Feature

የአውስትራሊያ ክልሎች እና ግዛቶች የወቅቱ የኮቪድ-19 እርምጃዎች

COVID

Source: Getty Images/Cheryl Bronson

SBS COVID-19 አገር አቀፍ መረጃን በተመለከተ, 

ይህ መረጃ ለመጨረ ጊዜ የተሻሻለው በ 07/12/2020 ሲሆን COVID-19 በተመለከተ አዳዲስ መረጃዎችን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለማግኘት  ይጎብኙ

ቪክቶሪያ  _ ገደቦችን አላላች

በአንድ ቦታ መሰባሰብን በተመለከተ ፦

  • ከቤት ለመውጣት ፦ ምንም አይነት ገደብ የለም
  • ህዝብ በሚሰባሰብበት ስፍራ ፦ ከውጭ እስከ 50 ሰዎች
  • በቤትዎ የሚጋበዙ ሰዎች ቁጥር ፦ በቀን እስከ 15 ሰዎችን ፤ ከተለያዩ የቤተሰብ አባላትንም ማካተት ይቻላል ፤ ( ቁጥሩ ህጻናትን እና ታዳጊ ወጣቶችን አያጠቃልልም )
  • የፈረንጆች ገና በአል አከባበር ፦ ከዲሴምበር 14 ጀምሮ እስከ 30 ሰዎችን በቤት ውስጥ ማስተናገድ ይቻላል ( ቁጥሩ ህጻናትን እና ታዳጊ ወጣቶችን አያጠቃልልም )
  • ሀኪም ቤቶች እና እንክብካቤን የሚያደርጉ ተቋማት ፦ የጎብኚዎች ቁጥር እና የሚያሳልፉት ሰአት ገደብ ተነስቷል ፡፡ሀኪም ቤቶች እና እንክብካቤን የሚያደርጉ ተቋማት ጎብኚዎቹን በተመለከተ የራሳቸውን ህግ ማውጣት ይችላሉ ፡፡ 
በሰርግ ፤ ቀብር እና በእምነት ተቋማት ስፍራ የሚደርጉ መሰባሰቦችን በተመለከተ የተቀመጠው የቁጥር ገደብ የተነሳ ሲሆን ፤ በሁለት ሜትር ስኩዬር ውስጥ አንድ ሰው ብቻ የሚለው ህግ መከበር ይኖርባታል፡፡

የስራ ቦታ

  •  ከቤት መስራት የሚችሉ እስከሆነ ድረስ ይህንኑ መቀጠል ይኖርብዎታል ፤ ይህም በስራ ቦታ የሚገኙትን ሰዎች ቁጥር በመቀነስ የCOVID-19 ስርጭትን ለማገድ ከፍተኛ አስተውጻኦ ያደርጋል ፡፡
  • ቀስ በቀስ 25 % የሚሆኑት ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው የሚመለሱበት አካሄድ የጀመረ ሲሆን በአራት ሜትር ስኩዬር ሜትሮች አንድ ሰው ብቻ የሚለው ህግም በተግባር ውሏል ፡፡
  • በቪክቶርያ የፊት ጭምብል ( ማስክ ) የማድረግ ግዴታነት የቀረ ሲሆን ይህ በቢሮዎችም ሆነ በሻይ ቤቶች አካባቢ  ያለውን ያጠቃልላል ፡፡
  • የፊት መሸፈኛ ጭንብል ሁል ጊዜም ይዘው መገኘት የሚጠበቅብዎት ሲሆን በህዝብ መጓጓዣ ፤ በጋራ የሚጠቀሙበት መኪና ፤ በዝግ የገበያ ማእከላት እና ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች ማድረግ የግድ ይላል ፡፡  
 ስራዎ ከቤትዎ መስራት ካልቻሉ ወደ ስራ መመለስ ይችላሉ ፡፡ በስራዎ ገበታዎ ላይ ሆነውም የሚከተሉትን በማድረግ ደህንነትዎን መጠበቅ ይችላሉ ፦  

  • እጅዎን ቶሎ ቶሎ ይታጠቡ
  • ሲያስሉ እና ሲያስነጥሱ ሶፍት ወረቀትን ይጠቀሙ ወይም በክንድዎ ስር ያድርጉ
  • ከሌሎች ጋር የ 1.5 ሜትር ርቀትዎ ይጠብቁ
ሁሉም የንግድ ተቋማት ከቤታቸው የሚሰሩትን ጨምሮ የCOVIDSafe Plan ሊኖራቸው ይገባል ፡፡ ( ለምሳሌ ከቤታቸው የሚሰሩ ጸጉር ሰሪዎች )

 ትምህርት ቤቶች

  • ሁሉም የቪክቶርያ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በአካል ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል
  • በዩኒቨርሲቲ ፤ ቴፍ እና የጎልማሳ ትምህርት ቤት  የገጽ ለገጽ ትምህርት ተጀምሯል ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፦

