አንኳሮች
- በዚህ ዓመት ማብቂያ ግድም በሚከናወነው ሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ለመስጠት ከ17 ሚሊየን በላይ አውስትራሊያውያን ተመዝግበዋል
- የድምፅ ለፓርላማ ድንጋጌ ይሁንታን አግኝቶ ማለፍ የድምፅ መስጫን ቀን ለመቁረጥ ግድ አሰኚ ነው
- የድምፅ መስጫው ቀን በሁለት ወራት ውስጥ መቆረጥና ሕዝበ ውሳኔውም ከጁን 19 አንስቶ በስድስት ወራት ጊዜያት ሊከወን ይገባል
ይህን መጣጥፍ ለወዳጅዎችዎና ለቤተሰብዎ ያጋሩ
አውስትራሊያውያን የድምፅ ለፓርላማ ድንጋጌ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት 52 ለ 19 በሆነ ድምፅ ማለፍን ተከሎ በመጪዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ በይፋ ድምፃቸውን ይሰጣሉ።
አውስትራሊያውያን የ2017 የኡሉሩ መግለጫ ከልብ ቁልፍ ምሰሶ የሆነውን ድምፅ ለፓርላማን በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ለማስፈር ከውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ለማስቻል ፓርላማ ሰኞ ጁን 19 ሕዝበ ውሳኔው ከመከናወኑ በፊት ያለውን የመጨረሻውን መሰናክል ተሻግሯል።
የ'ይሁን' ዘመቻ አካሂያጆች "የፓርላማ ተግባር ተከናወነ" ሲሉ ገልጠዋል። ቀጣዩ ለሕገ መንግሥታዊ ለውጥ ትግበራው በደጋፊ አባላት ግንዛቤ ማስጨበጡን ማካሄድ ነው።
የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሚኒስትር ሊንዳ በርኒ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅናን ለመላበስና "ይህችን ታላቅ አገር ይበልጥ ትልቅ ለማድረግ "ወደ ፊት ተራምደን "አንድ እርምጃ ተቃርበናል"
"ስንዱ ሆኗል ... ዛሬ፤ የፖለቲካ ሙግቱ አክትሟል። ዛሬ፤ በማኅበረሰብ ደረጃ ብሔራዊ ንግግር መጀመር እንችላለን" ብለዋል።
"ለረጅም ጊዜያት፣ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ካልሆኑት ይበልጥ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች በተከታታይ የከፋ ሁኔታ ገጥሟቸዋል ... ሥርዓቱ ያልተቃና ነው። እናም ለማቃናት ድምፅ ለፓርላማ የእኛ ማለፊያ ዕድል። ስለምን ቢሉ፤ በየቀዬው ሰዎችን ስናደምጥ፣ ከአካባቢ ሰዎች ጋር ስንመክር፣ ማለፊያ ውሳኔዎችን ከመወሰን ላይ ይደርሳሉ፤ መልካም ውጤትም ያስገኛል" ሲሉ አክለዋል።
ሌበር ፓርቲ ድምፅ ለፓርላማ፤ አውስትራሊያውያን ነባር ዜጎች ፓርላማውንና መንግሥትን በተለይ እንዱን በሚያውኳቸው ጉዳዮች ላይ ምክረ ሃሳባቸውን ለመቸር አጋጣሚን የሚቸራቸው ንፁህ አማካሪ አካል ነው ሲል አፅንዖት ሰጥቶበታል።
ይሁንና የተወሰኑ ተቺዎቹ ግና ዕሳቤው ለአደጋ አጋላጭ ነው ሲሉ፤ ሌሎች በፊናቸው ከቶውንም ለነባር ዜጎች በቂ ስልጣንን አይቸርም ባይ ናቸው።
ከሩብ ክፍለ ዘመን ወዲህ የሚካሔደው ሕዝበ ውሳኔ ከሰኞ ጁን 19 አንስቶ ባሉት ከሁለት እስከ ስድስት ወራት ጊዜያት ውስጥ ግብር ላይ ይውላል። ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ በእዚህ ዓመት እንደሚካሔድ ፍንጭ ሰጥተዋል።
