አንኳሮች
- የ'እደግፋለሁ' ዘመቻ ፌብሪዋሪ መገባደጃ ላይ ይጀምራል
- ረቂቅ ድንጋጌው ለፓርላማ ቀርቦ ክርክር ይካሔድበታል
- ረቂቅ ድንጋጌው በወርሃ ሜይ በፓርላማ ይሁንታን አግኝቶ ፅድቅ እንዲቸረው ይጠይቃል
የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሚኒስት ሊንዳ በርኒ ድምፅ ለፓርላማ ሕገ መንግሥቱ እንዲሠፍር ለማስቻል ሕዝበ ውሳኔ በወርሃ ኦገስት መጀመሪያ ላይ ሊካሔድ እንደሚችል ገለጡ።
ሚኒስትሯ ከሲድኒ ሞሪኒንግ ሔራልድ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የ 'እደግፋለሁ' ዘመቻ ፌብሪዋሪ መገባደጃ ላይ እንደሚጀመርና ረቂቅ ሕጉ በወርሃ ማርች ለፓርላማ ውይይት እንደሚቀርብ ተናግረዋል።
አክለውም፤ ዘመቻውን ማንቀሳቀስ ከጀመርን በኋላ አገሪቱን ለለውጥ ዝግጁ እናደርጋለን፤ ረቂቅ ድንጋጌው በሜይ ላይ ይሁንታን አግኝቶ ካለፈ በኋላም ሕዝበ ውሳኔው ቀደም ካለ በኦገስት፤ ከዘገየም ኖቬምበር ላይ እንደሚካሔድ አመላክተዋል።
ቴኒስ
የሜዳ ቴኒስ ኮከቡ ራፋኤል ናዳል ቅዳሜ ዲሴምበር 31 ከካሜሩን ኖሪ ጋር ለዩናይትድ ዋንጫ በሲድኒ ኬን ሮዝዌል ኧሬና ባደረገው ግጥሚያ 3-6, 6-3, 6-4 ውጤት ተረትቷል።
ይህንኑ ሽንፈቱን ተከትሎ ከጋዜጠኞች ከቴኒስ ለመጠወር ያስብ እንደሁ ተጠይቆ ሲመልስ "የተሸነፍኩት ግጥሚያውን ነው፤ አለቀ" በማለት ከቴኒስ የመሰናበትና አለመሰናበት ጥያቄን አሌ ብሎ አልፏል።