በቪክቶርያ የተጣለው ገደብ እንደሚራዘም ፕሪምየር ዳንኤል አንድሪውስ አስታወቁ ውሳኔው የመጣው ተጨማሪ 12 አዲስ ቁጥር በመመዝገቡ ነው

የቪክቶሪያው ፕሪምየር ዴልታን " ከፍተኛ ፈተና " ሲሉ ገልጸውታል እንዲሁም የወረርሽኙ ስፋት ሲዲኒን ባዳረሰበት መጠን እንዳይሆን ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል ፡፡

20210716001557641478-original.jpg
በቅርቡ ከታየው የቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ  ቪክቶርያ ተጨማሪ 12 አዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር በማስመዝገቧ  የተጣለው ገደብ እንደሚራዘም ፕሪምየር ዳንኤል አንድሪውስ አስታወቁ  ፡፡

“ይህ ገደብ ከነገ እኩለ ለሊት በኋላ አይነሳም ፤ ይህ ሃላፊነት የሚሰማው ሰው የሚያደርገው ተግባር አይደለም “  ሲሉ ለሪፖርተሮች ተናግረዋል

ገደቡ ከማክሰኞ እኩለ ለሊት በኋላ እንዲነሳ እቅድ ተይዞለት ነበር ፡፡ ሚስተር አንድሪውስ የሚቀጥለም ገደብ እስከ መቼ እንደሚዘልቅም ቁርጥ አድርገው  አልተናገሩም ፡፡

“አያይዘውም አስፈላጊ እስከሆነ ደረስ ሊቆይ ይችላል ብለዋል ”

የተመረመሩ ሰዎች ቁጥር ቫይረሱ የታየባቸው አካባቢዎች እና የምርመራ ውጤቶች ገደቡን ለምን ያህል ጊዜ እንደምናራዝም መመሪያ ይሰጡናል ብለዋል ፡፡ አያይዘውም እስከ ማክሰኞ ደረስ  ለምን ያህል ጊዜ የሚለውን ምላሽ ለቪክቶሪያውያን ለማሳወቅ እንደሚችሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡

ቪክቶርያ ወረርሽኙ እንደገና በመታየቱ ሳቢያ ችግሮችን እያሳለፈች ባለችበት ጊዜም ድንበሮች ጠብቆ ማቆየት ሌላኛው ቀጣይ ተግዳሮት መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

በሲድኒ የታየው የቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ እስካልቀነሰ ደረስ ፤ በተለይ በሰሜናዊ አካባቢ ያለው ድንበርን ድህንነቱን ጠብቆ ማቆየት አዳጋች ይሆናል ብለዋል፡፡

“ ማንኛውም ቫይረሱ ያለበት ሰው ወደ ክልላችን አለመምጣቱን እርገጠኛ መሆን አለበት፡፡ ይህ ለሌላ አንድ ቀን ሲሆን ለወደፊቱም በመሰረታዊነት የእኛ ተግዳሮት ነው የሚሆነው  ፡፡ ነገር ግን ማህበረሰቡ በዘላቂነት የራሱን አስተዋጾኦ እንዲወጣ ጥሪያችንን እናቀርባለን ”
የጤና ዲፓርትመንት እንዳረጋገጠውም እስከ ሰኞ ድረስ  በ24  ሰአት ውስጥ 13 አዲስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መመዝገቡን አስታውቋል ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ከሜልጁራ ነው ፡፡

በከተማዋ የታየው የአሁኑ የዴልታ ቫይረስ ወረርሽኝ ሙሉ ለሙሉ  መነሻው ከኒው ሳውዝ ዌልስ ነው፡፡

ከሌላ አገር ወደ ቪክቶርያ በመጣ እና በአሁን ሰአት በለያቶ ማቆያ ባለ ሰው ሳቢያ ተጨማሪ አንድ  የቫይረስ ቁጥርን ያስመዘገበች ሲሆን አጠቃላይ ቁጥሩንም ወደ  81 ከፍ እንዲል አድርጎታል፡፡

