የፈረንጆቹ የገና በአል በተቃረበበት ወቅት የክልልና የግዛት መሪዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽ እንደገና ባገረሸባቸው አካባቢዎች ማለትም በሲድኒ ሰሜን የባህር ዳርቻ ( Norther Beach ) እና ግሬተር ሲድኒ አካባቢ በሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ በፍጥነት አዲስ የጉዞ ገደቦችን አስቀምጠዋል ፡፡
በሲድኒ እሁድ እለት ምርመራን ካደርጉት 70 ሰዎች መካከል የ 30 ዎች ውጤት ቫይረሱ እንዳለባቸው አሳይቷል ፡፡ ባለስልጣናቱም እንደሚሉት የቫይረሱ ምንጭ አሁንም አለመታወቁ ነው፡፡
ባለፈው ቅዳሜ የክልሉ ፕሪምየር ግላዲስ በርጂክሊያን እንዳሉት የሲድኒ ሰሜን የባህር ዳርቻ ( Norther Beach ) እና ግሬተር ሲድኒ አካባቢዎች እንደገና ከእሁድ ከምሽቱ 5፡00 እስከ ረቡእ አኩለ ለሊት ድረስ ሙሉ ለሙሉ ዝግ ይሆናሉ ፡፡
“ በመሰረቱ አሁንም ተመልሰን የምንገባው ባለፈው ማርች ወር ላይ እዳደረግነው ሙሉ ለሙሉ ዝግ የማድረግ ሂደት ውስጥ ነው ” ብለዋል ፡፡
አስደንጋጭ የሆነው የቁጥር መጨመር በሲድኒ እና ኒውሳውዝ ዌልስ ነዋሪዎች ላይ አዲስ የጉዞ ገደብ እዲቀመጥ አድረጓል ፡፡
ቪክቶርያ
ግሬተር ሲድኒ የሴንትራል ኮስት እና የብሉ ማውንቴንስ ጨምሮ ያለውን አካባቢ ‘ የአደጋ ቀጠና ’ በማለት ፕሪምየር ዳንኤል አንድሪውስ የገለጹት ሲሆን በዚያ የሚኖሩ ነዋሪዎችም ከእሁድ እኩለ ለሊት ጀምሮ ወደ ቪክቶርያ መጓዝ እንደማይችሉ ተናግረዋል ፡፡
ወር ቪክቶርያ የሚገቡ ሁሉ ለ 14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ሆቴል የመቀመጥ ግዴታ አለባቸው ፡፡
የቪክቶርያ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው ተመልሰው እንዲመጡ ተጨማሪ የ 24 ሰአት ገደብ የተቀመጠ ሲሆን እንደደረሱም ራሳቸውን ለ 14 ቀናት ለይተው ማቆየት ይኖርባቸዋል ፡፡
ከሰኞ እኩለ ለሊት በኋላ የሚመለሱ ሁሉ ራሳቸውን ለ 14 ቀናት በሆቴል ለይተው ማቆየት ይኖርባቸዋል ፡፡

Source: AAP
ድንበሩን መዝጋትን በተመለከተ “ አስፈላጊ እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ ” ዝግ ሆኖ የሚቆይ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ፤ የሲድኒ ሰሜን የባህር ዳርቻ ( Norther Beach ) ላይ የተቀመጠው ገደብ በመጪው ረቡእ ሲነሳ አብሮ የማይነሳ መሆኑን አሳስበዋል ፡፡
በአሁን ሰአት በቪክቶርያ ያሉ እና በዲሴምበር 11 እና ከዚያ ጅምሮ በሲድኒ ሰሜን የባህር ዳርቻ ( Norther Beach ) አካባቢ የነበሩ ሁሉ ራሳቸውን ለይተው ማቆየት እና እና ምርመራው ማድረግ አለባቸው ፡፡
ኩዊንስላንድ
የኩዊንስላንድ የጤና ባለስልጣናት ክልሉ ወሰኑን በግሬተር ሲድኒ ነዋሪዎች ላይ ዝግ ማድረጉን አስታውቀዋል ፡፡
ከሰኞ ንጋት 1፡ 00 በኋላ የግሬተር ሲድኒ አካባቢ በይፋ የአደጋ ቀጠና ተብሎ ተሰይሟል ፡፡
