Feature

ኮቪድ-19 በአውስትራሊያ፤ በቋንቋዎ የግድ ሊያውቋቸው የሚገቡ መረጃዎች

ይህ መዘርዝረ ጭብጥ ስለ ኮቪድ - 19 በቋንቋዎ ሊያውቋቸው የሚገቡ መረጃዎችን አካትቷል።

COVID-19 vaccine

新州疫情嚴峻, 專家呼籲市民要快快接種疫苗。 Source: AAP

ለዕለታዊ ኮቨድ -19 ወቅታዊ የእንግሊዝኛ መረጃ   ይጎብኙ።

በአውስትራሊያ የኮቪድ-19 ክትባት

የአውስትራሊያ መንገስት የኮቪድ-19 ክትባት እንደተገኘ ለሁሉም አውስትራሊያውያን  ለጤና ጠንቅን በማያስከትል መልኩ በስፋት እና በፍጥነት ለማደረስ በቁርጠኝነት ተዘጋጅቷል፡፡

የኮቨድ-19 ክትባት ቀጠሮ ለመያዝ የት መመዝገብ እንዳለብዎት ለመረዳት  ይጎብኙ።

ዕድሜዎ 40 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ለመከተብ መመዘኛውን ያሟላሉ። የተወሰኑ ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 39 ያሉ ሰዎች ምናልባትም ለመከተብ መመዘኛውን ሊያሟሉ ይችላሉ። 

እዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉትን ደረጃ በደረጃ በመከተል ለክትባት መመዘኛውን ያሟሉ እንደሁ ያረጋግጡ፤ 

ዕድሜዎ 18 ወይም ከዚያ በላይ ሆኖ መመዘኛውን ገና ያላሟሉ ከሆነ፤ መመዘኛውን በሚያሟሉበት ወቅት እንዲያስታውቁዎ ይጠይቁ። 

አውስትራሊያ ውስጥ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ለመከተብ መመዘኛውን አያሟሉም። 

ቀጠሮዎን በጠቅላላ ሐኪምዎ በኩል ማስያዝና ስለ ክትባቱ በቋንቋዎ መረጃን ማግኘት ይችላሉ፤ 

ይሁንታን ያገኙ ክትባቶች የትኞቹ ናቸው?

በክትባት ላይ የአውስትራሊያ ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን [ATAGI] ምክረ ሃሳብ መሠረት የፋይዘር ኮቨድ-19 ክትባት ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 59 ላሉ ተመራጭ ክትባት ነው። 

የኮቨድ -19 ክትባት አስትራዜኔካም እንዲሁ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 59 ላሉ ይሰጣል።

ከኮቪድ-19 ጋር ተያያዥ የአዕምሮ ጤና ድጋፍ

በ 2020 የአውስትራሊያ መንግሥት መመዘኛውን ለሚያሟሉ ሕሙማን በእያንዳንዱ የዘመን መቁጠሪያ ዓመት 10 በሜዲኬይር የሚደጎሙ የስነ ልቦና ሕክምና ክፍለ ጊዜያት በ ስር የሥነ አዕምሮ፣ ስነ ልቦናና ጠቅላላ ሐኪሞች በ  የተሻለ ተደራሽነት እንዲኖራቸው አክሏል። 

የአውስትራሊያ መንግሥት ከኮቪድ -19 ጋር ተያያዥነት ያለው የአዕምሮ ጤና ድጋፍ በአዕምሮ ጤና ፖርታል "Head to Health" በኩል በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና ራስን አግልሎ በመቆየት ወቅት እንደምን የአዕምሮ ጤናን በጥሩ ሁኔታ ጠብቆ መቆየት እንደሚቻል የሚያስረዱ መረጃዎችንና መመሪያዎችን አሰናድቷል። )

 

 ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ መደብ ጀርባዎች ባላቸው የአዕምሮ ጤና ላይ የሚያተኩረው ፕሮጄክት የሚመራው በአዕምሮ ጤና አውስትራሊያ ሲሆን ባሕላዊ ይዘት ባለ መልኩ የእገዛ ምንጮች፣ ግልጋሎቶችንና መረጃን ያቀርባል። 

የአዕምሮ ጤና ድጋፍና በቋንቋዎ አስተርጓሚ የሚያሻዎ ከሆነ ብሔራዊ የትርጉምና አስተርጓሚ ግልጋሎት ዘንድ በ 131 450 ይደውሉ ወይም  ድረ ገጽን ይጎብኙ። ብሔራዊ የትርጉምና አስተርጓሚ ግልጋሎት ከ100 ቋንቋዎች በላይ ግልጋሎት ይሰጣል። በአካባቢ የስልክ ጥሪ ዋጋ በቀን ውስጥ 24 ሰዓታት በሳምንት ውስጥ ለ 7 ቀናት በመስመር ላይ ይገኛል።