ጉዞ እና መጓጓዣ

  • የህዝብ መጓጓዣን እና የጋራ መገልገያ መኪናዎችን በሚጠቀሙ ጊዜ ሁሉ የፊት መሸፈኛ ጭንብል ( ማስክ ) የግድ መጠቀም አለብዎ ፤ እንዲሁም የግል ንጽህናዎን መጠበቅ እና ጤንነት ካልተሰማዎ ጉዞን አያድርጉ ፡፡
  • ከቤት ለመውጣትም ሆነ የሚጓዙትን ርቀት የሚወስነው ገደብ ተነስቷል
  • በቪክቶሪያ ውስጥ በየትኛውም ስፍራ ለእረፍት መሄድ ይቻላል
  • የማረፊያ ሆቴልን በተመለከተም አብሮት ከሚኖር ሰው ጋር ፤ ከፍቅር አጋርዎ ጋር ፤ አብርዎት ከማይኖሩ እስከ ሁለት የሚደርሱ የቅርብ ጓደኞች ወይም የቤተሰብ አባላት ( ከነ ልጆቻቸው ) ጋር በመሆን ማረፊያ ሆቴልን መያዝ ይችላሉ ፡፡
  • በቪክቶርያ ገጠራማው እና ከተማ አካባቢ ለመጓጓዝ የሚከለክል ምንም ገደብ የለም
  • በአሁን ሰአት ወደ ቪክቶሪያ የሚደረጉ አለማቀፍ በረራዎች አይኖሩም
 የንግድ እና የመዝናኛ ስፍራዎች

በሻይ ቤቶች ፤ የምግብ ቤቶች እና የመጠጥ ቤቶች የሚታደሙት ሰዎች ቁጥር ገደብ የተነሳ ሲሆን ፤ በምትኩም አንድ ሰው በሁለት ሜትር ስኩዬር ውስጥ የሚለው ህግ ተግባራዊ ይሆናል ፡፡ ደንበኞች ለመስተናገድ የግድ ወንበር መያዝ አይጠበቀባቸውም ፡፡

የቤት ውጭ ስፖርት ፤ መዋኛ ስፍራ  ፦ በሁለት ሜትር ውስጥ አንድ ሰው የሚለው ህግ እስከተከበረ ድረስ በስፍራው በሚገኙ ሰዎች ላይ የቁጥር ገደብ አይኖርም ፡፡

ጂም ፦ የሚታደሙት ሰዎች ቁጥር የሚወሰነው እንደ ስፍራው ስፋት ሲሆን ሰዎች በሚበዙበት ጊዜ የአራት ሜትር ስኩዬር ህግ በተግባር ሊውል ይችላል ፡፡

ብዙ ሰዎች ከሌሉ በስምንት ሜትር ስኩዬር ውስጥ አንድ ሰው የሚለው ህግ በተግባር ሊውል ይችላል ፡፡

ቅጣቶች

ቅጣቶች በተግባር የሚውሉት ገደቦች ተጥለው ባሉባቸው ስፍራዎች ብቻ ይሆናል ፡፡ለምሳሌ ፦ የኮሮናቫይርስ እንደታየ ከተረጋገጠ ወይም ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ እንዳላቸው ታውቆ ተገልለው እንዲቀመጡ ተነግሯቸው ይህንን የማያደርጉ ቪክቶርያውያን ቅጣት እንዲከፍሉ ይደረጋሉ ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፦

ኒው ሳውዝ ዌልስ

በአንድ ስፍራ የመሰባሰብ ገደብ ፦

  • በመኖሪያ ቤት የውጭ መዝናኛ ስፍራ ካለው እስከ 50 የሚሆኑ ሰዎችን ማስተናገድ የሚቻል ሲሆን ነገር ግን የውጭ መዝናኛ ሥፍራ ከሌለ የታዳሚዎቹን ቁጥር ወደ 30 ዝቅ እንዲል ይመከራል ፡፡፡
  • ከዲሴምበር 7 ጀምሮ እስከ 100 የሚሆኑ ሰዎች ከቤት ውጭ መሰባሰብ ይችላሉ ፡፡ 
  • ሰርግ ፤ ቀብር እና የእምነት ስነ ስርአቶች ላይ የሚገኙት ሰዎች ቁጥር ከዲሴምበር 7 ጀምሮ የተነሳ ሲሆን ፤ ቁጥሩ የሚወሰነውም  በ2 ሜትር ስኩዬር ህግ ይሆናል ፡፡
የስራ ቦታ

  • በሰኞ ዲሴምበር 14 ፤ 2020 ጀምሮ ሰራተኞች ከቤት መስራት እስከቻሉ ድረስ ስራቸውን ከቤት ይስሩ የሚለው የህብረተሰብ ጤና ምክር የሚነሳ ይሆናል ፡፡
  • ተቀጣሪዎች ወደ ስራ ገበታቸም በሚመለሱበት ጊዜም አሰሪዎች የCOVID-19 Safety Plan ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል ፡፡
  • የሰራተኞችን የመግቢያ እና መውጫ ሰአት የተለያየ እንዲያደርጉ ቀጣሪዎች የሚመከሩ ሲሆን ይህም በህዝብ መጓጓዣዎች ላይ ሊኖር የሚችለውን መጨናነቅ ለመቀነስ ይረዳል ፡፡የህዝብ መጓጓዣዎችን የሚጠቀሙ ሁሉ የፊት መሸፈኛ ማስክ እንዲያደርጉ ይመከራሉ ፡፡
  • ጤንነት የማይሰማቸው ሰራተኞች ሁሉ የግድ ከቤታቸው መቆየት ይኖርባቸዋል ፡፡ እንዲሁም ምልክቶቹ ከተሰማቸው የ COVID-19 ምርመራን ማድረግ ይኖርባቸዋል ፡፡
ትምህርት ቤቶች