ማንኛውም ሰው በሲድኒ ፣ ብሉ ማውንቴንስ ፣ ሴንትራል ኮስት ፣ እና ኢላዋራ -ሾአልሄቭን አካባቢ ከዲሴምበር 11 ጀምሮ የነበረ ሁሉ የተለየ ፈቃድ ከሌለው በቀር ወደ ክልሉ ለመግባት አይፈቀድለትም ፤ ወደ ሆቴል በመሄድ ራሳቸውን ለ 14 ቀናት ለይተው ማቆየት ይጠበቅባቸዋል ፡፡
የኩዊንስላድ ነዋሪዎች ወደቤታቸው ለመመለስ ተጨማሪ 24 ሰአት ያላቸው ሲሆን ይህም የሚያበቃው ማክሰኞ ከሌሊቱ 1፡00 ላይ ይሆናል ፡፡ እደደረሱም ራሳቸን ለ14 ቀናት ለይተው ማቆየት እና መመርመር ይኖርባቸዋል ፡፡

Queensland Premier Annastacia Palaszczuk speaks during a press conference in Brisbane, Sunday, 20 December, 2020. Source: AAP
የኩዊንስላዷ ፕሪምየር አነስተሲያ ፓለሼ በእሁድ እለቱ ንግግራቸው “ ከግሬተር ሲድኒ አካባቢ ከሆኑ ይህ ጊዜ ወደ ኩዊንስላድ የሚጓዙበት አይደለም ” ብለዋል
ኩዊንስላድ በመንገድ ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር በኒውሳውዝ ዌልስ ድንበር ላይ እንደገና በተግባር አውላለች ፡፡
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
ከእሁድ እኩለ ለሊት ጅምሮ የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ማንኛውም ሰው ከሲድኒ ፣ ሴንትራል ኮስት ፣ ኢላዋራ -ሾአልሄቭን እና ኒፖን ፤ ብሉ ማውንቴንስ የሚመጡ ሁሉ ራሳቸውን ለ 14 ቀናት ለይተው ማቆየት ይጠበቅባቸዋል ፡፡
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪ ካልሆኑ እና በተጠቀሱት አካባቢዎች ቆይተው ከነበረ መልእክታችን ... ወደ አውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አይጓዙ ነው , በማለት የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከፍተኛ የጤና ሀላፊ ኬሪአን ኮልማን እሁድ እለት ተናግረዋል ፡፡
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ጤና ቢሮ ከተጠቀሱት አካባቢዎች ለሚመጡ ነዋሪዎች በጣም የተለየ የሚባል የሚያሳምን ምክንያቶችን ካላቀረቡ በቀር ምንም አይነት የተለየ ፈቃድ የማይሰጥ መሆኑን ዶ / ር ኮልማን አያይዘው አሳስበዋል ፡፡
“ ይህ ለበርካቶች አስቸጋሪ የሚሆንበት ምክንያትን ግልጽ የማይሆንልኝ ሲሆን በእኔ በኩል በጥብቅ የማሳስበው ውሳኔያችንን በቀላሉ የማናየው መሆናችንን ነው ፡፡
“ በማህበረሰባችን ላይ የሚጣሉት ገደቦች አስፋላጊ ሲሆኑ ብቻ እንደመሆኑ መጠን ፤ ይህም ከገና በአል እስከ አዲስ አመት ድረስ ሊቀጥል ስለሚችል ማህበረሰባችን ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ እናሳስባላን ”
ዌስተርን አውስትራሊያ
ዌስተርን አውስትራሊያ በሲድኒ ሰሜን የባህር ዳርቻ ( Norther Beach ) አካባቢ ያገርሸውን የኮሮና ቫይረስ ተከትሎ በበኒውሳውዝ ዊልስ አካባቢ ያላትን ዳርቻ እንደገና መዝጋቷን ፕሪምየር ማርክ መክጋወን አስታውቀዋል፡፡
ከቅዳሜ እኩለ ለሊት ጀምሮ የኒውሳውዝ ዌልስ “ አነስተኛ አደጋ ” አላባቸው የተባሉት አካባቢዎች “ መካከለኛ አደጋ ” ወደሚለው ከፍ ብሏል ፡፡
