ኮቪድ- 19 ፡ እድሜያቸው ከ 5-11 የሆኑ ሕጻናት ከአሁን ጀምሮ ክትባትን መውሰድ ይችላሉ

ይህ የጃንዋሪ 10, 2022 የኮሮናቫይረስ በአውስትራሊያ አዲስ መረጃ ነው

La vaccination est ouverte pour les enfants de 5 à 11 ans.

Source: AAP Image/Bianca De Marchi

  • የትምህርት ቤቶች መከፈት እየተቃረበ እንደመምጣቱ መጠን ፤ እድሜያቸው ከ 5- 11 የሆኑ ሕጻናት ከአሁን ጀምሮ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ይችላሉ።
  • ሌተናንት ጀነራል ጆን ፍሪወን እንዳሉት ከሉት 10,000 የክትባት መስጫዎች ውስጥ አብዛኞቹ ለህጻናቱ ክትባቱን መስጠት የሚችሉ ናቸው ፤ ወላጆች ይህንን በመገንዘብ ቀጠሮዎች በሙሉ ላይገኙ ይችላሉ ብሎ ከመገመት በተደጋጋሚ መሞከር ይኖርባቸዋል።
  • ስኮት ሞሪሰን አዲስ መመሪያ ይፋ መሆኑን ያሳወቁ ሲሆን ፤ በተለይም አስፈላጊ በሚባሉ የሰራ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎች የቅርብ ንክኪ ቢኖራቸውም ፤ ሙሉ ለሙሉ ከተከተቡ እና የኮቪድ-19 ምልክቶችን እስካላሳዩ ድረስ ራሳቸውን ለይቶ ማቆየት አይጠበቅባቸውም ።
  • በኩዊንስላድ ተማሪዎች በፌብሩዋሪ 7 ወደ ትምህርት ገበታቸው እንደሚመለሱ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም ቀድሞ ታቅዶ ከነበረው ጃንዋሪ 24 በሁለላት ሳምንት ዘግይቶ ነው ።
  • በኒው ሳውዝ ዌልስ 2,030 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ፤ ከነዚህም መካከል እሁድ ይፋ ከሆነው ቁጥር 1,927 የሚሆኑት ውስጥ159 ያህሉ ከፍተኛ እንክብካቤ በሚያስፈልገበት ክፍል የሚገኙ ሲሆን ተጨማሪ 151 በዚሁ ይገኛሉ ።
  • በቪክቶሪያ በኮቪድ-19 ሳቢያ ለሆስፒታል የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር ከ752 ወደ 818 ከፍ ብሎ አድሯል ።
  •  በኩዊንስላድ 419 ሰዎች በሆስፒታል ክትትል የተደረገላቸው ሲሆን ከነዚህ መካከልም 21 የሚሆኑት ከፍተኛ እንክብካቤ በሚያስፈልገበት ክፍል የሚገኙ ሲሆን የተቀሩት 7ቱ  የመተንፋሻ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ።
  • በቪክቶሪያ ሶስተኛው የኮቪድ-19 ክትባት በተወሰኑ የስራ መስኮች ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች ግዴታ እንደሚሆን የጤና ሚኒስትሩ ማርቲን ፎሌይ አስታውቀዋል ።
  • የኒው ሳውዝ ዌልስ ፕሪምየር ዶሚኒክ ፔሮቴት ተጨማሪ 50 ሚሊየን ፈጣን የመመርመሪያ ቁሳቁሶችን ማዘዛቸውን ያሳወቁ ሲሆን ፤ ይህም የክለሉን አጠቃላይ ቁጥር ወደ 100 ሚሊዮን ከፍ ያደርገዋል ።
  • የኒው ሳውዝ ዌልስ መንግስት  በፈጣን መመርመሪያዎች የሚገኙ ወጤቶች ከያዝነው ሳምንት ጀምሮ ኒው ሳውዝ ዌልስ ሰርቪስ አፕ እንደሚመዘገብ ይፋ አድርጓል
  • አብዛኛዎቹ ክልሎችም በፈጣን መመርመሪያ የሚገኙ ውጤቶችን የሚመዘግቡበት ቅጾችን አዘጋጅተዋል ።
የኮቪድ -19 አሀዛዊ መረጃዎች

ኒው ሳውዝ ዌልስ  በፒ ሲ አር በተመረመረ ምርመራ 20,239 በቫይረሱ መያዛቸው የታወቀ ሲሆን 18 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል ። ኒው ሳውዝ ዌልስ በፈጣን መመርመሪያ የሚገኙ ውጤቶችን ገና መመዝገብ አልጀመረችም ።

ቪክቶሪያ 34,808 ዜጎቿ በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ሁለት ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል ።

ኩዊንስላድ ቢያንስ 9,581 ሰዎች መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን ባለስልጣናቱ የተቀሩትን በ ፒ ሲ አር እና በፈጣን መመርመሪያዎች የተወሰዱትን ወጤቶች በመቁጠር ላይ ናቸው ።

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 939 አዲስ ተያዦችን ያስመዘገበ ሲሆን በታዝማንያም 1,218 ሰዎች ተይዘዋል ።

በክልልዎ  ኮቪድ-19ን በተመለከተ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በቋንቋዎ ማግኘት ካሻዎ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ  .

ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ 

 and የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ 

የገንዘብ እርዳታ 

 የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ከ 70 እና 80 በላይ ከሆነ ጀምሮ የክፍለ ሀገሮች የኮቪድ-19 የአደጋ ጊዜ ክፍያ ህጎች ተለውጠዋል 

·        


 

 

 

 

iframe src="" data-module="iframe-resize_module"]


Share
Published 10 January 2022 4:27pm


Share this with family and friends