- በመጪዎቹ ቀናት በኒው ሳውዝ ዌልስ በኮቪድ- 19ሳቢያ የሟቾች ቁጥር እንደሚጨምር የሚጠበቅ ሲሆን ፤ ይህም የሚሆነው በማህበረሰብ መካከል በሚሰራጭ ቫይረስ አማካኝነት መሆኑን ከፍተኛ የጤና ኦፊሰሯ ኬሪ ቻንት አስጠንቅቀዋል ።
- በኒው ሳውዝ ዌልስ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ 17 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ፤ በተያያዥም በሆስፒታል እና ልዩ እንክብካቤ የሚስፈልጋቸው ሰዎች በሚታከሙበት ክፍል የሚቆዩ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ተገልጿል ።
- ዶ / ር ቻንት እንደተናገሩት “ ተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባትን በመውሰድ ፤ መከላከያን ከፍ በማድረግ ኦሚኮርንን መከላከል ግድ ይላል ፤ በሪፖርታቸውም አያይዘው እንደገለጹት ባለፉት ሁለት ቀናት በግል የደም መስጫ ተቋም ከተሰበሰቡት ናሙናዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት የኦሚኮርን ቫርያንት ናቸው ።
- የቪክቶሪያ ከፍተኛ የጤና ኦፊሰር ብሬት ሰተን ፤ ምንም እንኳ በማህበረሰቡ ውስጥ የተዛመተው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቫይረስ ስርጭት ሪፖርት ባይደረግም ፤ ከተማዋ በቅርቡ ሰርጭቱ “ ከፍተኛ ” ደረጃ የሚባልበት ላይ እንደምትደርስ ተናግረዋል ።
- ከኩዊንስላንድ የተገኙት የቁጥር መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ፤ አንድ ያልተከተበ ሰው ሶስቱንም ክትባቶች ከወሰዱት ጋር ሲነጻጸር ፤ ከፍተኛ እንክብካቤ የሚያሻቸው ህሙማን ክፍል ውስጥ የመቆየት እደሉ በ24 እጥፍ ከፍ ያለ ነው ።
- የአውስትራሊያ ተጠቃሚዎች ተቆጣጣሪ እንዳለው የፈጣን መመርመሪ መሳሪያዎቹ ዋጋ በየጊዜው መናር አሳሳቢ መሆኑን ነው ።
- የአውስትራሊያ ተጠቃሚዎች ተቆጣጣሪ ከ 1,800 በላይ አሀዛዊ ሪፖርቶችን የተነተነ ሲሆን ፤ የዋጋ መጨመር የታየው ካለፈው ዲሴምበር 25 ጀምሮ ሲሆን ፤ በአሁን ሰአትም ከ 150 በላይ ሪፖርቶች በየቀኑ ይወጣሉ ።
- ቪክቶሪያ ክትባትን ለማበረታታት 1.2 ሚሊዮን ዶላር ለመድበለ ባህል የማህበረሰብ አባላት የመደበች ሲሆን ፤ ይህውም በስምንት የማህበረሰብ ድርጅቶች አማካኝነት የቋንቋ እርዳታን ለሚሹ ፤ በገበያ ማእከላት እና የክትባት ጣቢያዎች ክትባቱን ለማዳረስ የሚወል ይሆናል ።
- የፌደራል መንግስት በጊዜያዊነት የሚያገለግል የልዩ ሀኪሞች ቴሌ ሄልዝ በስልክ እና ቪዲዮ አገልግሎት የሚያስተዋውቅ ሲሆን ፤ ይህውም የመጀመሪያ እና ውስብስብ ልዩ የስልክ ህክምናን ፣ ረጅም የቤተሰብ ሀኪም ማማከርን የሚያጠቃልል እና እስከ ጁን 30 የሚዘልቅ ነው ።
- ኮቫክ ( COVAX ) የተባለው አለማቀፍ ድርጅት ክትባትን በመጋራት ዙሪያ አንድ ቢሊዮን ክትባቶችን ያዳረስ ቢሆንም ፤ እስከአሁንም ድረስ 40 በመቶ የሚሆነው የአለማችን ህብረተሰብ አልተከተበም ።
- በኒው ሳውዝ ዌልስ 29,504 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል ። በቪክቶሪያ 22, 429 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የስድስት ሰዎች ህይወትም አልፏል ።
- በኩዊንስላንድ 15,122 ስዎች ሲያዙ የ 7 ስዎች ህይወት አልፏል ። በታዝማንያ 1037 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ።
- በአሁን ሰአት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ላይ እየተሰጠ ያለውን ምላሽ በተመለከተ በቋንቋዎ መረጃን ካሹ የሚከትለውን ሊንክ ይጫኑ .
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር ፤
ጉዞ
የአለማቀፍ ጉዞን በተመለከተ መረጃዎችን እና የ ኮቪድ-19 የጉዞ መረጃዎችን በቋንቋዎ ያግኙ
የአለማቀፍ ጉዞን በተመለከተ መረጃዎችን እና የ ኮቪድ-19 የጉዞ መረጃዎችን በቋንቋዎ ያግኙ
የገንዘብ እርዳታ
በየክፍላት ሀገሩ ሙሉ ለሙሉ የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ከ 70 እና 80 በላይ ከሆነ ጀምሮ የክፍለ ሀገሮች የኮቪድ-19 የአደጋ ጊዜ ክፍያ ህጎች ተለውጠዋል።:
- ዜና እና መረጃን ከ60 በላይ ቋንቋዎች ከ ያግኙ
- የየክፍላት ሀገራቱ እና ግዛቶችን ትክክለኛ መመሪያዎች በተመለከት ፦ territory: , , , , , , .
- የኮቪድ-19 ክትባትን በቋንቁዎ መረጃን በተመለከተ ፦
በኒው ሳውዝ ሄልዝ መድብለባህል የጤና ክህለ ተግባቦት አገልግሎት የተተረጎሙ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ ፦
የየክፍላተ ሀገራቱ እና ግዛቶች የመመርመሪያ ክሊኒኮች ዝርዝር ፦