"ይህ በሕይወት ዘመን ውስጥ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚገጥም ዕድል አገራችንን ከቶውንም ወደ ላቀ ከፍታ የሚያደርስ ነው" ብለዋል።

Independent Senator Lidia Thorpe reacts after the passing of the Voice to Parliament in the Senate chamber at Parliament House. Credit: AAP / Lukas Coch
"ይህ ነገሮችን ለአውስትራሊያውያን ነባር ዜጎች ከማድረግ ይልቅ፤ ከአውስትራሊያውያን ነባር ዜጎች ጋር በተሻለ ሁኔታ ለመከወን የሚያስችል አጋጣሚ ነው" እንደሆነ አያይዘው ተናግረዋል።
የሊብራል ናሽናልስ ቅንጅት የሕዝበ ውሳኔ ድንጋጌውን አሌ እያለ ነው
ድምፅ ለፓርላማ ከመቃወም ባሻገር ቅንጅቱ ድንጋጌውን አሌ ብሏል።
የሊብራል ፓርቲ ምክር ቤት አባል ሚካኢላ ካሽ የ 'ይሁን' ድምፅ የአውስትራሊያን ሕገ መንግሥት "ለማይሻር ለውጥ" ይዳርጋል ሲሉ የተሟገቱ ሲሆን፤ ሌበር ድምፅ ለፓርላማ ምን ያህል "ከፋፋይ" አካል እንደሆነና በቂ ዝርዝርም ማቅረብ ተስኖታል ብለዋል።
"[ሆኖም] እኛ በእዚህች አገር ሰዎች አመኔታ አለን፤ በጉዳዮች ላይ ድምፃቸውን የማሰማት መብት አላቸው ብለን እናምናለን"
"የሚታወቅ አይደልም። ከፋፋይና ቋሚም ነው። ድምፅ ለፓርላማ እንደምን እንደሚሠራ ካላወቃችሁ፤ የእኔ ትሁት አተያይ 'አይሁን ' ብላችሁ ድምፃችሁን ስጡ ነው" ብለዋል።
የቅንጅቱ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ቃል አቀባይ ጃሲንታ ፕራይስ፤ የዋርልፒሪ/ሴልቲክ ሴት፤ ከሕዝበ ውሳኔው በኋላ ፓርላማው ዝርዝሩን እንዲያወጣ መተው በክስ ለተመላ አደጋ ተጋላጭነት እንደሚዳርግ ተሟግተዋል።
"ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንም ዓይነት ዋስትና መስጠት ተስኗቸው ሳለ፤ በጭፍን እንድናምናቸው፣ የእሳቸው ባዶ ቼክ ላይ በመፈረም አደጋ የተመላበት ዕሳቢያቸው ሕገ መንግሥት ላይ እንዲሠፍር ይሻሉ" ብለዋል።
በቁትር የተወሰኑ የቅንጅቱ አባላት ድንጋጌውን ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል። ያም ቴክኒካዊ በሆነ መልኩ በይፋ ለመራጮች በሚሰራጨው የ'አይሁን' ሕዝበ ውሳኔ በራሪ ወረቀት ላይ አስተዋፅዖ ለማድረግ ያስችላቸዋል።
ግሪንስ ፓርቲ 'እውነተኛ ታሪካዊ ቀን' ሲል ተቀብሎታል
የቃል ኪዳን ውልና እውነት አቋማቸውን ያሻሻሉት የግሪንስ የአውስትራሊያ ነባር ዚጎች ቃል አቀባይ ዶሪንዳ ኮክስ "እውነተኛ ታሪካዊ ቀን" ለአውስትራሊያውያን ነባር ዜጎች በማለት ተናግረዋል።
"የፓርላማ ሥራ ተከውኗል። ወቅቱ ለ 'ይሁን ' ሠፊ ደጋፊ ደጋፊዎች ወደ ማኅበረሰቡ ዘልቀው ለሁሉም አውስትራሊያውያን ይህ ሕዝበ ውሳኔ ጠቀሜታው ምን ያህል እንደሆነ፣ ድምፅ ለፓርላማ ጠቀሜታው ምን እንደሆነ የሚያጋሩበት ነው።" ሲሉ ገልጠዋል።

