የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ እንደራሴ በቤተሰቦች መካከል ግንኙነቶች ውስን እንዲሆኑ አሳሰቡ

*** ቪክቶሪያ ዛሬ ሶስት ሰዎች በቫይረስ የተጠቁባት መሆኑን ገለጠች፤ ሁሉም ወሸባ ውስጥ ያሉ ናቸው።

NSW Premier Gladys Berejiklian

NSW Premier Gladys Berejiklian speaks during a COVID-19 update and press conference on July 30, 2021 in Sydney, Australia. Source: Getty

  • የጤና ድንጋጌዎችን ለማስፈጸም ወታደሮች ከኒው ሳውዝ ዌይልስ ፖሊስ ጋር ሊሰማሩ ነው
  • የቪክቶሪያ ባለስልጣናት መነሻው ያልታወቀ የነበረን ቫይረስ ምንጭ ፈልገው አገኙ
  • አንድ የብሪስበን ትምህርት ቤት ከተማሪዎቹ አንዷ በኮቪድ-19 መያዝ ሳቢያ ለዳር እስከ ዳር ፅዳት ግድ ተሰኘ
  • ታዝማኒያ ወሰኗን ለቪክቶሪያ ክፍት አደረገች

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 170 በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን አስታወቀች፤ 42ቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።

እንደራሴ ግላዲስ በርጀክሊያን የቫይረስ በቤተሰቦች መካከልና ሥራ ቦታዎች ላይ መስፋፋትን ተከትሎ የቤተሰብ ለቤተሰብ ግንኙነት ውስን እንዲሆን አሳሰቡ 

የፖሊስ ኮሚሽነር ማይክ ፉለር  "የተቃውሞ ሰልፈኞች በሺህዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች ይገጥማቸዋል" ሲሉ የፀረ ኮሮናቫይረስ ገደብ ተቃውሞ ሰልፈኞችን አስጠነቀቁ

እንዲሁም፤ 300 የጦር ሠራዊት አባላት ከሰኞ ጀምሮ ገደብ ተጥሎባቸው ያሉ ሰዎች ቤት ውስጥ መሆናቸውንና ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር አለመቀላቀላቸውን ለማረገገጥ ይሰማራሉ

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ዛሬ ሶስት ሰዎች በቫይረስ የተጠቁባት መሆኑን ገልጣለች፤ ሁሉም ወሸባ ውስጥ ያሉ ናቸው። 

የቪክቶሪያ ጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ መነሻው ያልታወቀ የነበረን ቫይረስ ምንጭ መገኘቱን አስታውቀዋል። ሆኖም ግለሰቡ እንደምን በቫይረሱ ሊያዝ እንደቻለ ግልጽ አለመሆኑን ጠቁመዋል።

ወቅታዊ የኮቪድ ጥንቃቄ እርምጃዎችን ከዚህ ያንብቡ .

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • የኩዊንስላንድ ጤና ባለስልጣናት በኮቪድ-19 የተጠቃችው የብሪስበን ተማሪ ከጁላይ 27 ጀምሮ ለሶስት ቀናት ማኅበረሰቡ ውስጥ ስትዘዋወር እንደነበር ገልጠዋል።

  • ታዝማኒያ በቪክቶሪያ ላይ ለሁለት ሳምንታት ዘግታ የነበረውን ወሰኗን ከዛሬ ጀምሮ ክፍት አደረገች

ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤



ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 

Share

Published

Updated

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends