- ሜልበርን ላይ ተጥለው ያሉ ገደቦች ዛሬ ከምሽቱ 11:59PM ላይ ይረግባሉ
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ለንግድ ማቋቋሚያ ተጨማሪ ድጋፍ ልታደርግ ነው
- ኩዊንስላንድ ግዙፍ 'ልዕለ ቅዳሜ' የክትባት ዘመቻ መሰናዶዋን አስታወቀች
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ውስጥ 2,232 በኮቪድ-19 ተጠቁ፤ 12 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ሜልበርን ላይ ተጥሎ ያለው ስድስተኛ ዙር ገደብ ማምሻውን 11:59PM ያከትማል።
ቪክቶሪያ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለዓለም አቀፍ መንገደኞች የቤት ውስጥ ወሸባ ሙከራዋን ትጀምራለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ቪክቶሪያ የ70 ፐርሰንት ዒላማዋን መምታቷን አስመልክተው ሲናገሩ፤
“ረጅሙ ጉዞ ቪክቶሪያ ውስጥ ተከውኗል፤ ያ ረጅም መንገድ ዛሬ ምሽት ክፍት መሆን ይጀምራል" ብለዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 372 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። የአንድ ግለሰብ ሕይወት አለፈ።
የክፍለ አገሩ መንግሥት ለቱሪዝምና ኩነት መስክ የ$530 ሚሊየን ዶላርስ መመደቡን ካስታወቀ በኋላ ተጨማሪ ለምጣኔ ሃብት ማገገሚያ የሚውል ድጎማ እንደሚኖርም ጠቁሟል።
ኩዊንስላንድ
ኩዊንስላንድ አንድ በዚህ ወር መጀመሪያ ሜልበርን የነበረ የኡበር ሾፌር በቫይረስ መጠቃቱን አስመዘገበች።
ዋና የጤና መኮንን ጃኔት ያንግ እንደገለጡት በ30ዎቹ ያለው ሾፌር በጣሙን የታመመ በመሆኑ በቂ መረጃን ከግለሰቡ ማግኘት አዋኪ ሆኗል።
በሌላ በኩል፤ ኩዊንስላንድ ወሰኗን ዲሴምበር 17 ከመክፈቷ በፊት በ100 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ግዙፍ የሆነ የ'ልዕለ ቅዳሜ' ክትባት ታከናውናለች።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 28 ሰዎች በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን በጠቅላላው 425 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ከመዲናይቱ ነዋሪዎች 80 ፐርሰንቱ ሙሉ ክትባት መከተብ ጋር ተያይዞ ዛሬ ማምሻውን ተጨማሪ ገደቦች ይነሳሉ።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ታዝማኒያ ዛሬ የ70 ፐርሰንት ዒላማዋን መትታለች።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