የገንዘብችግሮች ( በወረርሽኝ ወቅት የአደጋ ጊዜ ክፍያ )

የገንዘብ ችግር ካጋጠመዎት የሚከተለውን ድረገጽ ይመልከቱ ወይም የብሄራዊ የእዳ መርጃ መስመር ላይ 1800 007 007 ይደውሉ ፡፡

የማእከላዊ መንግስት "የአደጋ ጊዜ ክፍያን" አስተዋውቋል ፡፡

ክፍያው እንዲያመለክቱ የሚፈቀድላቸው ራሳቸው ለይተው በሚያቆዩበት ጊዜ ገቢ የማይኖራቸው ሰራተኞች ወይም በኮቪድ-19 የተያዘን ሰው የሚያስታምሙ ናቸው ፡፡

የእያንዳንዱን ክልል የአደጋ ጊዜ ክፍያን በተመለከት የሚከተለውን ሊንክ በመጫን መረጃን ያግኙ፦

ኮቪድ-19 ከሰውወደሰውየሚዛመተው እንዴት ነው እንደምንስ ሊያስቆሙት ይችላሉ?

ኮቪድ-19 ከሰው ወደ ሰው የሚዛመተው

  • በቫይረሱ ተጠቅቶ ካለ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት በማድረግ ወይም በቫይረሱ የመያዙ ምልክት በግልፅ ከታወቀ ሰው ጋር በቅርበት የተገናኙ ሲሆን

  • በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሆኖ ከሚያስል ወይም ከሚያስነጥስ ሰው ጋር በቅርበት የተገናኙ እንደሁ

  • በቫይረሱ የተያዘ ሰው በሳል ወይም ንጥሻ የበከላቸውን ቁሶች ወይም ጠርዞች (እንደ የበር እጀታዎች ወይም ጠረጴዛዎች) ነክተው አፍዎን ወይም ፊትዎን የነኩ እንደሆነ ነው፡፡

ለመካላከልም የእጅን ንጽህና በመጠበቅ እና ሳልና ንጥሻን በመሽፍን እንዲሁም ጤንነት ካልተሰማዎ አካላዊ ርቀትዎን በመጠበቅ ቫይረሱን ለመከላከል ይችላሉ፡፡ እንዲሁም የሚከተሉትን ማድረግም ይጠበቅብዎታል ፦

  • የ1.5 ሜትር ማኅበራዊ ርቀትን ይጠብቁ እንዲሁም 1 ሰው በ 4 ስኩየር ሜትር ደንብን ይተግብሩ

  • እጆችዎን አዘውትረው በሳሙናና በውኃ ይታጠቡ፤ ምግብ ከመመገብዎ በፊትና ተመግበው ሲያበቁ፤ እንዲሁም መፀዳጃ ቤት ከተፀዳዱ በኋላ ይታጠቡ 

  • ሳልዎንና ንጥሻዎን ይሸፍኑ፤ የመፀዳጃ ወረቀቶችንና አልኮልነት ያላቸውን የእጅ ማፅጃዎች ይጠቀሙ

  • ጤንነት ካልተሰማዎት ከሌሎች ጋር ከመገናኘት ይቆጠቡ (ከሰዎች ጋር የ1.5 ሜትሮች ርቅትን ይጠብቁ) 

የአውስትራሊያ መንግስት ሁሉም ነዋሪዎች የኮቪድሴፍ አፕን እንዲጭኑ ምክሩን ይለግሳል፡፡ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን ድረ ገዕ ይመልከቱ፦

ምልክቶችን ካሳዩ ይመርመሩ

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ከአነስተኛ ሕመም እስከ የሳምባ ምች የሚደርስ ዘርፍ አላቸው። እንዲሁም  ከጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ ጋር ተመሳሳይነት አለው።

እነሱም፡

  • ትኩሳት

  • የመተንፈሻ አካል ህመም

  • ሳል

  • የጉሮሮ መከርከር

  • የትንፋሽ መቆራረጥ

  • ሌሎች ምልክቶች የአፍንጫ ፈሳሽ ፤ራስ ምታት ፤ የጡንቻ እና መገጣጠሚያ ህመም ፤ ማቅለሽለሽ ፤ ተቅማጥ ፤ ማስመለስ ፤ የማሽተት ስሜትን ማጣት ፤ የማጣጣም ስሜት መቀየር ፤ የምግብ ፍላጎትን ማጣት እና ድካም ይገኙበታል፡፡

