አውስትራሊያ ውስጥ የኮቨድ - 19 ክትባትን እንደምን ማግኘት ይችላሉ?

የአውስትራሊያ ኮቨድ-19 ክትባት ስርጭት በሂደት ላይ ነው። መቼና የት ክትባትዎን ለመከተብ መመዝገብ እንደሚችሉ ለመረዳት ይህን መጣጥፍ ያንብቡ።

Descartan dosis de vacunas COVID-19 por fallas de refrigeración.

Source: Getty Images/Larisa Bozhikova

የአውስትራሊያ ኮቪድ-19 ክትባት የአገር አቀፍ ትግበራ እቅድ   ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች እና በአገር አቀፍ ደርጃ የተመረጡ ስፍራዎችን እንዲሁም ክትባቱ የት ሊሰጥ እንደሚገባ ለይቶ ያስቀምጣል ፡፡በዚህም መሰረት በጤና ተቋማት የሚሰሩ ባለሙያዎች ፤ በለይቶ ማቆያ ስፍራ እና በድንበር አካባቢ የሚሰሩ እንዲሁም በአረጋውያን መጦርያ እና በአካል ጉዳተኞች እንክብካቤ መስጫ ተቋማት የሚሰሩ ባለሙያዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ናቸው ፡፡

የኮቨድ-19 ክትባት ቀጠሮ ለመያዝ የት መመዝገብ እንዳለብዎት ለመረዳት  ይጎብኙ።

እዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉትን ደረጃ በደረጃ በመከተል ለክትባት መመዘኛውን ያሟሉ እንደሁ ያረጋግጡ፤ 

ዕድሜዎ 18 ወይም ከዚያ በላይ ሆኖ መመዘኛውን ገና ያላሟሉ ከሆነ፤ መመዘኛውን በሚያሟሉበት ወቅት እንዲያስታውቁዎ ይጠይቁ። 

አውስትራሊያ ውስጥ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ለመከተብ መመዘኛውን ገና አላሟሉም። 

ቀጠሮዎን በጠቅላላ ሐኪምዎ በኩል ማስያዝና ስለ ክትባቱ በቋንቋዎ መረጃን ማግኘት ይችላሉ፤ 

ይሁንታን ያገኙ ክትባቶች የትኞቹ ናቸው?

በክትባት ላይ የአውስትራሊያ ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን [ATAGI] ምክረ ሃሳብ መሠረት የፋይዘር ኮቨድ-19 ክትባት ዕድሜያቸው ከ 60 በታች ላሉ ቅድሚያ ይሰጣል። 

የአስትራዜኔካ ክትባት ዕድሜያቸው 60 እና ከዚያ በላይ ለሆኑት በቀዳሚነት ይሰጣል። ይሁንና፤ ዕድሜዎ ከ18 እስከ 59 ከሆነ ከሐኪምዎ ጋር መክረው ይሁንታዎን ከቸሩ የአስትራዜኒካ ክትባትን መከተብ ይችላሉ።

ከሴፕተምበር ጀምሮ ግብር ላይ የሚውለው ሞደርና ክትባት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ እንዲከተቡት በጊዜያዊነት ተፈቅዷል። 
Coronavirus vaccine priority population
Source: SBS
በባህል እና ቋንቋ ዝንቅ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን የተመለከት የክትባእቅድ

የአውስትራሊያ መንግስት  በተግባር የሚያውለው ትግበራ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን የታቀድ ሲሆን በቋንቋ ፤በዘር እና ባህል ዝንቅ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን culturally, ethnically and linguistically diverse (CALD) ታሪክ ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው ፡፡

ክትባቱን የሚያዳርሱት ባለሙያዎችም እንዲሁ በየአካባቢዎቻቸው ከማህበርስብ ድርጅት ተቋማት እና መሪዎቻቸው ጋር  መስራት የሚኖርባቸው ሲሆን ክሊኒኮቹም ባህልን ባገናዘበ መልኩ መስራታቸውን ማረጋገጥ አላባቸው ፡፡ ይህንንም በተግባር ለማሳየት በእቅዱ ውስጥ ፤ በዘር እና ባህል ዝንቅ ከሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የወጡ የድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎችን በክትባት ጣቢያ ክሊኒኮች አካቷል፡፡