Ms Burney, seated left, was present for the debate. Credit: AAP / Lukas Coch
ሴናተር ኮክስ ድምፅ ለፓርላማ የነባር ዜጎችን ሉዓላዊነት የሚያሳንስ አይደለም በማለት ሲናገሩ ከግሪንስ ፓርቲ ራሳቸውን በማግለለ ነፃ ሆነው በድምፅ ለፓርላማ ላይ ዘመቻ ለማካሔድ የግል ተወካይ የሆኑት ሴናተር ሊዲያ ቶርፕ ደጋግመው ንግግራቸውን አቋርጠዋቸዋል።
በተደጋጋሚም "ያረጋግጡት" ሲሉ ተናግረዋል።
ሊዲያ ቶርፕ 'የሐሰትና አስመሳይ' ድምፅን አክርረው ተቹ
ሴናተር ቶርፕ፣ የጃብውራንግ፣ ጉናይ እና ጋንዲቲጅማራ ሴት በዕለቱ "የማዋሃጃ ቀን' በማለት አውስትራሊያውያን ሕዝበ ውሳኔው ላይ ድምፀ ተአቅቦ እንዲያደርጉ አበረታተዋል።
ለመናገር ተነስተው ሳለም ድንጋጌውን "በመቃብር ሳጥን ላይ የመጨረሻው ምስማር" ሲሉ ገልጠውታል። ሆኖም በሕዝበ ውሳኔው ዕለት በየትኛው መንገድ ድምፃቸውን እንደሚሰጡ ሲናገሩም፤
"ለእዚህ አንዳችም ስልጣን ለማይቸረን አውዳሚ ሃሳብ ድምፄን የምሰጠው 'አይሁን' ስል ነው።"
"ለሕዝቤ ስልጣን ለማይቸር ነገር ድጋፌን አልሰጥም። በማንኛውም ስልጣን ላይ ተለይተው ለሚመረጡ ድጋፌን አልቸርም" ብለዋል።

Minister for Indigenous Australians Linda Burney poses for a photo with 40 members of Jawun at Parliament House in Canberra. Credit: AAP / Mick Tsikas
"አዎን እዚህ ያለሁት ዋሻዎቹን ላንቀጠቅጥ፣ ይህ ሥፍራ የሚወክለውን የነጭ የበላይነት ላጠፋ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
የምክር ቤት ክርክሩ በሚካሔድበት ወቅት 'ሐሰት' የሚል ቃል የሠፈረበትን ካኔቴራ የለበሱት ሴናተር ቶርፕ ፓርላማው የአነባር ዜጎች የእሥር ቤት ሞቶች ሮያል ኮሚችን ያሳለፋቸውን ምክረ ሃሳቦች ግብር ላይ እንዲያውላቸው ጠይቀዋል።

Independent senator Lidia Thorpe reacts during a debate on the Voice to Parliament in the Senate chamber at Parliament House. Credit: AAP / Lukas Coch
"ይህ እንደምን ሕይወታችንን እንደሚያቃና እኒህን ሁሉ ውብ፣ ልብ ነኪ ታሪኮች እየሰማን ነው። ሁሉንም ነገሮች እንደሚፈታ። ሌላው ቀርቶ ሕዝበ ውሳኔው እስከሚከናወን ድረስ እንኳ ምንም ነገር ማድረግ አንችልም ... በእዚህ ወቅት፤ ልጆች እሥር ቤቶች ውስጥ ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው" ብለዋል።
ክርክርሩ በተካሔደበት ዕለት የሌበሯ ማላርንዲሪ ማክካርቲ አውስትራሊያውያን "ለተሻለ መፃዒ ዕድል" የይሁንታ ድምፃቸውን እንዲሰጡ ጠይቀዋል። አክለውም፤ ይህ ማለት ለነባር ዜጎች "ሁነኛ ነገር ነው"
"[ነባር ዜጎች] በእዚህ ወቅት በአገራችን ታሪክ ለመኩራት፣ አንዳችን አንዳችንን ከፍ ለማድረግ እጆቻቸውን ለሁሉም አውስትራሊያውያን ዘርግተዋል።"
"ነባር ዜጎች የሙሉዕ ድርና ማጉ አካል መሆን እንደሚችሉና ያም ስሜት እንዲያድርባቸው" ብለዋል።