  • በኒው ሳውዝ ዌልስ የሚኖሩ ተማሪዎች የ COVID-19 ምልክቶች ከታዮባቸው ተመርምረው ነጻ መሆናቸው ካልተረጋገጠ ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ አይችሉም ፤
  • በትምህርት ቤት ውስጥ የሚደረጉ የመዝጊያ ዝግጅቶች ፤ ዳንስ ፤ምርቃት እና ሌሎች ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ አይቻልም ፡፡
የኒው ሳውዝ ዌልስ  ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ ፡ 

ጉዞ እና መጓጓዣ

  • ወደ ኒውሳውዝ ዌልስ ከየትኛውም ክልል ለጉብኝት መጓዝ የተፈቀደ ሲሆን ይሁን እና በሚመለሱበት ጊዜ የክልላቸውን ህግ የማክበር ግዴታ አለባቸው ፡፡
  • ካራቫን ፓርክ እና የካምፕ ስፍራዎች ለአገልግሎት ክፍት ናቸው፡፡ የብሄራዊ መናፈሻዎችን ለመጎብኘት የሚሹ ተጨማሪ መረጃን  ከ   ማግኘት ይችላሉ፡፡
የንግድ እና የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች

  • ለተወሰኑ የንግድ ተቋማት እና ድርጅቶች  በህብረተሰብ ጤና መመሪያ መሰረት የኮቪድ-19 ሴፍ ምዝገባ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ፦  
  • ጂሞች እና የምሽት ቤቶች ፦ በ 4 ሜትር ስኲዬር አንድ ሰው የሚለው ህግ የሚሰራ ሲሆን  በአንድ ጊዜም በጂም ውስጥም ሆነ በዳንስ መድረክ ላይ እስከ 50 ሰዎች መግኘት ይችላልዑ ፡፡
  • ስታዲየም እና ቲያትር ቤቶች ፦ ( በውጭ ) 100 % የማስተናገድ አቅማቸውን መጠቀም ይችላሉ ፡፡ እንዲሁም ባልተስተካከለ የመቀመጫ ስፍራ አንድ ሰው በሁለት ሜትር ስኩዬር ውስጥ  የሚለው ህግ መከበር ይኖርበታል፡፡ በውስጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች 70 % የሚሆኑት መቀመጫዎች ለአገልግሎት መዋል ይችላሉ ፡፡
  • አንስተኛ የመዝናኛ ስፍራዎች ( ስፋታቸው እስከ 200 ሜትር ስኩዬር የሆኑት ) አንድ ሰው በሁለት ሜትር ስኩዬር ማስተናገድ ይችላሉ ፡፡
  • የማህበረሰብ የስፓርት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የተፈቀደ ሲሆን ይህም ንክኪን የሚጠይቁ ስልጠናን ያጠቃልላል፡፡
የንግድ ተቋማት እና የልዩ ዝግጅት አዘጋጆች  የኮቪድ_19 ሴፍ እቅድ ( COVID-19 safety paln ) ሊኖራቸው ግድ ይላል፡፡ እንዲሁም የሚገቡትን ሰዎች ዝርዝር በሙሉ ጽፈው ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፦

ቅጣቶች

  • የተቀመጡ ገደቦችን በጣሱ ላይ ሁሉ ቅጣት በተግባር የሚውል ይሆናል ፡፡ ለምሳሌ ያልተፈቀዱ መሰባሰብን መጥቀስ ይቻላል ፡፡
የማህበረሰብ ጤና አንቀጽ 2010 መተላለፍ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ የሚያስጠይቅ ሲሆን ቅጣቱም ከበድ ያለ ነው ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፡   

ኩዊንስላንድ  

በአንድ ስፍራ የመሰባሰብ ገደብ 

  • በመኖሪያ ቤቶች እስከ 50 ሰዎች እንዲሁም ህዝብ በሚሰባሰብበት ስፍራ  እስከ 100 ያህል ሰዎች መሰባሰብ በመላው ኩዊንስላድ የተፈቀደ ነው፡፡
  • የሰርግ ስነ ስርአት ፦ እስከ 200 ያህል ሰዎች መገኘት የሚችሉ ሲሆን ከውስጥም ሆነ ከውጭ ያሉ ታዳሚዎች ሁሉ ዳንኪራን መውረድ ይችላሉ፡፡
  • የቀብር ስነ ስርአት ፦ እስከ 200 ያህል ሰዎች መገኘት ይችላሉ ፡፡
  • በአእምሮ ጤና አደንዛዥ እጽ እንዲሁም አልኮል ሳቢያ ጤናቸው የተናጋ የቤተሰብዎ አባላት እንዲያገግሙ ከሚቆዩበት ስፍራ ሄዶ መጎብኘት የተፈቀደ ነው፡፡
  • የሃኪም ቤት ጉብኝት ፦ የጎብኚዎች ቁጥር የሚወሰነው በተለመደው የጎብኚዎች ህግ ይሆናል ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፦

የስራ ቦታ

የንግድ ተቋማት የሚከተሉትን የግድ ማክበር አለባቸው ፦

  • ከቤት መስራትን ማበረታት
  • ህመም የሚሰማቸውን ሰራተኞችን ወደቤት መመለስ
  • በ2 ሜትር ስኩዬር 1 ሰው ብቻን መፍቀድ
  • አካላዊ ርቀትን ለማበረታት በአይን የሚታዩ ምልክቶችን ማስቀመጥ
  • ስራቸውን በCOVID Safe Framework መሰረት ማከናወን
  • ሁሉንም ስፍራ ቶሎ ቶሎ ማጽዳት
  • የእጅ ማጽጃ ( ሳኒታይዘር ) ማቅረብ
ሰራተኞች የሚከተሉትን የግድ ማክበር አለባቸው፦