በመስኩ የተሰማሩት ባለሙያዎች የኮቪድ 19 ምልክቶች ሲታዩ በቤታችን ሆነን እንዴት መለየት እንደሚችል የሚረዳ መንግድን አዘጋጅተዋል፡፡

ለኮሮናቫይረስ ምንም አይነት የተለይ መድሀኒት የሌለው ሲሆን አብዛኛዎቹ ምልክቶቹም በህክምና እንክብካቤ ሊቀንሱ ይችላሉ፡፡ ይሁን እና አንቲባዪቲክስ ቫይረሱን ለማስቆም ምንም የሚረዱት ነገር የለም፡፡

ምልክቶቹ ከታየብዎት ይመርመሩ። 

የሚሰማዎትን ምልክቶች በተመለከት ከባለሙያዎች ጋር መነጋገር ካስፈለገዎ የብሄራዊ ኮሮና ቫይረስ ልዩ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ምክርን ይጠይቁ።የስልክ መስመሩም ለ24 ሰአት በሳምንት ሰባቱንም ቀን አገልግሎት ይሰጣል፡፡ቁጥሩም  1800 020 080

የመመርመሪያ ጣቢያዎችን በተመለከተ የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ ፦

  • ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ማለትም ትምህርት ቤቶች ፤ የገበያ ማእከላት ፤ ሙአለ ህጻናት እና ዩኒቨርሲቲዎች መገኘት የለብዎትም፡፡

  • ምግብን እና ሌች መሰረታዊ ነገሮችንም ሌሎች ሰዎች ገዝተው እንዲያመጡና ከቤትዎ ደጃፍ ላይ አስቀምጠው እንዲሄዱ ይንገሩ ፡፡

  • ሁል ጊዜም አብሮዎት ከሚኖሩ ሰዎች በቀር በምንም አይነት ሌሎች ጎብኚዎችን በቤትዎ እያስገቡ ፡፡

ለብርቱ በሽታ የተጋለጡት እነማን ናቸው?

የተወሰኑ ሰዎች ለሕመም ተጋልጠው ሕመም ላያድርባቸው ይችላል፥ የተወሰኑቱ መለስተኛ የሕመም ምልክቶች አሳይተው በቀላሉ ይድናሉ፥ ሌሎች ግና በአጭር ጊዜ ውስጥ በጣሙን ለመታመም ይበቃሉ። ካለፉት ተሞክሮዎች በአብዛኛው ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ፦

  • አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ስር የሰደዱ ሕመሞች ያሉባቸው እድሜያቸው ከ 50 አመት በላይ የሆኑ ነባር ዜጎች እና ቶረስ ስትሬት አይላንደርስ ፤ 

  • እድሜያቸው ከ 65 አመት በላይ የሆኑና ስር የሰደዱ ሕመም ያሉባቸው ሰዎች ፡፡

  • እድሜያቸው ከ 70 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች

  • የሰውነት መከላከያ አቅማቸው የተደከመ ሰዎች ናቸው፡፡

የፊት መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ ይኖርብኛልን ?

አንዳንድ ክልሎች እና ግዛቶች የፊት መሸፈናኛ ጭንብልን በተመለከት ነዋሪዎች እንዲጠቀሙ ይመክራሉ አንዳንዶቹም መደረግ እንዳለብት ያስገድዳሉ ፡፡

በሚኖሩበት ክልል እና ግዛቶች የፊት መሸፈኛ ጭምብልን በተመለከተ የሚወጡት መመሪያዎች ሊቀያየሩ ስለሚችል ወቀታዊ መረጃዎችን መከታተል የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ለተጨማሪ መረጃ ፦

የፊት መሸፈኛ ጭንብልን በተመለከት ለአዳዲስ መረጃዎች የአካባቢውን መንግስት መመሪያ ይመልከቱ

የፊት መሸፈኛውን በሚጠቀሙ ጊዜ በትክክል ማድረጎትን እርግጠኛ መሆን ይኖርብዎታል ፦

  • ከማድረግዎ እና ማውለቅዎ በፊት እጅዎትን መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር ማጽዳት፤

  • የፊት መሸፈኛው አፍዎትን እና አፍንጫዎት መሸፈኑን እንዲሁም ከአገጭዎ በታች በትክክል መቀመጡን ያረጋግጡ እንዲሁም በአፍንጫዎ መነሻ እና በፊትዎ ሁለቱም አቅጣጫ መቀመመጡን እርግጠኛ ይሁኑ ፤