ፓሊን ሃንሰን ከተናገሩ በኋላ የክርክር ድምፀት አሳሳቢነት
የዋን ኔሽን ሴናተር ፖሊን ሃንሰን አውስትራሊያውያን የተሰረቁት ትውልዶች ክስተት ስለምን እንደተከሰተ አውስትራሊያውያን "ለምን ብለው እንዲጠይቁ" ከተናገሩ በኋላ ሲናተር ማክካርቲ በመጪዎቹ ወራት የሚካሔዱ ክርክሮች ድምፀት የሚያሳስባቸው መሆኑን ገልጠዋል።
ሴናተር ማክካርቲ አውስትራሊያውያን ክርክር በሚካሔድበት ወቅት “ተራሳችሁን መልካም ጎን አድምጡ"
“እኔ በመጠኑ ስጋት ገብቶኛል፤ እየተካሔደ ያለውን አተያይ ሳደምጥ” ብለዋል።

Senator McCarthy conceded concern over the tenor of the debate just moments after Pauline Hanson's (pictured) comments. Credit: AAP / Lukas Coch
“ያኔ ነው እንደ አገር የራሳችንን መልካም ጎን ፈልገን የምናገኘው፤ እንደ አውስትራሊያውያን ማለፊያ ጎናችንን” ብለዋል።
ሴናተር ሃንሰን ቀደም ብለው የተሰረቁት ትውልዶች ባይገለሉ ኖሮ "ለትድግና ባልበቁ ነበር" ሲሉ ተናግረዋል።
“እንደምታውቁት፣ ስለ ተሰረቁት ትውልዶች ትናገራላችሁ። በእዚያን ወቅት ሆኗል። ለምን ስትሉ ራሳችሁን ጠይቁ” ብለዋል።
ዝርዝር የተመላበት የ1997ቱ ወደ ቤታቸው መልሷቸው ሪፖርት የናባር ዜጎች ሕፃናትን ከወላጆቻቸው መነጠል የጅምላ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንደሆነ አመላክቷል፤ ተነጥለው የተወሰዱ ልጆች ዝርያዎች በአብዛኛው ለእሥር መዳረግ፣ በጤና ጉዳዮች መታወክ እንደሚያገኛቸውና ሥር ፈልጎ የመግኘት ዕድላቸውም አናሳ መሆኑን አስፍሯል።
አቶ አልባኒዚ የሲናተር ሃንሰንን አተያዮች እንዳልተመለከቱ ገልጠው፤ ሆኖም ቀደም ሲል ሲሏቸው ከነበሩት ነገሮች ተመሳሳይነት እንደሚኖራቸው የሚገምቱ መሆኑን ተናግረዋል።
“ምላሽ ልስጣቸው አልዳዳም፤ ስለምን ጠቅላይ ሚኒስትራዊ ምላሽ ይገባቸዋል ብዬ አልስብም። ከዳር እስከ ዳር መከባበር የሰፈነበት ክርክር እንዲካሔድ ጥሪ አቀርባለሁ”
“በየትኛውም መንገድ ይሁን ሰዎች ድምፃቸውን ይሰጣሉ፣ ቀስቃሾች በተቻላቸው መጠን እውነታ ላይ መመርኮዝ ይገባቸዋል፤ እውነት ያልሆኑ ነገሮችን እያወቁ መናገር አይኖርባቸውም” ብለዋል።
ሊንዳ በርኒ ድምፅ ለፓርላማ መዋቅራዊ ለውጥን ያመጣል አሉ
ሕዝበ ውሳኔዎች የሚያልፉት እጥፍ አብላጫ፤ ሁሉን አቀፍ አብላጫና የክፍለ አገራት አብላጫ ድምፅ በሚባለው ነው። የኖርዘርን ቴሪቶሪና የአውስትራሊያ መዲና ግዛት በክፍለ አገራት የአብላጫ ድምፅ ቆጠራ ውስጥ አይካተቱም።
የግል ተመራጭ ሴናተር ዴቪድ ፖኮክ የአውስትራሊያ መዲና ግዛትና ሰሜናዊ ግዛት እኩል ድምፅ እንደሌላቸው አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ሴናተር ፖኮክ የቅንጅቱ ሕዝበ ውሳኔውን "የካንብራ ድምፅ" አስመስሎ መግለጥ "ግልፅ ቅጥፈት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
"ይህ በአውስትራሊያ ታሪክ ውስጥ አንዱ በእጅጉ ምክክር የተካሔደብት ውጤት ነው ... እውነት ነው፤ ካልተሰበረ፤ አትጠግነው። ግና ከተሰበረ ጥገናን ይሻል። ይህ የተሰበረውን ለመጠገን አንድ ዕድል ነው" ብለዋል።
