጋፍ ሰጪ ሰራተኞቹ አማካኝነት የምክር አገልግሎትን ለጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች ያቀርባል፡፡የካምፓኒይን ሃውስ አላማው ሰዎች የአውስትራሊያ ህይወታቸውን እንደገና እንዲገነቡ ፤ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንዲቋቋሙ እና የስቃይ ዘመኑን ጠባሳ እንዲረሱ የሚያደርግ ነው፡፡
የምክር አገልግሎት ባለሙያዎቹ አዲስ ከመጡትም ጋር ሆነ ለረጅም ጊዜ በሰፈራ ከቆዩ ጋር የሚሰሩ ሲሆን በተጨማሪም ለጎልማሶች ፤ ለህጻናት እና ወጣቶች የሚሆኑ አግልግሎቶችን ያቀርባሉ፡፡
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ መንግስት የአእምሮ ጤና የአደጋ ጊዜ አገልግሎትን በስልክ ቁጥር (1800 629 354 or 02 6205 1065) ወይም በድረ ገጽ ማግኘት ይቻላል፡፡
ሳውዝ አውስትራሊያ
ሬሌሽን አውስትራሊያ Relationships Australia
ግለሰባዊ ትምህርት እና የማህበረሰብን ማሳደጊያ The Personal Education and Community Empowerment (PEACE) ይህ ተቋም አገልግሎቱን የሚያቀርበው ማንኛውንም አይነት የይልፍ ወረቅት (ቪዛ ) ላላቸው የመድብለባህል የማህበረሰብ ክፍል አባለት ነው፡፡ PEACE ለግለሰቦች ፤ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች አገልግሎትን ይሰጣል፡፡
ከከባድ ስቃይ እና እንግልት የተረፉ ስዎች መርጃ እና ማቋቋሚያ አገልግሎት Survivors of Torture and Trauma Assistance and Rehabilitation Service, STTARS
STTARS ለስደተኞች እና ከስደት ጋር ተመሰሳይ ህይወት ላሳለፉ ልዩ የምከር አግልግሎትን የሚሰጥ ሲሆን አላማውም ባማገገም እና መዳን ሂደት ጉዞ ውስጥ ድጋፍን ማድረግ ነው፡፡አገልግሎቱ ያለምንም ክፍያ የሚሰጥ ሲሆን አንድ ሰው የፈለገውን ያህል ጊዜ በአውስትራሊያ ቢቆይም አገልግሎቱን ከማግኘት የሚያግደው የለም፡፡ የSTTARS ተጠቃሚ ለመሆን ወረፋ መጠበቅ ግድ የሚል ቢሆንም በአስቸኳይ መታየት የሚገባቸው ካሉ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
የSTTARS አገልግሎት ያለምንም ክፍያ ፤ በፈቃደኝነት ፤ምስጢራዊነቱን ተጠብቆ በሙያው በተካኑ የምክር ሰጪ እና አስተርጓሚዎች የሚካሄድ ነው፡፡ ለህጻናት፤ ለወጣቶች ፤ ለቤተሰቦች እና ለጥገኝነት ጠያቂዎች ተጨማሪ መርሃ ግብሮችን ያቀርባል፡፡
በአውስትራሊያ የሚኖሩ ዜጎች 1. 5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ አለባቸው፡፡ መሰባሰብን በተመለከተም የክልሉን ገደብ መመልከት ያስፈልጋል፡፡የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በአሁን ሰአት በሰፊው ይደረጋል፡፡የብርድ ወይም ጉንፋን ምልክቶችን ካሳዮ ሃኪምዎ ጋር በመደወል ምርመራን እንዲያደርጉ መጠየቅ የሚችሉ ሲሆን ወይም coronavirus Health Information Hotline on 1800 020 080 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
The federal Government’s coronavirus tracing app COVIDSafe በይፋ ስለወጣ በስልክዎ ላይ ይጫኑ፡
ኤስ ቢ ኤስ ለአውስትራሊያውያን መድብለ ባህል ማህበረሰብ አዳዲስ ኮቪድ- 19 መረጃዎችን በትጋት ያደርሳል፡፡ ዜናዎች እና መረጃዎች በ63 ቋንቋዎች ይገኛሉ ከ