  • ካመመኝ ከቤቴ መቆየት አለብኝ
  •  የ COVID-19 ምልከት ከታየ ምርመራን ማድረግ
  • ከሌሎች ጋር የ1.5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ
  • እጅን በሳሙና እና ሳኒታይዘር በየጊዜው ማጽዳት
  • ሲስሉ እና ሲያስነጥሱ መሸፈን
ትምህርት ቤቶች

  • ልጆች ጤንነት እንዳልተሰማቸው በትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር ፤ አስተማሪ ወይም የስራ ባልደረባ ከታወቀ ፤ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ተጠርተው ልጆቻቸውን እንዲወስዱ ይደረጋል ፡፡
  • ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች በአስቸኳይ መጥተው ልጆቻቸውን መውሰድ አለባቸው
  • ልጆች የማስተላለፊያ ጊዜውን እስኪያልፉ ድረስ ወደ ትምህርት ገበታቸው አይመለሱም
ለተጨማሪ መረጃ ፦

ጉዞ እና መጓጓዣ

  • ከዲሴምበር 1 2020 ጀምሮ የኩዊንስላንድን የድንበር ማለፊያ ቅጽ መሙላት የሚገደዱት ባለፉት 14 ቀናት ኮቪድ ታይቶባቸዋል በተባሉት ስፍራዎች ቆይተው ከነበር ፤ ወይም ከውጭ ሀገር ከተመለሱ ብቻ ይሆናል ፡፡
  • ማንኛውም ከኒውሳውዝ ዌልስ ወይም ቪክቶርያ መጥቶ በመንግስት ለይቶ ማቆያ ስፍራ የቆየ ፤ የኮቪድ19 ምርመራን ወስዶ ነጻ ከሆነ እና የት እንደሚቆይ አድራሻውን ማቅረብ ከቻለ ፤ ከመቆያ ስፍራው መውጣት ይችላል፡፡
  • ኮቪድ ታይቶባቸዋል ከተባሉ ስፍራዎች ወደኩዊንስላድ በአውሮፕላን ለመግባት ፈቃድ የግድ ያስፈልጋል ፡፡ እንዲሁም በምድር ተጉዞ ለመግባትም ለሚሹ ከከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በቀር ሌሎችሁሉ ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል ፡፡  
ለተጨማሪ መረጃ ፦

የንግድ እና የመዝናኛ ቦታዎች 

  • የውስጥ መዝናኛዎች ፦ አንድ ሰው በ2 ሜትር ስኩዬር ( የምግብ ቤቶች ፤የቡና ቤቶች ፤ የመጠጥ ቤቶች ፤ ክለቦች ፤ ሙዚየሞች ፤ የስነጥበብ ጋለሪዎች ፤ የማምለኪያ ስፍራዎች ፓርላም )   
  • የውስጥ እንቅስቃሴዎች ፦ 100 % የመያዝ አቅማቸውን መጠቀም የሚችሉ ሲሆን በታዳሚዎች መውጫ እና መግቢያ ስፍራ አካባቢ የፊት ጭምብል (ማስክ ) ማድረግ ግድ ይላል (ለምሳሊ ቲያትን፤ የቀጥታ ሙዚቃ ፤ ሲኒማ እና የቤት ውስጥ ስፓርት ) ትርኢቱን የሚያሳዪት ከታዳሚዎች ቢያንስ 2 ሜትሮች ያህል መራቅ ይኖርባቸዋል ፡፡
  • የውጭ እንቅስቃሴዎች ፦ ቁጥራቸው 1500 የሚሆኑ መታደም የሚችሉ ሲሆን የ COVID Safe even checklist ማዘጋጀት ግድ ይላቸዋል፡፡ እንዲሁም ለትልልቅ ዝግጅቶች COVID Safe Plan ያስፈልጋል ፡፡
  • ክፍት ስታዲየሞች ፦ 100 % የመያዝ አቅማቸውብን መጠቀም ይችላሉ፡፡
  • ክፍት የዳንኪራ መድረኮች ፦ በውጭ የሚደረጉ ዳንኪራዎች የተፈቀዱ ሲሆን ለምሳሌ የሙዚቃ ፌሲቫሎችን መጥቀስ ይቻላል ፡፡ለተጨማሪ መረጃ ፦
ቅጣቶች

  • የተቀመጡ ገደቦችን በጣሱ ላይ ሁሉ ቅጣት በተግባር የሚውል ይሆናል ፡፡ ለምሳሌ ያልተፈቀዱ መሰባሰብን ወይም የፊት ጭምብልን ማድረግ ግዴታ በሆነባቸው ስፍራ ሳያደርጉ መገኘት  ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፦

ሳውዝ አውስትራሊያ

በአንድ ስፍራ የመሰባሰብ ገደብ

  • በውስጥ 1 ሰው በ4 ሜትር ስኩዬር ሜትሮች
  • ከውጭ 1 ሰው በ2 ሜትር ስኩዬር ሜትሮች
የግል አዳራሾች( ለሰርግ እና ለቀብር ስነ ስርአቶች )