  • የፊት መሸፈኛውን በሚያደርጉበትም ሆነ በሚያወልቁበት ጊዜ የፊተኛውን ክፍል አይንኩ፤

  • የፊት መሸፈኛውን በአንገትዎ ዙሪያ ወይም በአፍንጫዎ ስር አያስቀምጡ ፤

  • ለአንድ ጊዜ ብቻ ተብለው የተዘጋጁ የፊት መሸፈኛዎችን ደግመው አይጠቀሙባቸው ፡፡

ክልሎች እና ግዛቶች የራሳቸን የገደብ ህጎች እስከ ድንበሮችን መዝጋት ደረስ በተግባር ማዋል ይችላሉ ፡፡

በግዴታ የሚደረጉ የመረጃ ስብሰባዎች

ከኦክቶበር 1 ፡ 2020 ጀምሮ በአገር ውስጥ በረራ የሚገቡ ሁሉ ስማቸውን ፤ የኢሜል አድራሻቸውን ፤ የሞባይል ቁጥራቸውን እና የሚኖሩበትን ከተማ የማሳወቅ ግዴታ ይኖርባቸዋል ፡፡ይህ መረጃ ሊኖሩ የሚችሉ የኮሮናቫይረስ ንክኪዎችን ተከታትሎ ለመያዝ የሚረዳ ነው፡፡

 

የህዝብ መጓጓዣዎች አገር አቀፋዊ መሰረታዊ ደንቦች

የህዝብ መጓጓዣ አገልግሎቶች በክለሎች እና ግዛቶች አስተዳዳሪዎች የሚመሩ ሲሆን የብሄራዊ የካቢኔ አባለት ጠንካራ የሆኑ ደቦችን ያወጣሉ፡፡ ይህውም የሰራተኞችን ጤና እና ደህንነት እንዲሁም የተሳፋሪዎችን ደህንነት ፤ በተለይም የጤና ችግር ከተሰማ ላለመጓዝ መወሰንን  ፤ በአሽከርካሪው እና ተሳፋሪዎች መካከል ያለውን አካላዊ ርቀት መጠበቅን እንዲሁም የጉዙ ክፍያ ገንዘብ መቀበልን ማስወገድን ያጠቃልላል ፡፡

የጉዞ ገደቦች

አለም አቀፍ ጉዞን በተመለከት ጊዜያዊ እርምጃዎች የተወሰዱ ሲሆን በየጊዜውም በመንግስት የሚሻሻሉ ናቸው፡፡

ይህውም ወደ አውስትራሊያ የሚያደርጉትን በረራ ሊያደናቅፍብዎት ይችላል፡፡ መረጆዎችም ቶሎ ቶሎ ይቀያየራሉ፡፡

አዳዲ ለሆኑ ተጨማሪ መረጃዎች 's ይመልከቱ ፡፡

ለይቶ ማቆያን እና ምርመራን በተመለከተ የሚመሩት በክልሎች እና የግዛት መንግስታት ነው፡፡

  • ጉዞዎ ከኮቪድ -19 ወረርሽን ጋር የተያያዘ እና የእርዳታን ስራ ለማድረግ ከሆነ

  • ጉዞዎ አስፈላጊ የሚባሉ የኢንዱስትሪ እና ንግድ ስራዎችን ( አስመጪ እና ላኪ )  ለማከናውን ከሆነ

  • የሚጓዙት በአውስትራሊያ የማይገኝን የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ከሆነ

  •  የሚጓዙት አስቸኳይ እና ሊቀር የማይችል የግል ጉዳይ ከገጠመዎ

  • ሊከለከል የማይቻልና ለግብረ ሰናይ ስራዎች

  • ጉዞዎ ለብሄራዊ የአገር ጥቅም ከሆነ

ከአውስትራሊያ ውጭ ለመጓዝ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን በተመለከት የሚከተለውን ሊንክ ይመልከቱ

      የመንግስት መረጃ

 የአገር ውስጥ ጉዳዮች - 


 

  • በአውስትራሊያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ሁሉ በመካከላቸው የ1.5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ አለባቸው፡፡በተጨማሪም መሰባሰብን በተመለከተ የክልሉ ንህጋዊ ገደብ ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

  • የጉንፋን ምልክቶችን ካሳዩ  በቤትዎ ይቆዩከዚያም ለሃኪምዎ ወይም የኮሮናቫይረስ የጤናመረጃ ልዪመስመር 1800 020 080 በመደወል ምርመራ እንዲደረግልዎ ሁኔታዎችን ያመቻቹ፡፡

  • ዜናዎችን እና መረጃዎች በ63 ቋንቋዎች ከ ያገኛሉ፡፡

 በክልልዎ ያለውን ተገቢ መረጃ በተመለከተ፦ 

 


Share
Published 24 March 2020 9:31pm
Updated 12 August 2022 3:03pm
By SBS Audio, Language Content
Presented by Martha Tsegaw
Source: SBS


Share this with family and friends