ከሰኞ ጃንዋሪ 4 ጀምሮ የፊት ጭንብልን (ማስክ) ያላደረጉ ሰዎች የ $200 ቅጣት ይጠብቃቸዋል ፡፡ እድሜያቸው ከ12 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች የማድረግ ግዴታ ባይኖርባቸውም ፤ የኒው ሳውዝ ዌልስ ባለስልጣናት ግን ሁሉም ሰው እንዲያደርግ ያበረታታሉ ፡፡
የምግብ ባለሙያዎች እና የካዚኖ ሰራተኞች የፊት ጭንብል (ማስክ) ማድረግ ይኖርባቸዋል ፡፡
በአምልኮ ስፍራዎች ፤ በሰርግ እና በቀብር ስነስርአት ላይ የሚገኙት ሰዎች ቁጥር ከ100 እንዳይበልጥ የተወሰነ ሲሆን በአራት ስኩዬር ሜትሮች ውስጥ አንድ ሰው ብቻ የሚለው ህግ በተግባር ውሏል ፡፡ የምሽት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ዝግ እንዲሆኑ ተደርጓል ፡፡ጂሞች የሚያስተናግዷቸው ስዎች ቁጥር ከ 50 ወደ 30 ዝቅ ብሏል ፡፡
በውጭ የሚደረጉ ክዋኔዎች እና የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች ቁጥር ከ500 እንዳይበልጥ የተወሰነ ሲሆን ፤ የመግቢያ ቲኬቶችን ቆርጠው ፤ ተቀምጠው የሚሳተፉባቸው የቤት ውጭ እንቅስቃሴዎች የታዳሚዎች ቁጥር ከ 2000 እንዳይበልጥ ተወስኗል ፡፡
የሚኖሩበትን ክልል እና ግዛት አዳዲስ መረጃዎች በተመለከተ፦
በአውስትራሊያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ሁሉ በመካከላቸው የ 1.5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ ይኖርባቸዋል ፡፡ በተጨማሪም በጋራ የመሰባሰብ ገደብን በተመለከተ የየክልላቸውን ህግ መመልከት ይኖርባቸዋል ፡፡የብርድ ወይም የጉንፋን ምልክቶችን ካሳዩ ከቤትዎ አይውጡ ፤ ይልቁንም የኮሮናቫይረስ ምርመራን እንዲያደርግልዎ ሀኪምዎ ጋር ይደውሉ ፤ወይም coronavirus Health Information Hotline on 1800 020 080 ወይም በመደወል መጠየቅ ይችላሉ ፡፡