እስከ 15 ሰዎች ወይም 1 ሰው በ2 ሜትር ስኩዬር ሜትሮች

የስራ ቦታ

  • አሁንም ድረስ ያልተነሱ ገደቦች እንደመኖራቸው መጥን ሰዎች ከቤታቸው መስራትን እንዲቀጥሉ በከፍተኛ ሁኔታ  ይመከራሉ ፡፡
  • በስራ ቦታ የሚኖር ማስተካከያ በሳውዝ አውስትራሊያ ኮቪድ19 ለመከላከል የሚደረገውን ጥርት የሚደግፍ ሲሆን ፤ ምናልባትም ወደፊት ሌላ የወረርሽኝ ወቅት ቢታይ የንግድ ተቋማት ስራቸው እንዳይተጓጎል ይረዳል ፡፡
ትምህርት ቤቶች

የሳውዝ አውስትራሊያ ትምህርት ቤቶች  ከሁለተኛው መንፈቀ ትምህርት ጀምሮ ክፍት ሆነዋል፡፡ ለተጨማሪ መርጃ ፦

ጉዞ እና መጓጓዣ

  • በህዝብ መጓጓዣዎች መጓዝ የሚሹ ከሆነ በተቻለ መጠን ቀጥተኛውን የጉዞ መስመር መውስድ ይኖርብዎታል
  • በአብዛኛው የሳውዝ አውስትራሊያ አካባቢዎች ጉዞ የተከለከለ አይደለም
  • በአለማቀፍ በረራዎች የሚመጡ ሁሉ በሳውዝ አውስትራሊያ የጤና ተቋም በተረጋገጠ የማቆያ ስፍራ ለ14 ቀናት መቆየት ግድ ይላል ፡፡
ንግድ እና መዝናኛ

  • በአንድ ስፍራ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር 1 ሰው በ2 ሜትር ስኩዬር ሜትሮች ውስጥ መብለጥ የለበትም ፡፡
  • ምግብ እና መጠጥ በመዝናኛ ስፍራዎች ማቅረብ ይቻላል ፡፡( በመጠጥ ቤቶች ፤ ቡና ቤቶች ፤ ክለቦች ፤ ምግብ ቤቶች ፤ የወይን ጠጅ መጥመቂያ ስፍራዎች ሁሉ ታዳሚዎች ተቀምጠው መስተናገድ አለባቸው )
  • ለሌሎች እንክብካቤን የሚያደርጉ ባለሞያዎች ተገቢውን የመከላከያ አልባሳትን መልበስ ይኖርባቸዋል ፡፡
  • በውስጥ የሚታዩ ሲኒማዎች ፤ ቲያትሮች ወይም ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች አዳራሾቹ 50 % የሚሆነውን የመያዝ አቅማቸውን ብቻ መጠቀም ይችላሉ ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ፦

ቅጣቶች

  • የተቀመጡ ገደቦችን በጣሱ ላይ ሁሉ ቅጣት በተግባር የሚውል ይሆናል ፡፡ ለምሳሌ ያልተፈቀዱ መሰባሰብን ወይም የፊት ጭምብልን ማድረግ ግዴታ በሆነባቸው ስፍራ ሳያደርጉ መገኘት  ፡፡
ዌስተርን አውስትራሊያ

ደረጃ 4

የዌስተርን አውስትራሊያ የኮቪድ 19 ገደቦች ለቀቅ እንዲል የተደረገ ሲሆን  ካሉት 6 ደረጃዎች ወደ ደረጃ አራት ተሸጋግሯል ፡፡

በአንድ ቦታ የመሰባሰብ ገደብ

  • በመኖሪያ ቤት የሚደረግ መሰባሰብ 1 ሰው በ2 ሜትር ስኩዬር ሜትሮች ውስጥ የሚለው ህግ እስከተከበረ ድረስ ገደብ የለውም
  • ህዝብ በሚሰባሰብባቸው ስፍራዎች 1 ሰው በ2 ሜትር ስኩዬር ሜትሮች የሚለው ህግ መከበር አለበት
  • 1 ሰው በ2 ሜትር ስኩዬር ሜትሮች የሚለው ህግ የመግቢያ ትኬት ቆርጠው በሚከታለሏቸው የመዝናኛ ዝግጅቶች ወይም የአምልኮ ስፍራዎች ላይ በተግባር አይውልም ፡፡
  • በገጠራማ ስፍራ በሚኖሩ የአቦሪናል ማህበርሰብን ለመድረስ አሁን ገደብ አለ
  • በአረጋውያን መጦርያ ውስጥ የሚኖሩ ተጧሪዎችን ለመጎብኘት የተቀመጡ ገደቦች አሉ
የስራ ቦታ

የዌስትርን አውስትራሊያ ነዋሪዎች የጤና መታወክ ካልገጠማቸው በቀር ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ይበረታታሉ ፡፡ ወደ ስራ መመለስን በተመለከተ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ቀጣሪዎን ማነጋገር ይኖርብዎታል ፡፡

በስራ ቦታዎ ሳሉ ፦

  • የግል ንጽህናን እና አካላዊ ርቀትን ይጠብቁ
  • በእጅ መጨባበጥን ያስወግዱ
  • ቶሎ ቶሎ የሚነካኩ ስፍራዎችን ያጽዱ
  • ምሳዎን ከመመገቢያ ክፍል ከመብላት ይልቅ ከተቀመጡበት ስፍራ ወይም ውጭ ይብሉ
  • ምግብን ከማቀራረብ ወይም ከሌሎች ጋር ተካፍሎ ከመብላት ይቆጠቡ
ለተጨማሪ መረጃ ፦  

