- የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት ኦሚክሮን 'እያሻቀበ' መሆኑን አመላከቱ፤ በመላ አውስትራሊያ ባለፉት 24 ሰዓታት 56 ሰዎች በኮቪድ-19 ሕይወታቸውን አጡ
- ነፃ ፈጣን አንቲጄን መመርመሪያ ለቅናሽ ካርድ ተጠቃሚዎች ከዛሬ ጀምሮ በነፃ ይሰጣል። ከ6 ሚሊየን በላይ የሆኑ ሲቪል ተጠዋሪዎች፣ የወታደር ጡረተኞችና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው በሶስት ወራት ገደብ ለ10 ጊዜ የሚውሉ መመርመሪያዎችን በነፃ ከመድኃኒት ቤቶች ማግኘት ይችላሉ።
- የፌዴራል መንግሥቱ የፈጣን አንቲጄን መመርመሪያ እጥረትን አስመልክቶ አሁንም ድረስ ብርቱ ጥያቄዎች እየቀረቡበት ነው። የጤና ሚኒስትሩ 16 ሚሊየን ፈጣን አንቲጄን መመሪመሪያዎች የታዘዙ መሆኑንና እስከ ወርኃ ጁላይ መጨረሻ ድረስም አውስትራሊያ እንደሚደርሱ ተናግረዋል።
- የኖቫቫክስ ኮቪድ-19 ክትባት አውስትራሊያ ውስጥ ለአዋቂዎች መከተቢያነት እንዲውል ይሁንታን አገኘ። ከፌብሪዋሪ 21 ጀምሮም ጥቅም ላይ ይውላል።
- ኖቫቫክስ ክትባት የሁለት ዙር ክትባት ሲሆን፤ በሶስት ሳምንታት ልዩነት የሚሰጥ ነው።
- የኒው ሳውዝ ዌይልስ የኮቪድ-19 ሆስፒታል ታካሚዎች ቁጥር እሑድ ተመዝግቦ ከነበረው 2,712 ወደ 2,816 ከፍ ብሏል። በሌላ በኩል የቪክቶሪያ የሆስፒታል ኮቪድ19 ሕሙማን ቁጥር ከ1,002 ወደ 998 ወርዷል። ኩዊንስላንድ ውስጥ የሕሙማኑ ቁጥር 863 ላይ ረግቷል።
- የኩዊንስላንድ መንግሥት በዚህ ሳምንት የትምህርት ቤቶች ከፈታ ዕቅዱን ይፋ ያደርጋል።
- የሁለት ዙር ክትባቶችን ከተከተቡ ሶስት ወራት የሞላቸው የኩዊንስላንድ ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምረው የሶስተኛ ዙር ክትባቶቻቸውን መከተብ ይችላሉ።
የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 30,825 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ25 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
ቪክቶሪያ ውስጥ 11,695 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 17 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኩዊንስላንድ 10,212 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 13 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።
ታዝማኒያ 619 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ፤ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤
- ከ60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ዜናዎችና መረጃዎች ከ
- የክፍለ አገርዎ ረብ ያላቸው መምሪያዎች , , , , , , .
- ስለ ኮቪድ-19 መረጃ በቋንቋዎ