በዚህ ዓመት አውስትራሊያውያን ሕገ መንግሥቱን በዘላቂነት በመለወጥ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎችን በሚያውኩ ጉዳዮች ላይ ለፌዴራል መንግሥቱ ምክረ ሃሳቦችን የሚያቀርብ ቋሚ ገለልተኛ አካል በቋሚነት እንዲቋቋም በሕዝበ ውሳኔ 'ይሁን' ወይም 'አይሁን' በሚል ድምፃቸውን እንዲሰጡ ይጠየቃሉ።
የሞዴሉ አቀራረፅና ዝርዝሮች ሕዝበ ውሳኔው ስኬታማ ከሆነ በምክር ቤት አባላት የሚቀረፅ ይሆናል።
ወ/ሮ በርኒ ዕሳቤው የጤናና ማኅበራዊ ምጣኔ ጉስቁልና ገጥሟቸው ላሉቱና ለአጭር የሕይወት ዘመን ለተዳረጉቱ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎችን ዒላማ ያደረገ እልባት ሰጪ ማበጀት አስፈላጊ እንደሁ አመላክተዋል።
በነባር ዜጎችና ነባር ዜጎች ባልሆኑ አውስትራሊያውያን መካከል በጤና፣ ማኅበራዊና ደህንነት በኩል ያሉ ክፍተቶችን የማጥበብ ዒላማዎች የሚከታተሉት መለኪያዎች ባለፈው ሳምንት ይፋ በሆኑበት ወቅት ያሳዩት መገኘታቸውን ነው።
"መዋቅራዊ ለውጦችን ያመጣል፤ እንደ ክፍተትን የማጥበብ ጉዳዮች መዘውር ያንቀሳቅሳል"
"ስልጣኑ የሚያርፈው መርሆዎቹ ላይ ነው፤ ከመነሻው በእጅጉ የላቀ የሞራል ስልጣን አለው። ስለ መርሆዎቹ ያስቡ፤ ገለልተኛ ይሆናል፣ ለፓርላማ ብቻ ሳይሆን [የፌዴራል] መንግሥትንም አክሎ ገለልተኛ ምክረ ሃሳብን ይቸራል"
"ተጠያቂነት ይኖረበታል። ሚዛናዊ፣ ማኅበረሰብ መር እና አሁን ባሉት መዋቅሮችና ድርጅቶች ውስጥ ታቅፎ የሚፀና ይሆናል" ብለዋል።
'ቢሮክራሲው ይከላ'
የናሽናልስ ፓርቲ መሪ፤ ዲቪድ ሊትልፕራውድ ባለፈው ዓመት ወርኃ ኖቬምበር ፓርቲያቸው ድምፅ ለፓርላማን አስመልክቶ ለ 'አይሁን ' ዘመቻ እንደሚያካሂድ ይፋ አድርገዋል።
በዚያን ወቅት ዕሳቤው "ስለ እውነት ክፍተትን ያጠባል" ብለው እንደማያስቡ ተናግረዋል።
እስካሁንም ያንኑ አቋማቸውን ይዘው ያሉ መሆኑንና መፍትሔው ድምፅ ለፓርላማ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ መሥፈርን እንደማይሻ አመላክተዋል።
"መንግሥታት ለእዚህ ችግር [ክፍተትን ለማጥበብ] መፍትሔ ለማበጀት ቢሊየን ዶላሮችን በማፍሰስ ሞክረዋል፤ ይሁንና የከወንነው በተሳሳተ መንገድ ነው።"
"የእኩልነት አዝማሚያው ሁሌም እዚያ አለ፤ የአፈፃፃም ጉዳይ እንጂ" በማለት ባለፉት 12 ዓመታት ፓርቲያቸው በቅንጅቱ መንግሥትነት በክሽፈት አቀራረቡ የችግሩ አካል መሆኑን አምነዋል።
"ክሽፈናል። ሁሉም ዓይነት መንግሥታት ከሽፈዋል ለማለት አልፈራም ... ቢሮክራሲውን ከከላን ክፍተቱን እናጠባለን" ሲሉ ለኤቢሲ ራዲዮ ተናግረዋል።
መፍትሔዎቹ ያለ ድምፅ ለፓርላማ የሚያጠነጥኑት በማሕበረሰብ ደረጃ እንደሆነም ገልጠዋል።
"የአረጋውያን ወሳኝና ተሳታፊ መሆን የሚያሻው በአካባቢ ማኅበረሰብ ደረጃ እንጂ በቀጣና ደረጃ አይደለም ... ይህ ቢሮክራቶችን ከካንብራ አስወጥቶ በቀበሌ አዳራሾችና በእሳት መሞቂያ ዙሪያዎች ተገኝተው አረጋውያንን እንዲያደምጡ ማድረግ ነው" ብለዋል።