ትምህርት ቤቶች

ንግድ እና መዝናኛ

  • በአንድ አዳራሽ ውስጥ የሚገኙት ሰዎች ቁጥር ወሰን የሌለው ሲሆን ነገር ግን የ2 ሜትር ስኩዬር ሜትሮች እና አካላዊ ርቀት ህጎችን በተግባር ማዋል ግድ ይላል ፡፡ ይህ ማለት የሚገኙት ሰዎች ቁጥር የሚወሰነው በአዳራሹ ስፋት መጠን ነው፡፡
  • ትላልቅ አዳራሾች እስክ 500 ያህል ሰዎችን ማስተናገድ ይችላሉ
  • የካዚኖ ጌም መጫወቻ ስፍራ በስምምነት ላይ በዋልው ጊዜያዊ ገደብ አማካኝነት ክፍት ሆኗል  
  • በምግብ ቤቶች ፤ ሻይ ቤቶች እና የመጠጥ ቤቶች ታዳሚዎችን መመዝገብ አያስፈልግም
  • ከታላላቅ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች በቀር ሁሉም አይነት ዝግጅቶች የተፈቀዱ ናቸው
  • Optus Stadium HBF park RAC Arena  50% የሆነውን የመያዝ አቅማቸውን መጠቀም ይችላሉ
  • ቆመው የሚታደሟቸው ኮንሰርቶች ፤ የቀጥታ የሙዚቃ ድግሶች ፤ በመጠጥ ቤቶች  እና የምሽት ቤቶች የተፈቀዱ ናቸው
  • ተቀምጠው የሚስተናገዱት ታዳሚዎች ብዛት ከ 60% መብለጥ የላበትም 
ለተጨማሪ መርጃ ፦

ቅጣቶች

  • የተቀመጡ ገደቦችን በጣሱ ላይ ሁሉ ቅጣት በተግባር የሚውል ይሆናል ፡፡ ለምሳሌ ያልተፈቀዱ መሰባሰብን ወይም የፊት ጭምብልን ማድረግ ግዴታ በሆነባቸው ስፍራ ሳያደርጉ መገኘት  ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፦

ታዝማ

ባንድ ስፍራ የመሰባሰብ ገደብ

  • በመኖሪያ ቤት ፡ የቤተሰቡን አባላት ሳይጨምር በማንኛውም ሰአት እስከ 40 ሰዎች መገኘት ይችላሉ
  • በሰርግ ፤ በአምልኮ ስፍራ እና ልዩ ዝግጅቶች ላይ የሚገኙት ሰዎች የሚወሰነው በቦታው የመያዝ አቅም ሲሆን ፤ በውስጥ እስከ 250 እንዲሁም ከውጭ እስከ 1000 ታዳሚዎችን ማስተናገድ ይቻላል
  • የሀኪም ቤት ጉብኝት ፦ የጎብኚዎች ቁጥር የተወሰነ ሲሆን ለአንድ በሽተኛ  በአንድ ጊዜ አንድ ሰው ብቻ እንዲጎበኘው ይፈቀዳል ፡፡
የስራ ቦታ

ሰዎች ከቤታችው መስራትን እንዲቀጥሉ የሚበረታቱ ሲሆን ይህም አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ እና በሰዎች መካከል የሚኖር መነካካትን ለመቀነስ ያግዛል፡፡

ትምህርት ቤቶች

  • ጤናቸው በመልካም ሁኔታ ላይ ያሉ ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከትምህርት ቤት መከታተላቸውን ይቀጥላሉ
  • ጤናቸውን በተመለከተ ስጋት ያላቸው ፤ በኮቪድ19 ምክንያት የጤና ችግር የገጠማቸው ሁሉ ከቤታቸው መማራቸውን እንዲቀጥሉ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ይህንንም ለማመቻቸት ትምህርት ቤቱን ማነጋገር ያስፈልጋል ፡፡
ጉዞ እና መጓጓዣ

  • ወደ ታዝማንያ መምጣት እና የፈልጉት ስፍራ መቆየት ይቻላል ፡፡ ይሁንና ገደቦችን እና የመሰባሰብ ህጎችን እንዲሁም የዘመድ ጉብኝቶችን በተመለከት የክልሉን ህግ ማክበር ግድ ይላል፡፡ 
  • ወደ ታዝማንያ የሚጓዙ ሁሉ ከመድረሳቸው በፊት አድራሻቸውን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል ፡፡ ይህም ኮቪድ19 የሚያደርሰውን ስጋት ሳይከሰት ለመከላከል ይረዳል፡፡
  • ተጓዦቹ ወደ ታዝማንያ ከመምጣታቸው በፊት የቆዩበት አካባቢ ወደ ክልሉ ሲገቡ የነበራቸውን ሁኔታ ለመሰን ያግዛል ፡፡
  • ራሳቸን ለይተው መቆየት ያለባቸው ሰዎች ክፍያ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሁኔታዎች እየታዩ ከክፍያ ነጻ የሚደረጉበትም አካሄድም አለ፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ ፦
የንግድ እና የመዝናኛ ቦታዎች