በትናንትና እለት የተዘገቡት ፦ 13 አዲስ የተያዙ 1 ከሌላ አገር በመጣ  (በአሁን ሰአት በለያቶ ማቆያ የሚገኝ )

  • 14,758 ሰዎች ክትባቱን ወስደዋል
  • 54, 839 የምርመራ ውጤቶች ተገኝተዋል
ተጨማሪ መረጃ በተከታታ ይወጣል ፦   

— VicGovDH (@VicGovDH) 

በአሁን ሰአትም 15,800 ቀጥተኛ ንክኪ ያላቸው ሰዎች በለይቶ ማቆያ ስፍራ ይገኛሉ፡፡

ሚስተር አንድሪውስ እንደገለጽት “ ዴልታ ቫርያንት “ በከፍተኛ ሁኔታ የሚፈትን ነው” አሁን የታዩት ቁጥሮች የሚያረጋግጡልንም ገደብ ለመጣል እና ለመዝጋት ያደረግነው ውሳኔ ትክክለኛ መሆኑን ነው፡፡

“ ከፍተኛ ወጤትንም  አሳይተናል በሺዎች የሚቆጥሩ የተጠቂዎች ቁጥር እንዳይኖር ለመከላከል ችለናል ”ብለዋል።

ገደብ ለመጣል ባንወስን ኖሮ ልክ እንደ ሲድኒ ሁሉ በብዙ መቶዎች  የሚቆጠሩ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ይኖረን ነበር  ፤ የአጭር ጊዜ ገድብንም አናደርግም ነበር ሁኔታውም የተለይ ይሆን ነበር ፡፡
ከፍተኛ የጤና ኦፊሰር ብሬት ሰተን በበኩላቸው የሰኞው መረጃ ያጠቃለለው ፤ አንደኛው ካርልተን ከጅሎንግ ጋር በኤም ሲ ጂ ባደረገም ግጥሚያ ፤  በሜልጁራ አዲስ የተያዘው ሰው ፤ አራት ከሚስ ፍራንኪ ሬስቶራንት ፤ ሁለት ከትሪኒቲ ግራመር ጋር የተያያዘ ፤  አንድ ከፊሊፕ አይንላን ፤ አንድ ዋላቢስ ከፈረንሳይ የራግቢ ቡድን ጋር በኤሚ ፓርክ ባደረገው ግጥሚያ ወቅት ፤ አንድ በሜልበር ከተማ አካባቢ ከያንግ ኤንድ ጃክሰን ፐብ ጋር በተያያዘ ፤ አንድ ከባካሽ ማርሽ ግራመር እንዲሁም አንድ ከክራፍቲ ስኩዬር ጋር የተያይዘ የቫይረስ ስርጭት ውጤት ነው ሲሉ አስረድተዋል ፡

Remember to check exposure sites daily. The following new Tier 1 exposure sites were recently added online at   . Go online for more. 

— VicGovDH (@VicGovDH) 

በሜልበርን ሰሜን እና ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ 250 የሚሆኑ ለቫይረሱ የተጋለጡ አካባቢዎች ተለየተው የታወቁ ሲሆን ከነዚህም መካከል ሬስቶራንቶች ፤ ካፌዎች ፤ የአካል ብቃት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም በዶንካስተር የሚገኝ አንድ የሼል ነዳጅ ማደያ ይገኙበታል ፡፡

ቁጥራቸው እየጨመረ የመጡ አካባቢዎችን እና ክልከላዎችን በተመለከት መረጃን ከሚከተለው ሊክ ማግኘት ይቻላል ፦ 

ባለፉት 24 ሰአታት 54839 የምርመራ ውጤቶች የተገኙ ሲሆን 14758 ሰዎችም ክትባቱን ወስደዋል ፡፡

ኩዊንስላንድ ፤ ዌስተርን አውስትራሊያ ፤ ሳውዝ አውስትራሊያ እና ታዝማንያ  ድንበራቸውን ለቪክቶርያውያን ዝግ አድርገዋል ፡፡


Share
Published 19 July 2021 9:18am
Updated 20 July 2021 12:28am
Presented by Martha Tsegaw
Source: AAP, SBS


Share this with family and friends