አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ ተስፋን በተላበሰ ርዕይ አውስትራሊያን አንድ ለማድረግ ቃል ገቡ

አዲሱ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር በምርጫ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ለአውስትራሊያውያን "ማለፊያ መፃዒ ጊዜን" ለማስገኘት ቃል ገብተዋል። ሆኖም የምርጫ ድምፆች ቆጠራቸው ቀጥሎ ባለበት ወቅት አናሳ መንግሥት ዕጣ ፈንታ የመግጠም ሳንካም ከፊታቸው ተደቅኗል።

Anthony Albanese celebrates with his partner Jodie Haydon and son Nathan Albanese after after winning the 2022Leader Anthony Albanese celebrates with his partner Jodie Haydon and son Nathan Albanese after after winning the 2022 Federal Election

Anthony Albanese celebrates with his partner Jodie Haydon and son Nathan Albanese after after winning the 2022 Federal Election Source: AAP / BIANCA DE MARCHI/AAPIMAGE

 

ሌበር እስካሁን በይፋ 72 የምክር ቤት ወንበሮችን ያሸነፈ ሲሆን ራሱን ችሎ አብላጫ መንግሥት ለማቆም ተቃርቧል። ሊብራል/ናሽናልስ 50 የግል ተወዳዳሪዎች 10 ግሪንስ ሶስት ወንበሮችን ያሸነፉ ሲሆን፤ ከ12 በላይ ወንበሮች አሸናፊዎቻቸው አልተገለጠም። የድምፅ ቆጠራዎች በመጪ ቀናት ውስጥ ይቀጥላሉ። ባለፈው ፓርላማ የሌበር ፓርቲ 68 ወንበሮች ነበሩት። 

ውጤቱ ከዘጠኝ ዓመት ተቃዋሚ ቡድንነት ቆይታ በኋላ በሌበር መንግሥት የሚመራ የአገሪቱ ፓርላማ ውስጥ መቆም አዲስ ምዕራፍ ነው። 

ሲድኒ ካምፐርዳውን ማኅበራዊ መኖሪያ ቤት ያደጉት አቶ አልባኒዚ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ሲያደርጉ በግልፅ በሚታይ ሲቃ "ለአውስትራሊያውያን ወገኖቼ ለዚህ ታላቅ ክብር ምስጋናዬን አቀርባለሁ" ብለዋል። 
"ዛሬ ምሽት አውስትራሊያውያን ለለውጥ ድምፃቸውን ሰጥተዋል" ያሉት አቶ አልባኒዚ የአካል ጉዳተኛ ተጠዋሪ ለነበሩት እናታቸው ሜሪአን ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የእሳቸው የግል ጉዞ "አውስትራሊያውያን ከዋክብትን እንዲነኩ" የሚያነቃቃ እንደሚሆንም ተስፋቸውን ገልጠዋል።

አክለውም "አውስትራሊያውያንን ወደ አንድነት ማምጣት እሻለሁ" 

"የጋራ ትልማችን ፍራቻን ሳይሆን አንድነትን፣ ፍራቻና ክፍፍልን ስይሆን ተስፋን የሚሰብክ እንዲሆን እጠይቃለሁ" ብለዋል። 
አክለውም፤ የኡሉሩን መግለጫ ዕውን ለማድረግ፣ "የአየር ንብረት ጦርነቶችን" ለማክተም፣ ምርታማነትን በማልጎበት ደመወዝን ለማሳደግ ከሠረተኛ ማኅበራትና የንግድ ማሕበረሰብ ጋር በጋራ ለመሥራት የቆረጡ መሆኑን ተናግረዋል።   

ቆጠራው እየተካሄደ ያለም ቢሆን አቶ አልባኒዚ አብላጫ ወንበሮች ያሉት መንግሥት ማቆም ይችላሉ፤ ሆኖም አናሳ መንግሥት የማቆም ሁኔታን ግድ የሚል ሁነትም ሊገጥማቸው ይችላል። 


የሌበር ድል ቀጣዩን የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር መንግሥት ለማቆም ከግሪንስና የግል ተወዳዳሪዎች ጋር ከመደራደር የሚያድን አይደለም።
 
እስከ ትናንት እኩለ ለሊት ባለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮች ሌበር 68 ሊብራል / ናሽናልስ 46 ምናልባትም ግሪንስ ሶስት የግል ተወዳዳሪዎች ስድስት ናቸው።
 
30ኛው የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ከምሽቱ 11pm በፊት ድል መነሳታቸውን በማመን ለአቶ አልባኒዚ ስልክ መትተው እንኳን ደስ ያለዎት ሲሆን፤ “ይህች አገር የመረጋጋት መኖር በጣሙን አስፈላጊ ነው። ለዚህች አገር ወደፊት መራመድ በጣሙን አስፈላጊ ነው" ሲሉ በምርጫው ምሽት ከሊብራል ፓርቲ ዋና የምርጫ ማዕከል ተገኝተው ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል። 
Outgoing Prime Minister Scott Morrison concedes defeat in the 2022 Federal Election, at the Federal Liberal Reception at The Fullerton Hotel, Sydney
Outgoing Prime Minister Scott Morrison concedes defeat in the 2022 Federal Election, at the Federal Liberal Reception at The Fullerton Hotel, Sydney Source: AAP/ DEAN LEWINS/AAPIMAGE
አቶ ሞሪሰን የአገር አመራራቸው ወቅት "ታላቅ የሁከት ጊዜ" ጠቅሰዋል። ከፓርቲ መሪነታቸውም መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። 





