የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ በኮቪድ - 19 ሳቢያ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ

*** ቪክቶሪያ ውስጥ 11 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲጠቁ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 141 በቫይረሱ ተይዘዋል

NSW Premier Gladys Berejiklian

NSW Premier Gladys Berejiklian looks on during a COVID-19 update and press conference in Sydney, Sunday, July 25, 2021. Source: AAP


  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ በኮቪድ-19 ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን አስመዘገበች  
  • ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረሱ የተያዙት ሁሉም ሰዎች ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው 
  • የፌዴራል መንግሥቱ ተጨማሪ 85 ሚሊየን ፋይዘር ክትባቶችን ሸመተ
  • ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ ተጥሎ ያለው ገደብ ለመነሳት ተቃርቧል
     

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 141 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መጠቃታቸውንና አንዲት የ70 ዓመትና አንዲት በ30ዎቹ ውስጥ ያለች ሴት ሕይወት በቫይረሱ ሳቢያ ማለፉን እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን አስታወቁ።  

ኒው ሳዝ ዌይልስ ተጨማሪ 50,000 የኮቪድ-19 ፋይዘር ክትባቶች ተመድበውላታል። በሌላም በኩል በትናንትናው ዕለት ሲድኒ ውስጥ በተካሔደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ሰልፈኞችን የሚለይ አንድ ልዩ የፖሊስ ቡድን ተቋቁሟል፤ እንዲሁም 510 የመቀጮ ማዘዣዎች ወጥተዋል።  

ቫይረሱ ተሰራጭቶ ያለባቸውን አካባቢዎች ዝርዝር ወይም ካርታ እዚህ ይፈልጉ 

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ 11 አዲስ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችን ዛሬ አስመዝግባለች። ሁሉም የቫይረሱ ተጠቂዎች ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው። 

ባለስልጣናት ተጥሎ ያለውን የኮቪድ-19 ገደቦች ማክሰኞ ጁላይ 27 ለማንሳት ገና ከውሳኔ ላይ አልደረሱም። 

ቫይረሱ ተሰራጭቶ ያለባቸውን አካባቢዎች ዝርዝር ወይም ካርታ እዚህ ይፈልጉ 

ባለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • አውስትራሊያ በ2022 እና 2023 85 ሚሊየን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ትረከባለች
  • ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ ተጥሎ ያለው ገደብ ለመነሳት ተቃርቧል  
  • ኩዊንስላንድ ከሆቴል ወሸባ አምስት በቫይረስ ተጠቂዎችን መዝግባለች

የኮቪድ-19 አፈ ታሪክ፤
ጤናማ ወጣቶች በኮቪድ-19 አይጠቁም። ቫይረሱ የሚያጠቃውና የሚገድለው በዕድሜ የገፉና የታመሙን ብቻ ነው።

የኮቪድ-19 መዘርዝረ ጭብጥ፤
ቫይረሱ ፅኑ ሕመም ያለባቸው በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ብርቱ ተፅዕኖዎች አሉት። ሆኖም የተወሰኑ ጤናማ ወጣቶችንም ያጠቃል፤ ይገድላል። 


ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤


ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 

Share

Published

Updated

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends