- የሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ ኮሮናቫይረስ ገደብ እስከ ሴፕቴምበር 10 ተራዘመ
- ቪክቶሪያ 25,000 የፋይዘር ክትባቶችን ተቀበለች
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶር የንግድ ድጎማ ተጀመረ
- ኩዊንስላንድ ቱዉምባ አጠገብ የወሸባ ማዕከል ልትገነባ ነው
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,029 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 37 በማኅበረሰብ ውስጥ የተዛመቱ ናቸው። የሶስት ክትባት ያልተከተቡ ሰዎች ሕይወትም አልፏል።
እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ሙሉ ክትባት ለተክተቡ ነዋሪዎች ከሴፕቴምበር 13 ጀምሮ ተጨማሪ ነፃነቶችን አስታውቀዋል፤
- የስጋት ሥፍራዎች ከሆኑ የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ውጪ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ከቤታቸው አምስት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ውስጥ ባሉ ሥፍራዎች ከአምስት ሳይበልጡ መሰባሰብ ይችላሉ
- የስጋት አካባቢ በሆኑ የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ነዋሪ የሆኑ ቤተሰቦችም ከቤታቸው ውጪ መሰባሰብ ይችላሉ፤ ሆኖም የሰዓት ዕላፊና የአካል እንቅስቃሴን አስመልክቶ ያሉ ገደቦችን ማክበር ይጠበቅባቸዋል .
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 80 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 41ዱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
የቪክቶሪያን 25,000 ክትባቶች መቀበል ተከትሎ የኮቪድ ኮማንደር ጄሮን ዌይማር እንዳስታወቁት ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በታች ሆኖ የአስትራዜኔካ ክትባት ቀጠሮ ያላቸው በቀጥታ ያለ ተለዋጭ ቀጠሮ የፋይዘር ኮቪድ-19 ክትባትን መከተብ ይችላሉ።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 14 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን በጠቅላላው 190 ደርሷል።
ንግዳቸው በተጣለ ገደብ የተጎዳባቸውና ሠራተኞችን ቀጥረው የሚያሠሩ የካንብራ ኩባንያዎች እስከ $10,000 ያለ ተቀጣሪ ያሉ ነጋዴዎች እስከ $4,000 ድጎማ ማመልከት ይችላሉ
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ኩዊንስላንድ ቱዉምባ ዌልካምፕ አውሮፕላን ማረፊያ አጠገብ ሪጂናል የወሸባ ማዕከል ልትገነባ ነው
- ኖርዘርን ቴሪቶሪ የሚገኙ ማናቸውም ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች የፋይዘር ኮቪድ-19 ክትባቶችን መከተብ ይችላሉ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