
Source: SBS
- ቪክቶሪያ ፈቃድ ያላቸው ሰራተኞች ክትባትን የግድ መውሰድ እንዳለባቸው አስታወቀች
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ የንግድ ተቋማት የገንዘብ ድጎማን ማግኘታቸው ይቀጥላል ተባለ
- ኩዊንስላንድ ሁለት ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስታወቀች
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,143 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤
ፈቃድ ያላቸው ሰራተኞች በሙሉ በስራቸው ላይ መቀጠል ከፈለጉ፤፤ እስከ ኦክቶበር 15 ድርስ ቢያንስ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ማግኘት አለባቸው ፡፡ በተያያዘም እስከ ኖቬምበር 26 ድረስ ሙሉ ለሙሉ መከተብ ይኖርባቸዋል ፡፡
ከማክሰኞ ኦክቶበር 5 ጀምሮ 25 በመቶ የሚሆኑት የግንባታ ሰራ ባላሙያዎች ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሳሉ ፡፡ ይሁንና ሰራተኞቹ ቢያንስ አንዱን ዙር ክትባት መውሰድ አለባቸው ፡፡
የሞራቦል ሎካል ገቨርንመንት አካባቢ ከዛሬ እኩለ ለሊት በኋላ ለሰባት ቀናት በሚቆይ ገደብ ውስጥ ይቆያሉ ፡፡
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 864 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን 15 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
አቃቤ ነዋይ ዶምኒክ ፔሮቴት እንዳረጋገጡት ከሆነ የንግድ ተቋማት የተቀመጠውን መስፈርት እስካሟሉ ድረስ የገንዘብ ድጎማን እስከ ኖቬምበር 30 ድረስ ያገኛሉ ፡፡
ለጥቃቅን የንግድ ተቋማት የሚሰጠው የገንዘብ ድጎማም የሚቀጥል ሲሆን ትርፋቸው ከ $75,000 በታች ለሆኑት ተቋማት ድጎማው ቀንሶ በሁለት ሳምንት ወደ $750 ዝቅ ይላል ፡፡
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 53 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተያዙ ሲሆን የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከፍተኛ ሚኒስትር አንድው ባር እንዳሉት 40 በመቶ የሚሆኑ እና መከተብ የሚገባቸው የክንብራ ነዋሪዎች ክትባቱን አልወሰዱም ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኛዎች ከ 40 አመት በታች ናቸው፡፡
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