  • ሁሉም የስራ እና የንግድ ተቋማት ወደ ስራቸው የተመለሱ ሲሆን የኮቪድ19የጥንቃቄ ሂደቶችን መከተል ይኖርባቸዋል፡፡
  • የሚያስተናግዷቸው ሰዎች ብዛት አንድ ሰው በ 2 ሜትር ስኩዬሮች መሆን አለበት
  • ጂሞች የተከፈቱ ሲሆን COVID -Safe plan ማሟላት የሚይዙትን ሰው ብዛት ፤ አካልዊ ርቀትን ፤ ተጠቃሚዎችን ዝርዝር ማቆየትን፤ ንጽህናን በተመለከት መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፦

ቅጣቶች

  • የተቀመጡ ገደቦችን በጣሱ ላይ ሁሉ ቅጣት በተግባር የሚውል ይሆናል ፡፡ ለምሳሌ ያልተፈቀዱ መሰባሰብን ወይም የፊት ጭምብልን ማድረግ ግዴታ በሆነባቸው ስፍራ ሳያደርጉ መገኘት  ፡፡
ኖርዘርን ቴሪቶሪ

ባንድ ስፍራ የመሰባሰብ ገደብ

  • በአሁን ሰአት በክልሉ ምንም አይነት ገደብ አልተቀመጠም ፤ ይሁንና   ነዋሪዎች በሰዎች መካከል የ 1. 5 ሜትር ርቀትን እንዲያከብሩ ይጠየቃሉ፡፡
  • ሰርግ እና የቀብር ስነ ስርአቶች ተፈቅደዋል፡፡
  • ከ100 በላይ ሰዎች የሚሰባሰቡ ከሆነ የ COVID-19 ዝርዝር ሊኖር ግድ ይላል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፦

የስራ ቦታ

በ CHO አመራር መሰረት የንግድ ተቋማት ፤ ድርጅቶች እና የማህበረሰብ ተቋማት  የሚከተሉትን ማሟላት አለባቸው ፦ 

  • የ COVID-19 Safety plan ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን በየስድስት ወር መከለስ ይኖርበታል
  • ለሁሉም ደንበኞች የሚሆን የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር ማዘጋጀት የሚያስፈልግ ሲሆን ይህም ካልሆነ የእጅ መታጠቢያ ስፍራ ሊኖር ግድ ይላል
  • ለሰዎች በግልጽ በሚታዩ ስፍራዎች ምልክቶችን በማስቀመጥ የሚከተሉትን ከግምት ውስጥ እንዲያደጉ ማድረግ ይቻላል ፦
የ1.5 አካላዊ ርቀት መጠበቅን

የቅርብ ግንኙነትን ከ 15 ደቂቃዎች ያለማስበላጥ ይህ ካልሆነም  በ1.5 ሜትር ርቀት ውስጥ መቆየት 

የእጅ ንጽህናን በመታጠብ እና ሳኒታይዘር በመጠቀም መጠበቅ

ጤንነት ካልተሰማዎ ከቤዎ ይቀመጡ ከዚያም ምርመራን ያድርጉ

ለተጨማሪ መረጃ ፦

ትምህርት ቤቶች 

  •  ሁሉም የኖርዘርን ቴሪተሪ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ በአካል  እንዲገኙ ይጠበቃል፡፡
ጉዞ እና መጓጓዣ

  • ወደ ግዛቷ ከውጭ ሀገር የሚመጡ ተጓዦች በሙሉ  በቀጥታ ክትትል ወደ ሚደረግበት  Howard Springs quarantine facility እንዲሄዱ ይደርጋል፡፡
ከሌላ ክልሎች የሚመጡ ፦

  • ኮሮናቫይረስ ታይቶባቸዋል ከተባሉ አካባቢዎች እስካልመጡ ድረስ ራሳቸውን ለይተው ማቆየት አይጠበቅባቸውም
  • ስኬትፓርክ ፤ የመዋኛ ስፍራዎች ፤ የመጫወቻ ስፍራዎች ፤ የውጭ ጂሞች እንዲከፈቱ ተፈቅዷል
  • የሻይ ቤቶች ፤ የምግብ ቤቶች ፤ የመጠጥ ቤቶች ፤ የስፓርት ማሰልጠኛዎች ፤ የቤት ውስጥ ገበያዎች ፤ ጂሞች ፤ ቤተ መጻህፍት ፤ ጋለሪዎች እና ቤተ መዘክሮች ፤ እንዲሁም ሁሉም የንግድ ተቋማት ክፍት ይሆናሉ፡፡
  • የማህበረሰብ ስፖርታዊ ውድድርን በተፈቀድ ስፍራ ሆኖ መካፈል የተፈቀደ ነው፡፡ የታዳሚዎቹ ቁጥር ከ 500 ከበለጠ የCOVID-19 Safety plan ሊኖር ግድ ይላል፡፡
ቅጣቶች

  • የተቀመጡ ገደቦችን በጣሱ ላይ ሁሉ ቅጣት በተግባር የሚውል ይሆናል ፡፡ ለምሳሌ ያልተፈቀዱ መሰባሰብን ወይም የፊት ጭምብልን ማድረግ ግዴታ በሆነባቸው ስፍራ ሳያደርጉ መገኘት  ፡፡
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪተሪ

