- ኮውራ ላይ ከዛሬ 5pm ጀምሮ የኮሮናቫይረስ ገደብ ተጣለ
- ቪክቶሪያ ውስጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ ክትባቶች ለተከታቢዎች ዝግጁ ናቸው
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ዕድሜያቸው ከ12-15 ላሉ የፋይዘር ክትባት ቀነ ቀጠሮ ማስያዝ ጀመረች
- ኖርዘርን ቴሪቶሪ ውስጥ አንድ መንገደኛ በኮቪድ ተጠቃ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 935 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። የክትባት መመዘኛዎችን ከሚያሟሉ ነዋሪዎች ውስጥ 52.7 ፐርሰንት ሙሉ ክትባት ተከትበዋል።
ኮውራ ውስጥ አንድ የዘጠኝ ዓመት ልጅ ተያዘ። በርካታ የተጋላጭነት ሥፍራዎች ተመዘገቡ የሪጂናል ከተማዋ ላይ ገደብ የሚጣለው ከዛሬ 5pm አንስቶ ነው።ከሴፕቴምበር 13 ጀምሮ ኮውራ የነበሩ ማናቸውም ሰዎች "የቤት ውስጥ ቆይታ መስፈርቶችን በአስቸኳይ እንዲተገብሩ" ማሳሳቢያ ተሰጥቷል። ከተማይቱ ውስጥ ቫይረሱ እንደምን እንደተከሰተ ለጊዜው አልታወቀም።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ ዳርቶን ከተማ የቁሻሻ ፍሳሽ ውስጥ የቫይረስ ምልክት በምርመራ ተገኝቷል።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 567 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።
እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ 4,800 አስትራዜኔካና ከ2,000 በላይ ፋይዘር ለተከታቢዎች ዝግጁ መሆኑን ገለጡ። በቂ የፋይዘር ክትባት ኦክቶበር ውስጥ ላይኖር እንደሚችል በማመልከት ሰዎች ለጊዜው ዝግጁ ሆኖ ያለውን የክትባት ዓይነት እንዲከተቡ አሳስበዋል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ሰባት ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስመዝግባለች። ዋና ሚኒስትር አንድሩ ባር 55 ፐርሰንት የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች የሁለተኛ ዙር ክትባቶችን መከተባቸውን አስታወቁ።
ዕድሜያቸው ከ 12 እስከ 15 ያሉ ከዛሬ ጀምሮ በመንግሥት በሚካሄዱ ክሊኒኮች ዘንድ የክትባት ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- አንድ ከብሪስበን አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ኖርዘርን ቴሪቶሪ ያረፈ መንገደኛ በቫይረስ የተጠቃ ሆኖ ተገኝቷል።