 
“በፖለቲካችን ውስጥ ታላቅ መናጠብ እንደገጠመን ከዛሬው የሰዎች ለዋነኛ ፓርቲዎች ድምፅ አሰጣጥ አይተነው የማናውቀው ዝቅተኛ የመጀመሪያ ድምፅ ተመልክተናል"


“ይህ ለአገራችን ድኽነት በጣሙን ጠቃሚ ነው" ብለዋል።


የሴት የግል ተወዳዳሪዎች ቀደም ሲል የፓርቲው ማዕከል የተሰኙ የምክር ቤት ወንበሮችን ይዘው የነበሩ ቁልፍ የሊብራል ምክር ቤት አባላትን ድል በመንሳት ለስኮት ሞሪሰን ዳግም አለመመረጥ ብርቱ ጉዳት አድርሰዋል። 
 
በጅሮንድ ጆሽ ፍራይደንበርግ በኩዮንግ የግል ተወዳዳሪዋ ሞኒክ ራያን ለሽንፈት መብቃታቸውን ያልካዱ ሲሆን፤ ምናልባትም በጥምር መንግሥቱ መጠነ ሰፊ ድጋፍ እጦት ሳቢያ ከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ሰለባ ሆነዋል።


“ከስሌት አኳያ ኪዮንግ ለማሸነፍ የምንችል ቢሆንም በእርግጠኝነት አዋኪ ነው" ሲሉ አቶ ፍራይደንበርግ የምርቻው ምሽት ተናግረዋል። 


በአየር ንብረት 200 ቡድንና በሕዝብ የገንዘብ ድጋፍ አግኝተው የተቀናጁት የግል ተወዳዳሪዎች የአየር ንብረት ለውጥ፣ የፀረ ሙስና ኮሚሽንንና የፆታ እኩልነትን አስመልክቶ የተካሂደው ረቀቅ ያለ የምርጫ ዘመቻ አስተውሎትና ተቀባይነትን አግኝቷል።
 
ውጤቱም የሊብራል ፓርቲ ጠንካራ ድጋፍ አለኝ ብሎ ያመነባቸውን ወንበሮች ማጣት መሆኑ ፓርቲውን መልሶ ራሱን እንዲመረምር ግድ አሰኝቷል።
 
የሊባራል ሴናተር ሳይመን በርሚንግሃምን “ለውጤቱ ፆታ ምክንያት መሆኑ ግልፅ ነው”  ፓርቲው ተጨማሪ ሴቶችን እንዲያክል "ፍጹም" የሆነ "ግልፅ መልዕክትን" ተቀብሏል አሰኝቷል። 
 
”ከእኒህ መራጮች ዕሴቶች ጋር የሊብራል ፓርቲ ተመልሶ ሊያያዝ ይገባል" ሲሉ ለ ABC ገልጠዋል።


የሌበር በምርጫ ወደ ስልጣን መውጣት አንቶኒ አልባኒዚ የምርጫ ዘመቻቸውን በይፋ በከፈቱበትና ብርቱ የምርጫ ዘመቻ ባካሄዱበት የምዕራብ አውስትራሊያ ቀይ ማዕበል ጎልብቷል። 


ምዕራብ አውስትራሊያ ውስጥ የሊብራል ፓርቲ ምክር ቤት አባል የነበሩት ክሪስቲያን ፖርተር በሌበር ዕጩ ትሬሲ ሮበርትስ ድል ተነስተዋል። በተጨማሪም ሌበር ስዋንን ከሊብራል ፓርቲ ወስዷል። 


እንዲሁም የቀድሞው የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሚኒስትር የነበሩት ኬን ውያት ይዘውት የነበረውን ሃስላክ የምክር ቤት ወንበር በሌበር ሊወሰድ ተቃርቧል። 
 
ያልተጠበቁ አስገራሚ ውጤቶች
የሌበር ክሪስቲና ኬኔሊን ወደ ምዕራብ ሲድኒ ፎውለር ዕጩ አድርጎ ማቅረብ ነባር የሌበር መቀመጫ የነበረውን የምክር ቤት ወንበር በግል ተወዳዳሪዋ ዳይ ሊ ሊነጠቅ እየተመራ ነው። 


እስከ ቅዳሜ እኩለ ለሊት የሌበር ፓርቲ 20 ፐርሰንት ድጋፍ አጥቷል። 


ይሁንና በአጎራባች ሪድ የሌበር ዕጩ ሳሊ ሲቱ ከሊብራል የምክር ቤት አባል ፊዮና ማርቲን አሸንፈው ለመውሰድ ተቃርበዋል። 


Sally Sitou, who will become the Labor MP for the NSW seat of Reid
Sally Sitou, who will become the Labor MP for the NSW seat of Reid Source: AAP / DEAN LEWINS/AAPIMAGE

Share

Published

Updated

Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS


Share this with family and friends