በአንድ ስፍራ የመሰባሰብ ገደብ

  • በመኖርያ ቤት ውስጥ፦ ያለገደብ እንግዶችን ማስተናገድ ይቻላል ፡፡
  • ሰርግ እና የቀብር ስነ ስርአት ፦ በአራት ሜትር ስኩዬር ውስጥ አንድ ሰው የሚለው ህግ እስካልተጣሰ ደረስ 500ያህል ሰዎች በሰርግ እና የቀብር ስነ ስርአት ላይ መገኘት ይችላሉ
  • የአምልኮ ስፍራዎች ፦ 25 ሰዎች ፤ በስፍራው የሚሰሩ እና አገልግሎቱን የሚያካሂዱትን ሳያጠቃልል መታደም ይችላሉ
  • የአረጋውያን መጦርያ ፦ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን እና ጓደኞቻቸውን በአረጋውያን መጦርያ ቤቶች ሄደው መጎብኘት እና ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ፡፡  ከዚያ ለሚቆዩበት የተውሰነ የጊዜ ገደብ የለም ፡፡
  • የህዝብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች ፦ የቀብር ስነ ስርአትን ጨምሮ በአንድ ስፍራ እስከ 100 ሰዎች መሰባሰብ ይችላሉ (  በአራት ሜትር ስኩዬር ውስጥ አንድ ሰው የሚለው እንዲሁም በቤት ውስጥ በሁለት ሜትር ስኩዬር ውስጥ አንድ ሰው የሚለው ህግ እስካልተጣሰ ደረስ ህግ)
ለተጨማሪ መረጃ ፦

የስራ ቦታ

  • ለቀጣሪዎች እና ተቀጣሪዎች አመቺ እስከሆነ ድረስ ወደ ስራ መመለስ ይቻላል የ COVID safe paln ማዘጋጀት ግድ ይላል
  • ጤንነት ካልተሰማዎ ከቤትዎ ይቀመጡ የCOVID-19 ስሜቱ ካለዎት ምርመራን ያድርጉ
ለተጨማሪ መርጃ ፦

ትምህርት ቤቶች

  • የአውስትራሊይ ካፒታል ቴሬቶሪ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ክፍት ናቸው ፤ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች እና መምህራን ወደ ትምህርት ቤት ተመልሰዋል ፡፡
  • ስር የሰደደ የጤና ችግር ያላቸው እና የሰውነት የመከላከያ አቅማቸው የተዳከመ መምህራን እና ተማሪዎች እና ከቤታቸው መስራት እና መማር ይችላሉ
  • ልጅዎ ጤንነት ከልተሰማው እባክዎን ወደ ትምህርት ቤት አይላኩት
ጉዞ  እና መጓጓዣ

  • COVID-19 በቀላሉ የሚሰራጭ እና መቼ እንድሚከሰት መገመት አይቻልም
  • የምጓጓዙ ሂደት እስካልተወሰነ ድረስ የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶር የተጋለጠና ከአደጋ ውጭ ብሎ ያስቀመጠው ስፍራ የለም
  • COVID-19 በብዛት በታየበት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከመጓዛቸው በፊት ሊያስቡበት ግድ ይላል
  • ጤንነት ካልተሰማዎ ወይም ራስዎን ለይተው ማቆየት ካልብዎ በህዝብ መጓጓዣ አይጠቀሙ
  • ራስዎን ለማግለል እየተጓዙ ከሆነ የህዝብ መጓጓዣን አይጠቀሙ ፡፡
የንግድ እና የመዝናኛ ተቋማት

  • በካንብራ ጂም ፤ የምግብ ቤቶች ፤ የሻይ ቤቶች እና መጠጥ ቤቶች እስከ 25 ሰዎችን ማስተናገድ ይችላሉ
  • የንግድ ተቋማት እና አዳራሾች ከ 25 ሰዎች በላይ ማስተናገድ ከፈለጉ 1 ሰው በ 2 ሜትር ስኩዬር ውስጥ የሚለውን ህግ መጠቀም ይችላሉ
  • መጠጥን የሚጠጡ  ተቀምጠው መስተናገድ አለባቸው
  • ሲኒማ ፤ ፊልም እና ቲያትር ቤቶች 65 % የመያዝ አቅማቸውን መጠቀም የሚችሉ ሲሆን የ CBR app የሚጠቀሙ ከሆነ እስከ 500 ያህል ሰዎችን ማስተናገድ ይችላሉ
  • ታላላቅ አዳራሾች 65 % የሚሆነውን የመያዝ አቅማቸውን በመጠቀም እስከ 1500 ሰዎችን ማስተናገድ ይችላሉ
  • በውጭ ያሉ የመዝናኛ ስፍራዎች እስክ 65% የሚሆነውን የመያዝ አቅማቸውን በመጠቀም 1500 ያህል ሰዎችን ማስተናገድ ይችላሉ
  • GIO stadium እና  Manuka Oval 65% የሚሆነውን የመያዝ አቅማቸውን መጠቀም ይችላሉ፡፡
ቅጣቶች

  • የተቀመጡ ገደቦችን በጣሱ ላይ ሁሉ ቅጣት በተግባር የሚውል ይሆናል ፡፡ ለምሳሌ ያልተፈቀዱ መሰባሰብን ወይም የፊት ጭምብልን ማድረግ ግዴታ በሆነባቸው ስፍራ ሳያደርጉ መገኘት  ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፦

 

 


Share
Published 17 May 2020 5:12pm
Updated 11 December 2020 4:55am
By SBS/ALC Content
Presented by Martha Tsegaw
Source: SBS


Share this with family and friends