የዝንቅ ባህል የህብረተሰብ ሰራተኞች ፤ ከአንድ በላይ ቋንቋ የሚናገሩ ባለሙያዎች እና አስተርጓሚዎች መረጃዎችን በአግባቡ በማዳረስ ሰዎች የሁለተኛውን ዙር ክትባት እንዲወስዱ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው ፡፡ 
Coronavirus vaccine priority population
Source: SBS
የወሰዱት ክትባት በህብረተሰብ መዝገብ ማህደር ውስጥ ይቀመጣል

መንግስት ክትባቱን የወሰዱ ግለሰቦችን የተወስኑ መረጃዎች  የሚያስቀምጥ ሲሆን ይህም የሚሆነው የተከተቡ ሰዎችን ዝርዘር ለይቶ ለማወቅ እንዲቻል ነው ፡፡የአውስትራሊያውያን የክትባት ፕሮግራም አቅራቢዎች እያንዳንዱን የኮቪድ -19 ክትባትን ከሰጡ በኋላ መረጃውን በማህደር ዘግበው የማስቀመጥ ግዴታ አለባቸው ፡፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ የክትባት መረጃ እና ሁኔታ የእኔ ጤና ማህደር  ፤ ሜዲኬር ( ቀድሞ የተወሰዱ የክትባት አይነቶች ዝርዝር ) ወይም ክትባቱን በወሰዱ ጊዜ የተሰጡ የማረጋገጫ ሰርተፊኬት ፤ በማስከተልም የኤሌክትሮሪክ ግልባጭ በኢሜል  መቅረብ አለበት ፡፡

ሁሉም የኮቪድ-19ክትባቶች የሚሰጡት በነጻ ነው

ክትባቱ ለሁሉም የአውስትራሊያ ዜጎች ፤ ቋሚ ነዋሪዎች እና የሁሉም አይነት ቪዛ ላላቸው ሁሉ በነጻ የሚሰጥ ነው ፡፡ በአውስትራሊያ የሚኖሩ ተማሪዎች ፤ የጊዜያዊ ቪዛ ባለቤቶች ፤ የሰብአዊ ፤ የክልላዊ ፤ የመሸጋገሪያ ፤እንዲሁም የልዩ ቪዛ ባለቤቶች ሁሉ የኮቪድ -19 ነጻ ክትባትን ማግኘት ይችላሉ ፡፡

የመኖሪያ ቪዛ የተከለከሉ እና በማገቻ ቤቶች ውስጥ ያሉ ግለሰቦችም እንዲሁ ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ ፡፡


ኮሮናቫይረስን በተመለከት መረጃዎችን በቋንቋዎ ያግኙ ፦

የመንግስት የኮሮናቫይረስ መረጃዎች

  • የጤና ዲፓርትመንት _ ኮቪድ19 የክትባት መረጃዎች በቋንቋዎ  .
  • ዲፓርትመንት ኦፍ ሆም አፌር የኮቪድ -19 የኮቪድ19 መረጃዎች .  

 

  • በአውስትራሊያ የሚኖሩ ሰዎች በመካከላቸው የ 1.5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ ይኖርባቸዋል
  • የጉንፋን ምልክቶችን ካሳዩ በቤትዎ ይቆዩ ከዚያም ምርመራ የሚያደርጉበትን መንገድ ያመቻቹ
 






The Australian Technical Advisory Group on Immunisation (ATAGI) advises the  (Comirnaty) vaccine will be prioritised for people under 60 years of age.

The  vaccine will be prioritised for people aged 60 years and over.  However, if you are aged 18-59 you can choose to receive the AstraZeneca vaccine after consulting your health professional and providing consent.

The vaccine has been provisionally approved for Australians aged 18 and over with a rollout expected from September onwards.

The Australian Technical Advisory Group on Immunisation [ATAGI] recommends the COVID-19 Comirnaty (Pfizer) vaccine as the preferred vaccine for those between 16 and 59 years old.

The COVID-19 Vaccine AstraZeneca can also be provided to people aged 18 to 59.

 


Share
Published 25 February 2021 1:20am
Updated 12 August 2021 6:32pm
By SBS/ALC Content
Presented by Martha Tsegaw
Source: SBS


Share this with family and friends