- አውስትራሊያ ውስጥ የሶተኛ ዙር ኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዕድሜያቸው 16 እና 17 ያሉ ልጆች ቁጥር 8.4 ሚሊየን አለፈ።
- የጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት ሙሉ ክትባት ሶስተኛ ዙር ክትባትን ያካተተ እንዲሆን በአውስትራሊያ የፈዋሽ ቁሶች አስተዳደር ይሁንታን የማግኘቱ ጉዳይ "ከአለመሆኑ ይልቅ መሆኑ" እንደሚያመዝን ተናገሩ።
- የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንቶኒ አልበኒዚ የአረጋውያን ክብካቤ ግልጋሎቶች ሚኒስትር ሪችድ ኮልቤክ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅትን በብቃት አልተወጡም በማለት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠየቁ።
- የአውስትራሊያ ዋና የጤና ኃላፊ ሰዎች የኦሚክሮን ማዕበልን የኮሮናቫይረስ መጨረሻ አድርገው እንዳይመለከቱ አሳሰቡ።
- አክለውም፤ አዲስ የኮቪድ-19 ወረርሽኝና ከ2020 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የጉንፋን ወረርሽኝ እንደሚከሰት አመላክተዋል።
- ምዕራብ አውስትራሊያ ውስጥ ትምህርት ቤቶች በተከፈቱ ጥቂት ቀናት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችና በደርዘኖች የሚቆጠሩ መምህራን ለሁለት ሳምንታት ወሸባ ለመግባት ግድ ተሰኙ። ምዕራብ አውስትራሊያ ውስጥ 19 ስዎች በቫይረስ መያዛቸው ተመዝግቧል።
- ኒውዝላንድ በአምስት ደረጃ ዕቅድ ድንበሮቿን ከፌብሪዋሪ 27 ጀምሮ ትከፍታለች፤ በወርኃ ኦክቶበርም ሙሉ በሙሉ ድንበሮቿ ለዓለም አቀፍ መንገደኞች ክፍት ይሆናሉ።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 12,632 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ360 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 2,578 ሕመማን 1 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ቪክቶሪያ ውስጥ 12,157 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 34 ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 752 ሕመማን 82 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ኩዊንስላንድ 8,643 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 9 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 749 ሕመማን 47 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ደቡብ አውስትራሊያ 1,583 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ 226 ሆስፒታል ይገኛሉ።
ታዝማኒያ፣ ደቡብ አውስትራሊያና ኖርዘን ቴሪቶሪ እያንዳንዳቸው አንድ የሟች ቁጥር አስመዝግበዋል።
የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤
- ከ60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ዜናዎችና መረጃዎች ከ
- የክፍለ አገርዎ ረብ ያላቸው መምሪያዎች , , , , , , .
- ስለ ኮቪድ-19 መረጃ በቋንቋዎ