ከዲሴምበር 20 በኋላ ከኒው ሳውዝ ዊልስ ወደ ክልሉ በአውሮፕላን መግባት የሚችሉት የተለየ ፈቃድ ያላቸው ብቻ ናቸው ፡፡
አቶ መክጋውን እንዳሉት “ በዚህ ሰአት ይህንን “ አስቸጋሪ ውሳኔ” መወሰን ይከብዳል ፡፡
“ ቤተሰቦቻችው ለገና እና አዲስ አመት ለማየት እና ለመገናኘት ለሚሹ ሁሉ ይህ ውሳኔ እንደሚጎዳቸው እረዳለሁ ” ብለዋል ፡፡
ኖርዘርን ቴሪሮሪ
ኖርዘርን ቴሪሮሪ ለግሬተር ሲድኒ ተጓዦች ወሰኗን ሙሉ ለሙሉ መዝጋቷን ተጠባባቂ ሚኒስትሯ ኒኮል ማኒሰን እሁድ እለት ከሰአት በኋላ ባደረጉት ንግግር ላይ አስታውቀዋል ፡፡
ከሲድኒ ፣ ብሉ ማውንቴንስ ሴንትራል ኮስት እና ኢላዋራ ፤ የሚመጡ ሁሉ ራሳቸውን ለ 14 ቀናት ለይተው ማቆየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
“እንደተናገርነው እኛ ቅድሚያ የምንሰጠው በግዛታችን የሚኖሩ ነዋሪዎቻንን ህይወት መታደግ ነው ፤ ማድረግ ካለብንም ከዚህ በበለጠ በስፋት እና በፍጥነት እናደርገዋለን ”ሲሉ ማኒሰን ለሪፓርተሮች ተናግረዋል ፡፡
አያይዘውም ገደቡ የተጣለው በቅጽበት ነው ምንም እንኳን ከሲድኒ የሚጓዙ መንገደኞችንም ያለምርጫ ያስቀረ ውሳኔ ቢሆንም፡፡
እንደደረሱም ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ስፍራ እንዲቀመጡ ምርጫ ይሰጣቸዋል፤ ይህንን ካልተቀበሉ ግን በመጡበት በረራ ተመልሰው ወደ ሲድኒ እንዲሄዱ ይደረጋል ፡፡
ታዝማንያ
የጤና ባለስልጣናቱ የኖርዘርን ቢች አካባቢ ከፍተኛ አደጋ ያለበት መሆኑን የአካባቢው መንግስት የገለጸ ሲሆን በአካባቢው ከዲሴምበር 11 ጀምሮ የተጓዙ የተለየ ፈቃድ ከሌላቸው በቀር ወደ ታዝማንያ እንዳይገቡ ከልክሏል ፡፡
ማንኛውም የታዝማንያ ነዋሪ የሆነ እና በተጠቀሱት ቀናት ወደዚያ አካባቢ የተጓዘ ሁሉ ራሱን ለ14 ቀናት ለይቶ ማቆየት እና መመርመር ይኖርበታል ፡፡
የሲድኒ ሆባርት ያች ሬስ በታሪክ ለመጃመሪያ ጊዜ እንዳይካሄድ ተደርጓል ፡፡ አዘጋጆቹ እንደገለጹት በሲዲኒ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዝግጅቱ እንዳይካሄድ አድርጎታል ብለዋል ፡፡
ሳውዝ አውስትራሊያ
የሳውዝ አውስትራሊያ ፕሪምየር ስቲቭ ማርሻል እንዳሉት ከእሁድ እኩለ ለሊት ጀምሮ ድንበራቸው ለግሬተር ሲድኒ ነዋሪዎች ዝግ አድርገዋል ፡፡ በተያያዥም ወደ አደላይድ አየር ማረፊያ በሚያቀናው መንገድ ላይም የCOVID19 ጊዜያዎ መመርመሪያ ጣቢያዎች የሚከፈቱ ይሆናል ፡፡
ከግሬተር ሲድኒ አካባቢ የሚመጡ ነዋሪዎች ሁሉ ለ 14 ቀናት ተለየተው እንዲቀመጡ የሚገደዱ ሲሆን ከኖርዘርን ቢች አካባቢ የሚመጡ ነዋሪዎች ወደመጡበት እንዲመለሱ ይደረጋሉ፡፡
በአውስትራሊያ የሚኖሩ ነዋሪዎች በመካከላቸው የ 1.5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ አለባቸው ፡፡ በጋራ የመሰባሰብ ገደብን በተመለከት የክልልዎትን መመሪያ መመልከት ያስፈልጋል ፡፡
ዜናዎችን እና መረጃዎችን በ63 ቋንቋዎች ከsbs.com.au/coronavirusያግኙ፡፡የክልልዎትን መመሪያ በተመለከተ , , , , , ,