- 1,000 የኒው ሳውዝ ዌይልስ ኮቪድ ሕሙማን ሆስፒታል ውስጥ ይገኛሉ
- ቪክቶሪያ ውስጥ 50,000 የአስትራዜኔካ ክትባትን መከተብ ለሚሹ ዝግጁ ነው
- በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ክፍያ ላስተጓጎሉ ተከራዮችን ጥበቃ የአሥራ ሁለት ሳምንት ድንጋጌ አለፈ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,431 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 12 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን የዴልታ ቀውስ በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ ይበልጡን እንደሚስፋፋ አመላከቱ።
በአሁኑ ወቅት 979 የኮቪድ-19 ሕሙማን ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ከእነሱም ውስጥ 160 ፅኑዕ ሕሙማን ክፍል 63 የአየር መተንፈሻ ተገጥሞላቸው ይገኛሉ። የጤና ባለ ስልጣናት በሚቀጥሉት አሥራ አራት ቀናት የሆስፒታል ሕሙማን ቁጥር እንደሚጨምር ከወዲሁ አሳስበዋል።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 208 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 96ቱ ከታወቁ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሥፍራዎች ናቸው። የአንድ በ60ዎቹ የሚገኝ ግለሰብ ሕይወት አልፏል።
እንደራሴ አንድሩስ ከማክሰኞ ሴፕቴምበር 7 ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ቅድሚያ ተሰጧቸው ክትባት መከተብ እንደሚጀምሩና በቀጣይነትም ዕድሚያቸው 12 ላለ ልጆች የፋይዘር ኮቪድ-19 ክትባት ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 18 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል፤ 15ቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
መንግሥት በገደቦች የተነሳ ገቢያቸውን በማጣት ወይም የሥራ ሰዓታቸው በመቀነሱ ሳቢያ የቤት ኪራያቸውን መክፈል ለተሳናቸው ለአሥራ ሁለት ሳምንታት ኪራያቸው ተቋርጦ ከኪራይ ቤታቸው እንዲወጡ እንዳይደረግ ድንጋጌ አሳለፈ
ያእፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ከሰኞ ሴፕቴምበር 6 አንስቶ ኩዊንስላንድ ውስጥ 680 የሆቴል ወሸባ ክፍሎች ስንዱ ይሆናሉ
- ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ቡድናት ውስጥ አንዱ ቢሆኑም ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ ከሆኑ ነባር ዜጎች እስካሁን መከተብ የቻሉት 20 ፐርሰንት ብቻ ናቸው
- ተጠባባቂ እንደራሴ ጀርሚ ሮክሊፍ ታዝማኒያ ውስጥ የሚገኙ የጤና ክብካቤ ሠራተኞች ላይ ክትባት የመከተብ ግዴታ መጣሉን አስታወቁ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