- ለኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች ተጨማሪ ሁለት ክፍያዎች ይፋ ሆኑ
- በሜልበርን የተጣለው ገደብ ለተጨማሪ ሁለት ሳምንታት ተሸጋገረ
- በኖርዘርን ቴሮቶሪ የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ገደብ ተጣለ
- በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አስራ ዘጠኝ ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ በኩዊንስላንድ ምንም ሰው አልተያዘም
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 478 ነዋሪዎቿ በማህበረሰብ ውስጥ ባለ የኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ፤ ሰባት ሰዎችም ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዎል ፡፡
መንግስት የኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ደርጃ ታይባቸዋል በማለት ለይቶ ባወጣቸው አካባቢ የሚኖሩ እና የኮቪድ -19 ምልክቶችን ላሳዩ ፤ ምርመራን ለሚያደርጉ እና ራሳቸውን ለየተው ማቆየት ለሚጠበቅባቸው እድሜያቸው ከ 17 አመት በላይ ለሆኑ ሁሉ የ $320 ክፍያን ማግኘት ይችላሉ ፡፡
የጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ላላቸው እና ሌሎች የመግስት ክፍያዎችን የማያገኙም የድንገተኛ ጊዜ ክፍያን $400 በቀይ መስቀል አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ ፡፡
ተጨማሪ 530,000 የፋይዘር ክትባቶች በሲድኒ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቅተዋል በተባል 12 አካባቢዎች የሚዳረስ ሲሆን እድሜያቸው ከ 20 እስክ 39 ለሆኑ ነዋሪዎች ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 22 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። ከነዚህ ውስጥ አምስቱ ቀደም ሲል ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎች አይደሉም። እንዲሁም ስምንቱ አስተላልፊ በሆኑበት ወቅት በማህበረሰቡ ውስጥ የቆዩ ናቸው ፡፡
በሜልበርን የተጣለው ገደብ እስከ ሀሙስ ሴፕቴምበር 2 ከምሽቱ 11:59 ድረስ የተሸጋገረ ሲሆን ከዛሬ ከምሽቱ 3:00 የሚጀምር የሰአት እላፊ ገደብም ታውጇል ፡፡
ያለፉት 24 ሰዓታትበአውስትራሊያዙሪያ
- ግሬተር ደርዊን እና ካተሪን ሪጅን በማህበረሰብ ውስጥ የታየ አንድ የኮሮናቫይረስን ተከተሎ ለ72 ሰአት የሚቆይ እና ፈጣን የሚባል ገደብ የተጣለ ሲሆን ፤ ገደቡም በአካባቢያቸው ባለው ሰአት አቆጣጠር ከእኩለቀን ጀምሮ በተግባር የሚውል ነው፡፡
- በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አስራ ዘጠኝ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሲሆን የሁለት ሳምንት ተጨማሪ ገደብም ተጥሏል ፡፡
ወሸባ፣ጉዞ፣የክሊኒክምርመራናየወረርሽኝአደጋክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